Site icon Dinknesh Ethiopia

ከኢትዮጵያ ፖለቲካ አስረኞች አንድነት ኮሚቴ ካናዳ


Solidarity Committee for Ethiopian Political Prisoners (SOCEPP-Canada)
የኢትዮጵያ ፖለቲካ እሥረኞች አንድነት ኮሚቴ በካናዳ (ኢፖእአኮ-ካናዳ)
Email: socepp.can@humanrightsethiopia.com and socepp.can@sympatico.ca
Web: www.humanrightsethiopia.com


ጥር 7, 2013 (ጃንዋሪ 15፣ 2021)
ለዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
ባምቢስ ፣ ጆሞ ኬንያታ ጎዳና፣ የመልእክት ሳጥን ቁጥር 1370
አዲሰ አበባ

info@eag.gov.et ስልክ +251 11 551 5099

ክቡር ዶክተር ጌዲዮን
ባለፉት ጥቂት ቀናት ፣ የሀወሀት ከፍተኛ ባለስልጣኖች እነ አቶ ሰብሀት ነጋን ጨምሮ በመንግስት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን በአንክሮ እየተመለክትን ነው፡፡

ሀወሀትና መሪዎቹ በቅርቡ በሀገራችን ሰራዊት ሰሜን እዝ እና በማይካደራ አካሄዱት ከተባለው በማንነት ላይ ያተኮረ ጭፍጭፋ በተጨማሪ ባለፉት 27 አመታት እጅግ ሰፋፊና አስቃቂ የስብአዊ መብት ጥሰት አካሂደዋል። ተቀናቃኞቻቸውን አፍነው ማዳረሻቸውን አጥፍተዋል።

በተደጋጋሚ እንዳሳወቅነው፤ ከነዚህ የሀወሀት ሰለባዎች ውስጥ በብዙ የመብት ተሟጋቾች ሳይቀር ትኩረት ካልተስጣቸው መሀል የኢህአፓ መሪዎችና እና አባላት የሆኑት እነ ጸጋየ ገብረ መድህን፣ ይስሀቅ ደብረጽዮን፣ ሰጦታው ሁሴን በለጠ አምሀ አበርሽ በርታ ሀጎስ በዛብህ፣ ተክላይ ገብረ ሰላሴ፣ ደሳለኝ አምሳሉ፣ ፣ አዛናው ደምሌ፤ ለማ ሀይሌ ተስፋየ ከበደ ፣ ሙሉ አምባው ፣ ወንዱ ሲራክ ደስታ ፣ አበበ አይነኩሉ ሞት ባይኖር፣ ብርሀኑ እጅጉ፣ ድሉ ገበየሁ፣ አባይነህ ሽፈራው፣ ጌታቸው አበበ፣ ጌታቸው ሽፈራው፣ ታምራት ግዛቸው፣ ድንቁ ሽፈራው፣ አዱኛ አደም፣ ዮሴፍ ተሾመና ሊሎችም ፡ ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ክአዲስ አባባ፣ ከባህርዳር፣ ክአርባ ምንጭ አፍነው እንዲሁም ከሱዳን መንግስት ጋር በመተባበረ ከሱዳን ታፈነው እንዲመለሱ ተደረጎ እስካሁን የት እንዳደረሷቸው ያልታወቁት በምሳሌነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ህወሀት እስካሁን ድረስ የ እነዚህን ግለስቦች መዳረሻ ይፋ አላደረገም፣ ወይንም የፈጽሙት ወንጀል ቢኖር ለፈርድ አላቀረበም። እነዚህ ግለስቦች ምናልባትም በሀገራችን ውስጥ መዳረሻቸው ሳይታወቅ ረጅም ጊዜ ከቆዩት የመብት ሰለባወች ውስጥ በዋናነት የሚቆጠሩ ናቸው ብለን እናምናለነ። ሰለዚህ የሀወሀት መሪዎች አሁን በተለያየ የወንጀል ክስ በሀግ ጥላ ስር እየገቡ ሰለሆነ፣ ከላይ የተጠቀሱት ግለስቦችንም የት እንዳደርሱዋቸው አስፈላጊው ምርመራ እንዲደረግና ለሰሩትም ግፍ ተገቢው ሀጋዊ እርምጃ በመውስድ የዘገየም ቢሆን ፍትህ እውን እንዲደረግ አበክረን እንጠይቃለን።

ከታላቅ አክብሮት ጋር

አክሊሉ ወንድአፈረው

የ ኢትዮጵያ ፖለቲካ አስረኞች አንድነት ኮሚቴ ካናዳ ሊቀመንበር

ግልባጭ፣ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት፣ ለፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት, ለኢትዮጰያ ሰባዊ መብት ኮሚሽን፣ ለኢትዮጰያ እርቀ ሰላም ኮሚሽን፣ ለኢሕአፓ


SOCEPP-Canada ደብዳቤ ለጠቅላይ አቃቢ ህግ ጥር2013

Exit mobile version