ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ
እያንዳንዱ አገር በአጭርና በረጅም ጊዜ ለማሳካት የሚሻቸው ሦስት – አራት የኤኮኖሚና የልማት ግቦች አሉት። እነዚህም የኤኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ፣ የሥራ ዕድል መፍጠርና የህዝቡን ህይወት የሚያሻሽሉ ልማቶች እንዳይደናቀፉ “ፊስካል” ና “ሞነታሪ” ፖሊሲዎችን እንዳስፈላጊነታቸው መውሰድ ነው።እነዚህም የባንኮችን የወለድ መጠን ማሳደግ ወይንም መቀነስ፣ ባንኮች መያዝ ያለባቸውን ሪዘርቭ መጨመር ወይንም መቀነስ፣መንግሥት ቦንዶችንና ዋስትናዎችን (ሴኩሪቲስ) መግዛት ወይም መሸጥ፣ እንዲሁም የገንዘብ የውጭ ምንዛሪ ተመንን ማስተካከል፣ ይህም መጨመር ወይም መቀነስ ሊሆን ይችላል። የዋጋ ግሽበት በሚኖርበት ሁኔታ፣ የዋጋ ግሽበትን (inflation) ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ርምጃዎች ይወሰዳሉ። እነዚህን ግቦች ለማሳካትና አገራቸውን የተሻለ ለማድረግ አገሮች የገንዘብና (ሞኔታሪ) ና የፊስካል ፖሊሲዎችን ይጠቀማሉ። የፊስካል ፖሊሲ መንግሥት ታክስ እንዲሰበስብና በመንግሥት የተለያዩ የሥራ ዘርፎች፣ እንደ መሠረተ-ልማት፣ ትምህርት፣ የጤናና የመሳሰሉት ላይ እንዲውል በማድረግ በዋናነት በአገር ውስጥ ኤኮኖሚ ላይ ብቻ የሚያተኩር ሲሆን፣ የገንዘብ ፖሊሲ ደግሞ ከሀገር ውስጥና ከዓለም አቀፍ ኤኮኖሚ ጋር የተያያዘ ነው። ይህ ማለት መንግሥት የገንዘብ ፖሊሲንና ፊስካል ፖሊሲዎችን ከሀገር ኢኮኖሚያዊ ጤንነት አኳያ መምሮ ይተገብራል ማለት ነው። ከፊስካል ፖሊሲዎች አንዱ የሆነውን የብር ምንዛሪ-ተመን ቅነሳ ወይም መጨመር የማድረግን ፖሊሲን በመጠቀም የሀገር ውስጥና የውጭ ገበያን እንደየአስፈላጊነታቸው ይነካል፣ ያስተካክላል ማለት ነው።
በቅርቡ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ገንዘብ በብድርና በዕርዳታም እንድንሰጣችሁ ከፈለጋችሁ የኢትዮጵያን ገንዘብ (ብር) ምንዛሪ ተመን በገበያ (አቅርቦትና ፍላጎት) መሠረት የሚወሰን እንዲሆን አድርጉ በማለት ርዳታና ብድር ፈላጊውን የኢትዮጵያ መንግሥት ጠይቋል፣ ጫና ፈጥሮም ተደራድሯል። ሌሎችም ለህዝብ ያልተገለጡ ቅድመ-ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ። IMF ይህን የታወቀውን ዐይነት ቅድመ-ሁኔታ በደካማ ሀገሮች ላይ የመጫን ፖሊሲውን በማራመዱ የተነሳ፣ አያሌ ሀገሮችን ለከፍተኛ ቀውስ ከዚህ በፊት ዳርጓል። ጠንካራ የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበ ባለ፣የተረጋጋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በሚያደርግ፣ የሰከነ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በሚያራምድ ሀገር ውስጥ ቢደረግ ምናልባት ሀገርንና በተለይም በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደረውን ህዝብ በጣም ሳይጎዳው ኢኮኖሚያዊ ቀውሱ ሊገታ ይችላል። የአገራችን የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ያለው በአስቸጋሪ ሁኔታ ነው። ሀገራችን የመሠረተ-ልማት አውታሮችን የመገንባትም ሆነ የአምራች ተቋማትን የመመስረት ፖሊሲዎች ስርአት ባለው መንገድ ሊተገበሩ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ አይደለችም። ሀገራችን ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች በጠቅላላና ፊሲካል ፖሊሲ በተለይ፣ በጤናማ ሁኔታ ውስጥ አይደሉም። በጦርነቶች፣ በድርቅ፣ በመፈናቀሎች፣ በቀጠናዊ ነውጦች፣ እጅጉን አስቸጋሪ በሆነና የገዥው 2 ፓርቲ ፖሊሲዎችን አካሄድም በጦርነት-መር አስተሳሰብ በተዛባበት ሁኔታ ነው የብርን የውጭ-ምንዛሪ የማንሳፈፍ ርምጃ የተወሰደው።
እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ደካም ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ላይ ለሚገኙ ሀግሮች የገንዘብን የውጭ-የምንዛሪ ተመን (ዋጋን) መቀነስ እንኳን ይጎዳቸዋል፣ እንኳንስ ማንሳፈፉ ቀርቶ። የሚጎዳ ጎኑ የሚያመዝነው ኢትዮጵያ ብዙ ወደ ውጭ የምትልከው በቂ ምርት የላትም። ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች ውስጥ ዋነኛው ቡና ነው። ቡናውን እንኳን ጥሬውን ነው አብዛኛው ወደ ውጭ የሚላከው። ሊኡእሎች ሀገሮች ከኛ በርካሽ የገዙትን ቆልተውና ፈጭተው በማሸግ ብዙ ትርፍ ያካብቱበታል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከሀገር ወደ ውጭ ከምትልካቸው እንደ ሌጦና ቆዳ፣ የስጋ ከብቶች፣ የቅባት እህሎች፣ … ምርታቸው በጦርነቶች፣ በድርቅ፣ በአምራቾቹ መፈናቀል፣ ወ.ዘ.ተ. የተነሳ እጅጉን ቀንሷል።ስለሆነም ከጥሬ ዕቃዎች መላክ የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ እጅጉን ትንሽ ነው። የጸጥታ ሁኔታዎች ሻል ባሉት አካባቭቢዎችም ቢሆን ሀገራችን ውስጥ የቡና ምርቷ በዘመናዊ መንገድ የሚመረት ሳይሆን እንዲያውም ተፈጥሮን ጠብቆ የሚመረት በመሆኑ ምርቱ ከፍና ዝቅ የሚል የግል የአርሶአደሩ ምርት ነው። የቡና ምርት ከሌሎች አምራቾች ከፍ ያለ አቅርቦት ቢኖረው በእርግጥ የብር ዋጋ በዓለም ገበያ መቀነስ የውጭ ነጋዴዎች ዋጋ ስለሚቀንስላቸው ከሌሎች ሀገራት ከመግዛት ይልቅ የኢትዮጵያን የቡና ምርት መውሰዱ አዋጭ ሊሆን በቻለ ነበር። የብር ዋጋ መቀነስ ወደ ውጭ ሊላክ የሚችለው ያለ የሌለ የገበሬውን ምርት አራግፈን ትርፍ አልባ ልውውጥ እንድናደርግ የሚያስገድድ ሁኔታን የሚፈጥር ነው።
ሌላው የብር ዋጋ መቀነስ ለኢትዮጵያ ዓይነቱ ሊጠቅም የሚችለው የዓለምአቀፍ ቱሪስቶችን በመሳብ ይሆን ነበር። በእርግጥም ኢትዮጵያ ቱሪስቶችን የሚስቡ ብዙ ታሪካዊ ቅርሶች፣ ተፈጥሮአዊ መስህቦች አሏት። ሠላም ወደ ጠፋባትና ጸጥታዋም ወደ ተናጋባት ኢትዮጵያ፣ የብር ዋጋ በመቀነሱ፣ ብዙ የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ ጎብኝዎችን ሊመጡ ግን አይችሉም። በዚህ አኳያ መንግሥት ሰላምን አስፍኖ፣ የፖለቲካ ለውጥ አምጥቶ ትኩረቱ ዕድገት ላይ ከመሆኑ ይልቅ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በሚካሄዱ ጦርነቶች ምክንያት እንኳን የውጭ ጎብኝዎችን ለመሳብ ቀርቶ ከተለያዩ ክፍለዓለማት የውጭ ምንዛሪ ይዘው ወደ አገራቸው የሚገቡ ዘመድ ጠያቂ ኢትዮጵያውያንን ሳይቀር ወደ አገር እንዳይገቡ ያስገደደበት ጊዜ ነው። በተመሳሳይ ጦርነት በማይካሄድባቸው አካባቢዎች (አዲስ አበባን ጨምሮ) በአገዛዙ ድጋፍ የሚሰጣቸው ወይም ገዝዎቹ በቸልታ በሚመለከታቸው ወንጀለኞች ዜጎችን አግቶ ከፍተኛ ገንዘብ መጠየቅ እንኳን ከውጭ ወደ አገር የሚገባውን ቀርቶ አገር ውስጥ ያሉ ባለሀብቶች ተንቀሳቅሰው ሥራ እንዳይሠሩ ያደረገ ጉዳይ ሆኗል።
