Site icon Dinknesh Ethiopia

ከኢትዮጵያ  ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የተሰጠ መግለጫ

EPRP

አገራዊ ምክክር ውጤታማ የሚሆነው አካታች ሲሆንና ሂደቱም ነፃና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ ውሳኔዎቹን ለመተግበር አስቻይ ሁኔታዎች ሲኖሩ ነው!

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከአንድ ቀውስ ወደ ሌላ ቀውስ እየገባች፤ የጋራ እሴቶቻችን፤ ሀገራዊ ራዕያችንና ለዘመናት ሕዝባችን አጋምደው ያኖሩን ትስ ስሮቻችን እየተሽረሽሩ ሄደው ሊጠገኑ ወደማይችሉበት ድረጃ የተደረሰበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። በሕገ መንግሥቱ፡ በክልሎች አወቃቀር፡ በሀገር መንግሥት ምሥረታ … ወዘተ ላይ ያለው አመለካከት ሰፊና ተፃራሪ ነው። በሀገራዊ ተቋሞቻችን፡ በሰንደቅ ዓላማና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የጋራ ዕይታችን እየተራራቅ ከመጣ ውሎ አድርሯል።

ሀገራችንን እንደ ሀገር በማስቀጠል ላይ የአመለካከት ልዩነቶች ከስተዋላቸው በተጨማሪ በጋራ ታሪካች ላይም ሰፊ አለመግባባት ይታያል። ከሁለት ዓመታት በፊት በህወሓትና በብልጽግና መካከል የተቀሰቀሰው የፖለቲካ ቀውስ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ የአንድ ሚሊዮን ወገኖቻችንን ሕይወት ወደቀጠፈው ጦርነት እንደተሸጋገረ ይታወሳል። ጦርነቱ የብዙ ብሊዮን ብር የኢኮኖሚ ኪሳራም አድርሷል። ይህ አልበቃ ብሎ አገራችን ዛሬም በኦሮሚያ፤ በቤኒሳንጉል፤ በአማራ፤ በጋምቤላ እና በሌሎችም አካባቢዎች በጦርነት ውስጥ ትግኛለች። ስለዚህ ከአውዳሚ የርስ-በርስ ጦርነት አዚሪት ውስጥ መውጣት ለኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ ሳይሆን የግድ በመሆኑ ይህን ሊያሳካ የሚችል ውይይት፤ ድርድርም ሆነ ምክክር ተድርጎ ብሄራው መግባባት መገኘቱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑም ኢሕአፓ አጥብቆ ያምናል።

 

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Exit mobile version