Site icon Dinknesh Ethiopia

የህወሓት ቅጥፈትና እብጠት፣ ለውድቀትና ውርደት

ዴሞክሲያ

አንድ እርምጃ ብቻ ሳይሆን ብዙ እርምጃዎችን በመራመድ የኢትዮጵያ ልጆች የትእቢት ግንቡን አፍርሰዋል፣ ኢትዮጵያን የምንል ሁሉ ተደስተናል፣ ኢትዮጵያም የዓመታት እንባዋ ይታበስ ዘንድ ቀኑ ደርሷል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ታላቅ ገድል ሠርቷል፤ በግንቡ ውስጥ ተሸሽገው የነበሩትን የህወሓትን መሪዎች ለሕግ እስኪያቀርብ ድረስ ግና እረፍት የለውም፡፡

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከተመሠረተበት ከ1968 ዓ.ም. ጀምሮ በፕሮግራሙ ቀርፆ የተነሳው “በኢትዮጵያ ውስጥ የቅራኔዎች ሁሉ እምብርትና አውራው በብሄረሰቦች መካከል ያለው ቅራኔ ነው፣ አማራም የትግራይ ሕዝብና የሌሎች ብሄረሰቦች ጠላት ነው” የሚል ነበር። በዚህ በተሳሳተና በጥላቻ የተሞላ አስተሳሰቡ አገራችንን ለግማሽ ምዕተ-ዓመት ሲያተራምስ ኖሯል።

ድርጅታችን ኢሕአፓ ገና ከጠዋቱ ጀምሮ ይህን የተሳሳተ አስተሳሰብ ከባድ መስዋዕትነትን በመክፈልም ጭምር ሞግቶታል፣ ታግሎታል። ያኔም ሆነ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቅራኔ፣ በአንድ በኩል በመደቦች መካከል ሚዛናዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር፣ የዜጎች የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩና በሕዝብ ሉዓላዊነት ላይ ተመሥርቶ በሚቋቋም ሕዝባዊ መንግሥት የሚያምኑና በሌላ በኩል ደግሞ ሠፊውን ሕዝብ በድህነት አስሮ ማኅበራዊ ፍትኅ የሚነጥቀውን አምባገነናዊ ሥርዓት ማስቀጠል በሚፈልጉ ኃይሎች መካከል የነበረው ተቃርኖ መሆኑን በማስተማር ከፍተኛ ትግል አካሂዷል። ይሁን እንጂ በጥላቻ የተሞላው ህወሓት፣ የኢትዮጵያ ገዥ መደብ አባላት የተለያዩ ብሄረሰቦች ስብጥር መሆኑን ሊገነዘብ የማይፈልግ ቡድን እንደሆነ እስካሁን ዘልቋል፡፡

ሙሉ ዴሞክራሲያን ለማንበብ

 

የኢሕአፓን ፕሮግራም ለማንበብ

Exit mobile version