የብር ዋጋን በገበያ እንዲወአሰን ማንሳፈፍ ማለት የኢትዮጵያ ነጋዴዎች ከውጭ ወደ አገር ውስጥ ሊያስገቡ የሚያስችላቸውን የመግዛት አቅም ማዳከም ማለት ነው። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ነጋዴዎች የያዙት ገንዘብ ረክሶ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ከፍ ስለሚል በዓለም ገበያ መገበያያ የሆነውን ዶላር ለመግዛት አቅሙ እያጠራቸው ይሄዳል። አስመጭ ኩባንያዎችም ከዚህ በፊት ማስገባት የሚችሉትን ሁሉ ሳይሆን ቀንሰው ያስገባሉ ማለት ነው። ኩባንያዎቹም ሆኑ ግለሰብ ባለሀብቶች ከውጭ የሚያስገቧቸው ዕቃዎች ከወትሮው ከፍ ባለ ገንዘብ ስለሚገዟቸው አገር ውስጥ ለገበያ ሲያቀርቧቸው ዋጋቸው ከፍተኛ ይሆናል። ይህ ደግሞ ፍላቶትና አቅርቦት (demand and supply) የሚባለውን የገበያ ሕግ ቀውስ ውስጥ ይከተዋል ማለት ነው።
የብር ዋጋ ማሽቆልቆል ከላይ ያሳየነው የውጭ ምንዛሪንም ሆነ ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎችን ዋጋ መናር ከማስከተሉ ባለፈ በአገሪቱ ውስጥ በንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎችን፤ የመንግሥትና የግል ተቀጣሪ ደመወዝተኞችን የሚፈጠረው የገበያ ንረት ዜጎች ለኑኗቸው 3 የሚያስፈልጓቸው ቁሳቁሶችና መገልገያዎች ዕቃዎች እጥረትን ያስከትላል። በገበያ ውስጣዊ ህግ እንዲመራ የሚገደደው ገበያ ሚዛኑን ያጣል፣ የፍጆታና የመገልገያ ዕቃዎች እጥረት በተከሰቱ ቁጥር ዋጋ ማሸቀቡ ደግሞ አይቀሬ ነው። መንግሥት ፊሲካል ፖሊሲን ሳያስተካክልና ከገበያው ጋር ሳያጣጥም ነጋዴውንና አቅራቢውን ማሰር መክሰስና የንግድ ፈቃዱን መንጠቅ ውጤታማ አይደለም።እንዲያውም መንግሥትና ህዝብን ወደ ከፋ ቅራኔና መፋጠጥ ያመጣል።
የብርን ዋጋ መቀነስ የአንድን አገር ገንዘብ የመግዛት አቅም ከረጅሙ ግብ አኳያ ዝቅ ለማድረግ እርምጃዎችን መውሰድን ያካትታል። አገሮች በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ ተወዳዳሪነት ለማግኘትና የዕዳ ሸክሞችን ለመቀነስ እንዲህ ዓይነቱን ስትራቴጂ ሊከተሉ ይችላሉ።ይህ ግን ኢኮኖሚአዊ አቅማቸውን ችግሮቹን ሊሸከሙ ሲያስችላቸው ነው።
ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ሲኖሩት የአንድ ሀገር ገንዘብ የውጭ-ምንዛሪ ተመን መቀነስ የዚያን አገር የውጭ ንግድ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ያደርገዋል፣ በተመሳሳይ ጊዜ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን የበለጠ ውድ ያደርጋቸዋል። ይህ ማለት አሁን ባለችበት ሁኔታ ለኢትዮጵያ የማይሠራ ነው። በዓለም የገንዘብ ድርጅት ግን በበርካታ ሀገሮች ዉስጥ የኤኮኖሚ ርምጃው አድርጎ ይጠቀምበታል። እንደ ኢትዮጵያ ለመሳሰሉ አገራት ብዙ ዕቃ ለዓለም ገበያ የማያቀርቡ፣ በአንፃሩ ከውጭ የሚያስገቡት ከነዳጅ ዘይት ጀምሮ የተለያዩ ቁሳቁሶች ዋጋ ላይ ከባድ ጫና ሊያስከትልባቸውና ወደ ከፋ የኤኮኖሚ ቁልቁለት የሚከታቸው ነው ሊሆን የምችለው።
