Site icon Dinknesh Ethiopia

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) 10ኛ መደበኛ ጉባዔውን በተሳከ ሁኔታ አጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)

 

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) 10ኛ መደበኛ ጉባዔውን በተሳከ ሁኔታ አጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዝያ 1 እና 2 ቀን 2014 ዓ. ም በአዲስ አበባ ራስ ሆቴል አዳራሽ 10ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶ በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቋል፡፡

በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት ያካሄደው ጉባዔ አንኳር አንኳር በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችንም አስተላልፏል፡፡ ጉባዔው በፓርቲው ቋሚ ኮሚቴ በኩል የቀረበለትን የድርጅቱን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ አዳምጦ ከመረመረ በኋላ መስተካከል የሚገባቸውን አስተካክሎ የፓርቲው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መመሪያ ሰጥቷል፡፡ ማሻሻያ ተደርጎበት የቀረበውን የሕገ ፓርቲውን ረቂቅ መርምሮና ተጨማሪ ማሻሻያዎችን አድርጎ አፅድቋል፡፡ በመጨረሻም ድርጅቱን ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚመሩትን አባላት በሚስጥራዊ የድምፅ አሰጣጥ ሥርዓት መርጧል፡፡ በዚህም መሠረት የፓርቲውን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን፣ የአባላት መብት አስጠባቂ ኮሚሽን አባላትን፣ የውስጥ ኦዲተሮችንና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል፡፡ የ

ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በመሆን የተመረጡት 1ኛ) ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ ሊቀመንበር፣ 2ኛ) መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር፣ 3ኛ) አቶ ገብረወልድ ወልደሰንበት ም/ሊቀመንበር፣ 4ኛ) ወ/ት ደስታ ጥላሁን ፀሐፊ፣ 5ኛ) ወ/ት ዘነበች ጤናው የፋይናንስና የንብረት ክፍል ሃላፊ፣ 6ኛ) አቶ ሸዋፈራው ሽታሁን የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ እንዲሁም አቶ አንቄቦ ለማጎ፣ አቶ መላከ ካሣና አቶ ጌታነህ ዓለሙ ተጨማሪ አባላት ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ

መነበብ ያለበት

Exit mobile version