Dinknesh Ethiopia

አሳዛኝ የኢትዮጵያኖች እልቂት በኤደን ባሕር ሰላጤ፣

Ethiopian Solidarity Movement

አሳዛኝ የኢትዮጵያኖች እልቂት በኤደን ባሕር ሰላጤ

አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ

August 7, 2025

የኢትዮጵያውያን ትብብር ንቅናቄ (ኢትን) በኤደን ባሕር ሰላጤ August 3, 2025, በደረሰው የጀልባ መገልበጥ አደጋ በንፁሀን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ በደረሰው እልቂት የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን መግለፅ እንወዳለን።

በዚህ አሳዛኝ ሁኔታ 68 ሰዎች መሞታቸው የተረጋገጠ ሲሆን፣ ሌሎች 76 ሰዎች እስከ አሁን በተደረገው አሰሳ ያልተገኙ መሆናቸውን አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት አረጋግጧል። አዲስ በሚደርሰን ዜና የሟቾች ወገኖቻችን ቁጥር ክ140 በላይ ደርሷል። እነዚህ ስደተኞች አብዛኛዎቹ ወጣቶች ሲሆኑ፣ ከራያ አካባቢ ሰሜን ኢትዮጵያ እንደሆነ ተገልጻል።

ይህ ልብ የሚሰብር ሁኔታ በኤደን ባሕር ሰላጤ ሲደርስ የመጀመሪያው አይደለም፤ ከዚህ በፊትም ብዙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በዚህ ባሕረ ሰላጤ ውስጥ ሰጥመዋል። ባለፈው ዓመት ብቻ 558 ስደተኞች በዚህ ባሕር ውስጥ ሞተዋል። ብዙዎች የሚሰደዱት፣` በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ መቋቋም ስለአቃታቸው፣ ወደ አረብ አገሮች በመሄድ የተሻለ ኑሮ ለመኖር ተስፋ በማድረግ ነው።

እነዚህ ወጣቶች ኑሮን ለማሸነፍ ብቻ ሳይሆን፣ በ ገር ውስጥ ያለውን አስከፊ ድህነት፣ የፓለቲካ ግጭትና የዘር ፓለቲካ ያደረሰውን ጭቆና ለመሸሽ ነው። የኢትዮዮጵያ መንግስት ወጣቱን ለዚህ ስደት ያበቃውን ችግር መሠረታዊ መፍት ከመስጠት ይልቅ፤ በየቦታው ዜጎችን በመከፋፈልና እርስ በርሳቸው እንዲተላለቁ የማድረግ ስልቶች ላይ ተጠምዶ ይታያል።

(ኢትን) የሚከተሉት ጉዳዮች በአስቸኳይ መፍት ይጠይቃል፦

፩ኛ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የሚደረጉ ጦርነቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ፣

፪ኛ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያሳተፈ የፓለቲካ መፍትሔ እንዲፈልግና፣ በ አስተማማኝ የኑሮ ዋስትና መስጠት፣ እንዲያገኙ ገሪቱ ሰላም፣ መከባበርና ለሕዝቡ

፫ኛ ስደተኞችን በሕገ ወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩትን ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ፣ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ፣

፬ኛ የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡም በዓብይ አህመድ አስተዳደር ላይ ጠንካራ ተፅ እንዳይሰደድ ማድረግ።

በመጨረሻም ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ስደተኞችን ለመርዳ የሚያደርገውን ጥረት እያደነቅን በተጨማሪ በዲፕሎማሲውም መድረክ አስፈላጊውን ተፅዕኖ እንዲያደርግ እንጠይቃለን።

የሚዲያ ግንኙነት ለሚፈልጉ፣
የኢትዮጵያውያን ትብብር ንቅናቄ (ኢትን)
Email: contact@ethiopiansolidarity.org
Website: www.ethiopiansolidarity.org

Exit mobile version