በአደጉና የንካራ የኢኮኖሚ መደላድል ባላቸው ሀግሮች ውስጥ ቢደረግ ኖሮ፣ የገንዘብ ምንዛሬ ማሽቆልቆል የአገር ውስጥ ኤኮኖሚ እድገትን ሊያበረታታ ይችላል። ምርቶችም ተመጣጣኝ ዋጋ ይኖራቸዋል ምክንያቱም ሸማቾች ከውጭ ከሚገቡ ምርቶች ይልቅ የአገር ውስጥ ምርቶችን ሊመርጡ ይችላሉ። ይህ በንግዱ ላይ የሚኖረው መሻሻል በአጠቃላይ ወደ ዝቅተኛ ሂሳብ ጉድለት (ወይም የበለጠ ሂሳብ ትርፍ)፣ ከፍተኛ የሥራ ስምሪትና ፈጣን የአገር ውስጥ ምርት ዕድገትን ያመጣል። ይህ የሚሆነው ግን ሠላም በሰፈነበት፣ ህዝብ በማረት ተግባር ያለስጋት በሚሰማራበት፣ ማለትም ሰላምና መረጋጋት ባለበት አገርና በይበልጥም የአገር ምርት አቅርቦት ገበያውን ሊያጠግብ ችሎ ሌላ ተወዳዳሪ የአገሩን ምርት ገበያውን እንዳይካፈለው የሚያደርግ ሲሆን ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ፣ የግብርናው ዘርፍ ከሀገሪቱ ኢኮኖሚ ወደ 80% በያዘበት፣ ርሻና ከርሻ ምርት ጋር የተያያዙት ስራዎች ደግሞ እስከ 85% የሚደርሰን የሥራ ዘርፍ በያዙበት፣ የገበሬውም ምርት ለሀገር ፍጆታ እንኳን ሳይበቃ የምግብ እህል እጥረት በተንሰራፋበት፣ አብዛኘው ምርት አሁንም በበሬና በሰው ጉልበት በሚመረትበት አገር የብር ምንዛሬ ቅነሳ ፖሊሲን መከተል እጅግ ጎጂና ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትም ጎታች ነው የሚሆነው። ዛሪ በተለይም ከተማ ውስጥ ኗሪ የሆኑት ሸማቹ አንድ ጊዜ በልተው ለማደር የተቸገሩበት ሁኔታ ነው ያለው።ደሞዝተኞች ሁሉም ተመጣጣኝ የደሞዝ ጭማሪ ስለማያገኙ የመግዛት አቅማቸው እጅጉን ይመናመናል ማለት ነው። በቀን አንዴ መብላትም ሊያቅታቸው ይችላል። በርካታው በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ያለው ህዝብ ጨርሶ የሚላስ የሚቀመስ ሊያጣ የሚችልበት ሁኔታ የሚፈጥር እንዳይሆን ያስፈራል።
ይህ ሊሆን የሚችለው ጦርነቶች ቀጥለው፣ ሀገራችን ሠላም እንደጠፋባት ቀጥላ፣ አምራቹ ህዝብ መተላለቁን እየቀጠለ፣ ሀገራዊ መረጋግት በሌለበት ሁኔታ፣ ለማምረት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን እንደ ማዳበሪያምርጥ ዘሮችን እንዲሁም ሌሎች እንደ ትራክተሮችና ነዳጅ የመግዛት አቅም ይጠፋና፣ ለማምረትም ሆነ ምርቱን ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች እንደዛሬ ቅጥአምባራቸው ጠፍቶ ከቀጠሉ ነው። የነዳጅና የመሳሰሉት ግብዓትፕች ዋጋ እጅግ ስለሚንር ያንን ለማካካስ የሀግር ውስጥ 4 ምርትም ሆነ በተለይም ከውጭ የሚገቡት ምርቶች ዋጋ ላይ የሚያስከትለው የዋጋ ጭማሪ ይህዝቡን በገንዘብ የመግዛት አቅም አለመኖር ያስከትልና በሁሉም ላይ ከፍተኛ ችግር ስለሚፈጠር ነው።
ኢትዮጵያ ሰፊና የዓለም አቀፉ ገበያ የሚፈልገው ቅይጥ የምርት ክምችት የላትም። ወደ ውጭ የምትልካቸው የፋብሪካ ውጤቶች ጨርቃጨርቅና የቆዳ ውጢቶችም ቢሆኑ አነስተኛ ናቸው። አብዛኛው ወደ ውጭ የምትልካች ምርቶቿ ከእርሻ ውጤቶች ጋር የተያያዙ ስለሆኑ በውጭ ገበያ ውድድር ለተመራጭነት የሚበቁ አይደሉም። የቡና ምርቷም ቢሆን ሰፊና ዓለም አቀፍ ገበያን ተቆጣጥሮ በውድድር አቸንፎ የውጭ ምንዛሬ ለማምጣት የሚያስችል ሰፊ ገበያ የለውም። ስለሆነም በአገራችን አሁናዊ ሁኔታ የብር የውጭ ምንዛሬ ቅነሳ እንኳን ይጎዳዋል፣ እንኳንስ የምንዛሬ ተመኑ በገበያ እንዲወሰን መንሳፈፉ ቀርቶ!!
