Site icon Dinknesh Ethiopia

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ እና ቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሜ ወረዳ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ይፋ ሆኑ

ታህሳስ 2016 ዓ.ም

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 

1. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ – ኢሰመጉ በበጎ አድራጎትና ማኅበራት አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሠረት ሐገር በቀል ድርጅት ሆኖ በ 1984 ዓ.ም የተመሠረተና በምዝገባ ቁጥር 1146 ከ 02/11/11 ዓ.ም ጀምሮ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዳግም ተመዝግቦ በሕጋዊነት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ነው፡፡ ኢሰመጉ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ነጻና ገለልተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተከላካይ ተቋም ሲሆን፣ ዓላማውም በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት፣ ለሕግ የበላይነት መስፈንና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የበኩሉን አስተዋጽዖ ማድረግ ነው፡፡

ኢሰመጉ የተቋቋመበት ዋነኛ ዓላማው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የጎለበተባት፣ የሕግ የበላይነት የሰፈነባት እና ሰብዓዊ መብቶች የሚከበሩባት ኢትዮጵያን ማየት ነው፡፡ በሥራውም ከማናቸውም የፖለቲካ ፓርቲ፣ የኃይማኖት ተቋም፣ የብሔረሰብ ቡድን፣ ማኅበራዊ መደብ ወዘተ የማይወግን፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ነጻና ገለልተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተከላካይ ተቋም ነው። ኢሰመጉ ላለፉት 30 ዓመታት በቆመላቸው ዐበይት ዓላማዎች ላይ በመመርኮዝ ሁለንተናዊ፣ ሐገራዊና ሕዝባዊ ተልዕኮ በመያዝ በነደፋቸው በርካታ የመርሐ -ግብር ተግባራት አማካኝነት ሰብዓዊ መብቶች \እንዲከበሩ፣ የሕግ የበላይነትና ሕጋዊ ሥርዓት እንዲሰፍንና በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲኖር የበኩሉን አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ይገኛል።

የኢሰመጉ ዋነኛ ተግባሩ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብቶችን አያያዝና ሁኔታ መከታተል፣ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በማጣራትና በመተንተን በማስረጃ የተደገፉ መግለጫዎችን ማውጣት ነው። ኢሰመጉ በሚያወጣቸው መግለጫዎች ሁሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተጎጂዎች ፍትሕና ካሣ እንዲያገኙ፣ የጥሰት ፈጻሚዎች በሕግ እንዲጠየቁና ወንጀል ሠርቶ በነጻ የመኖር ልማድ እንዲያበቃ፣ ከእያንዳንዱ ክስተት ትምህርት ተወስዶ ለወደፊቱ ጥንቃቄና ተገቢው የፖሊሲና የአፈጻጸም እርማት እንዲደረግ ሲወተውትና ሲጠይቅ ቆይቷል፣ አሁንም በመጠየቅ ላይ ነው፤ ለወደፊትም በዚሁይቀጥላል። ከኢሰመጉ የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ተግባራት መካከል፣ የሕግ ታራሚዎችን መጎብኘትና ሰብዓዊ መብቶቻቸው መጠበቃቸውን መከታተል፣ የፍርድ ቤቶችን ሒደት ፍትሓዊነት መከታተል እንዲሁም በመንግሥት የወጡና የሚወጡ ሕጎችን ይዘትና አፈጻጸማቸውን ከሰብዓዊ መብቶች አንጻር መመርመር ይገኙበታል። ከእነዚህ በተጓዳኝ ኢሰመጉ በተለይ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ሰለባ ለሆኑ ሰዎች የተለያየ ደረጃና መልክ ያለው የሕግ ድጋፍ ይሰጣል።

በእስካሁኑ ቆይታው ኢሰመጉ 39 መደበኛ መግለጫዎችና 153 ልዩ መግለጫዎችን በተጨማሪም በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በርካታ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን ይፋ አድርጓል። ኢሰመጉ አሁን በሚገኝበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም ቢሆን፣ ሁኔታና ዐቅም በፈቀደለት መጠን የሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ የሕግ የበላይነት እና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ በኢትዮጵያ እውን እንዲሆን ካለው የጸና ዓላማ አኳያ በመሥራት ላይ ይገኛል።

 

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ 

Exit mobile version