የራያ ወንድሞቻቸውን የፍርድ ሁኔታ ለመከታተል ወደ መቀሌ የሄዱት የራያ ተወላጆች ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው ሲሆን በዚህ ሰዓት የጊደይ ዋዕሮ እህት የሆነችው አወጣሽ ክንፈ “ፎቶ እያነሳሽ ለራያ ኮሚቴ የምትልኪው አንች ነሽ” በሚል የሃሰት ክስ በመቀሌ አስረዋታል።
= ወንድማችን ሙለታ ዳግም ለህዳር 10 ተቀጥሯል። በጣም የሚገርመው ምስክሮች የተገኙ ቢሆንም ምስክሮች አልተገኙም በሚል የጥድፊያ ሻጥር ከ34 ቀናት በኋላ ይቅረብ ብሎ ችሎቱ ወስኗል።
= በተመሳሳይ በማንነታቸው ብቻ ታፍነው ያለ ፍትህ እየተሰቃዩ ያሉት እነ ሃይሉ በለጠ ፣ ጊደይ ዋዕሮ ፣ ዳርጌ ከበደ ፣ ብርሃኑ በላይ እና ሌሎች ወንድሞቻችን ዛሬ ከሰዓት በመቀሌ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።
ትህነግ ስለ ህገመንግስት የሚጮኸው ፣ በመግለጫው ሌሎቹን ፓርቲዎች እና የፌደራሉን መንግስት የሚከሰው ፣ የኔ ክልል ሰላም ነው እያለ የሚለፍፈው ምን ያህል ሃሰት እንደሆነ ለማረጋገጥ በራያ ተወላጆች ላይ እየፈፀመ ያለውን ግፍ እና ሰቆቃ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ብልሹ የፍትህ ሂደትን ማየት ብቻ በቂ ነው።