በተጨማሪም ኢትዮጵያ የምታገኘው የውጭ ምንዛሬ ከትውልደ-ኢትዮጵያውያን ከሚላክ ገንዘብ (remittance) እንዲሁም ከቱሪዝም ከሚገኘው ገቢ ነው። ይሁን እንጂ 1ኛ) አገር ውስጥ እየተካሄዱ ባሉ ጦርነቶች ምክንያት ከውጭ የሚላከው ገንዘብ እጅግ የቀነሰበት ወይም የቆመበት ደረጃ ላይ በመደረሱ፣ 2ኛ) ቱሪስቶችን የሚስቡ ጥንታዊ ቅርሶች፣ አብያተ-ክርስቲያናትና ገድማት በአብዛኛው በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ ስለሆነና በአካባቢው ጦርነት እየተካሄደ በመሆኑ ከቱሪዝም ዘፍ የሚገኘውን ገቢ በጣም ጎድቶታል። በአጠቃላይ፦
1. የብር ዋጋ ቅናሽ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ውድ ስለሚያደርገው አጠቃላይ የዋጋ ንረትን ያስከትላል።
2. የብር ዋጋ ማሽቆልቆል የመግዛት አቅምን ስለሚሸረሽር ለነዋሪዎች ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ያስከትላል።
3. የብር ዋጋ ቅነሳ የኢንቨስተሮችን እምነት ሊያዳክም ስለሚችል የካፒታልን ወደ ውጭ መፍለስንና ያስከትላል፣ የውጭ ኢንቨስትመንት ወደ ሀገር የመግባቱን ዕድል እንዲቀንስ ያደርጋል።
4. ተደጋጋሚ የዋጋ ቅነሳዎች ከተከተሉ ደግሞ፣ ኤኮኖሚያዊ አለመረጋጋትና አለመተማመንን ይፈጥራሉ።
5. እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ከፍተኛ የውጭ ዕዳ ባለለባቸው አገሮች፣ የብር ዋጋ ቅነሳ የዕዳቸውን የአገር ውስጥ ምንዛሪ ተመን (ዋጋ) ስለሚያሳድገው የሀገሪቱን የመክፈል አቅም ይቀንሳል፣ የዕዳ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል።
ስለሆነም የብር ምንዛሪ ዋጋ መቀነስ በንድፈ-ሃስዳብ ደረጃ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን የማሳደግና የኤኮኖሚ ዕድገትን የማበረታታት ሁኔታዎችን ሊፈጥር ቢችልም፣ በደካማና ጦርነት እያደቀቀርው ባለው፣ ሥራ-አጥነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ባልበት፣ ሠርቶ ገቢ የሚያገነውን እንኳን የኑሮ ውድነትና የምርት እጥረት ፈተና ላይ በጣለበት፣ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ፣ የባለሃብቶች አመኔታ ማጣትና የዕዳ ጫና መጨመርን የዜጎችን የመግዛት አቅም መንሳት፣ … የመሳሰሉ ጉልህ ጉዳቶችን ስለሚያስከትል የሚያመጣው ጥፋት ከፍተኛ ነው የሚሆነው።የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ በማቃወስ፣ ሀግራችንን ለከፋ ትርምስ ሊዳርግ ይችላል።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያ እና ሕዝቧን ይጠብቅ
ሐምሌ ፴ ቀን ፪ ሺህ ፲፮ ዓ. ም August 5, 2024

