Site icon Dinknesh Ethiopia

ኢትዮጵያ – ብሔራዊ የአገር ማዳን ጥሪ

Save Ethiopia Forum

ኢትዮጵያ – የአገር አድን ጥሪ
ክፍል 1

የ63 ዓመቶች የፖለቲካ ጉዞ – ከ1953-2016 ዓም

መግቢያ

ይህ ሰነድ የኢትዮጵያ አስከፊና ህልውናዋንም የሚፈታተን መስቀለኛ መንገድ ላይ መቆሟን ይገልፃል። ይህም ሁኔታ የሚያሳየው እንደ ሉዓላዊ አገር
የመቀጠል፣ ወይም በቅርቡ እንዳየናቸው አገሮች የመፈራረስ፣ ለአካባቢው አገሮችና ለሰፊው ቀጠና የቀውስ ምንጭ መሆን ነው። ያ እንዳይሆን ውድ
ዜጎችዋ በረዥም የታሪክ ሂደት ያካበቱትን እሴቶችና የአብሮነት መንፈስን ይዘው መቀጠል ይጠበቅባቸዋል።

ባለፉት 60 ዓመታት ለፍትህ፣ ለእኩልነትና ለዕድገት የተደረጉት ህዝባዊ ትግሎች በጥቂት አምባገነኖች ተነጥቀዋል። እነኝህም አምባገነኖች ሁሉም የሚጋሩት ጠባያቸው ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ህዝቡን ያካተተ መንግሥት አለማቋቋማቸው፣ በጠመንጃ መተማመናቸውና የመንግሥትን ሀብት ለራሳቸው እያዋሉ የለየላቸው አምባገነኖች መሆናቸው ነው። ይህ ሰነድ ያሳለፍናቸውንና የቅርብ ጊዜ ታሪካችንን እያስጨበጠ ከታሪክ አለመማር የሚያድርሰውን አገራዊ አደጋ ያሳየናል። በዚህ ሰነድ በ1953 ዓ ም አፄ ኃይለ ሥላሴን ከስልጣን ለማውረድ በተደረገው ሙከራ የተጀመረው ሂደት፣
ከዚያ በኋላ በየዘመኑ የተፈጠሩ ዕድሎች፣ በ2011 ዓ ም የተፈጠረውን ጨምሮ፣ እንዴት እንደመከኑና ሀገሪቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ ለአስከፊ ሁኔታ እንደዳረጉና ሕዝቡን ለከፍተኛ መከራ እየማገዱ እንደሄዱ ከእነማስረጃው ቀርቧል ።

በቅርብ ከሥልጣን የተወገደው በህዋህት የሚመራው የኢህአደግ አንድና በኦሮሙማ የሚመራው የኢህአድግ ሁለት ብልፅግና ካለፉት መንግሥታት የተለዩ ናቸው። የሚያምሳስላቸው እንደአለፉት መንግሥታት ሁሉ አቃፊ መንግሥት ያልመሠረቱ፣ በጉልበት የሚመኩና በተለይ የአገሪቱን ኃብት እንዳሻቸው ለግል ጥቅም ያዋሉ መሆናቸው ነው። ከበፊቶቹ የሚለዩበት ግን ኢትዮጵያን ለዘመናት የሚክፋፍል የዘውግ ሥርዓት መሥርተው በሥራም ላይ ማዋላቸው ነው። ይህም ከዓለም አገሮች ሁሉ የተለየና ኢትዮጵያን ወደ መበታተንና ሕዝቧን እርስ በርስ ወደሚያፋጅ ጎዳና የሚወስድ ነው።

 

ሙሉ ሠነዱን ለማንበብ

Exit mobile version