ታጠቅ መንጂ ፤ 23 ኦክተበር 2019
-መደመር እነማንን እንደሚመለከት የሚጦቁመውና ያለቅድመ ሁኔታ ዝም ብለን አንደመር የሚል መልዕክት ያለው ጽሁፌ ፤ለሁለተኛ ግዜ ለአደባባይ
በዚህ በድህረ ህድሳት(ፖስት ሞደርን) ዘመን የምንበላቸው፣የምንጠጣ ቸው ፣የምንለብሳቸው፣ የምናጌጥባቸው ወዘተርፈ ነገሮች ሁሉ መሰረታቸ ወን ለቀው (ጅኒትቲካሊ ሞዲፋይድ፣ ኮሞዲፋይድ፣ፋሽኒፋይድ፣ ኮስሚ ፋይድ …) ሁነውና በቀለማ ቀለማት ተሸፈነው ገበያ እንደሚወጡ ሁሉ፣ ‘እውነቱን ውሸት ፣ እውሸቱን እውነት በማለት እኛ በንፈልገውና ለእኛ በሚመቸን አመኔታ የምንገልጽበት፣የምናስተምርበትና የምንጽፍበት ዘመን ነው።ጥምዝ ወይም ማኑፕሌቲቭ አስተምሮት ወይም ዲስኮርስ ይባላል።
ጠቅላይ ምኒስተር አብይ አህመድ እርሳቸው በሚፈልጉት ትርጉምና እይታ ‘በእንደመር’ አስተምሮት/ዲስኮርስ ፤ ሶሞኑ መጽሃፍ አስመርቀው ለሸማ ች ገበያ አውጥቷል።
እኔ ‘ለዕንደመር’ ያለኝን ትርጉም የሚገልጽ ትንሽ ጽሁፍ ባለፈው ዓመት እ.ኤ.አ በዚሁ ወር ከታች ለጽሁፉ በሰጠሁት አርእስትና ቀን ለአንባቢያን አጋርቼአለሁ። ይህ የእኔ የዕንደመር ስሪት/ቭርሽን የሚያሳይ ትንሽ ጽሁፍ ያላነበቡት እንዲያነቡት ፣ ያነበቡትም ደግሞ እንዲያነቡት በማሰብ በድጋ ሚ አደባባይ እንዲወጣ ስለፈለኩ እነሆ ተጋሩኝ ።
ምነው በዕንደመር ላይ ፀሐፊዮች በዙ! እኔም አለሁበት!
ታጠቅ መንጂ ፤ 18 ኦክቶበር 2018
‘የዕንደመር’ ቃል፦ዘቤያዊ፣አርማዊ፣ ምልክታዊ፣ተምሳሌታዊ ወዘተርፈ ነው ። በእንግሊዝኛ <ሜታፎር ወይም ሜታፍሪካል> የሚል ትርጉም ያለው ይመስለኛል ።
የዕንደመር ቃል -ማኅበራዊ አብሮነት ሶሻል ኢንክሉዥን(Social Inclusion) ከተሰኘ ጽንሰ ሃሳብ – ከማኅበራዊ ሳይንስ የተወሰድ ወይም ከዚያ ጋር የተዛ መ ሊሆን ይችላል ።
የቅድመ ኅድሳትና የዘመነ ኅድሳት ጥናት ሊሂቃን በእነዚያ ዘመናት ፥ የፖለቲከኞችን ንግግር፣የአደባባይ ስዎችን ዲስኩር ፣የፀሃፊዮችን መጽሃፍ፣ የሳዓሊዮችን፣ የተዋኒያን (የኪነጥበብ)ሰዎችን ወዘ…ሥራዎች በቅጡ ሳይተቹና ሳይፈተሹ በሕዝብ አእምሮ ይሰረጹ ነበር ፤ የሚተቹና አቃቂር የሚያወጡ ቢኖሩም በጣም ጥቂቶች ነበሩ ይላሉ ።
ጠ/ምኒስተር አብይ ይህ አምስት ሆሄያት የያዘ ቃል በአደባባይ ንግግራቸው ጣልቃ አስገብተው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ካስደመጡት በግምት ከአምስ እስከ ስድስት ወራት ይሆናል።ያንን ንግግር ካደረጉበት ሰዓት ጀምሮ የበርካታ የሃሳቡን ደጋፊና ተቃዋሚ ፀሃፊዮች ቀልብ ሳበ፤የመጻፊያ መድረክ ፈጠረ።
በኢንዱስትሪ፣በቴክኖሎጂ፣በኮምኒኬሽን፣ በኢኮኖሚ ወዘተርፈ እድገት ላቅ ባሉ አገሮች ሕዝቦች አሰያየም ፤አሁን ያለንበት ዘመን ድኅረ-ህድሳት (postmodern) ይባላል።ለምን ድኅረ ህድሳት እንደተባለ የማያቁ ካሉ ወደፊት ራሱን በቻለ ጽሁፍ እገልጸዋለሁ።
የድኅረ-ህድሳት ጥናት ሊሂቃን -የሉል/ግሎባል ማኅበረሰብ ንቃተ-ኅሊና ስላደገ/ከ ስላለ በዚኅ ዘመን በያንዳንዱ በግል ፣በጥንድና በቡድን (በሚነ ሱ ፣በሚሰነዘሩ ፣በሚወረወሩ ቃል/ቃላት፣በሚደረጉ ንግግሮች/ ዲስኩሮች ፣በሚጻፉ ጽሁፎች፣በሚሳሉ ሥዕሎች፣በሚተወኑ ትወናዎች፣በሚለበሱ ፋሽኖች) ወዘተርፈ ላይ (የመተቸት ፣የመገምገም ፣የመሰንጠቅ ፣የመጠን ጠን ፣የመቀጥቀጥ፣የመፈጥፈጥ) ወዘተርፈ ፈተናዎች አሉባቸው ይላሉ ። ለምን ?ስለምን?በምን ምክንያት?እንዴት ? መቼ? ከየት? ወዘተርፈ ብሎ የሚጠይቅ ማኅበረሰብ ተፈጥሮዋል ይላሉ ።
ስለሆነም ነው ‘በዕንደመር’ ላይ የዕንደመርን ቃል ካዋቀሩት ሆሄያት የበዙ ሰንጥቅጥቅ ታይታዎችን የተፈጠሩት ። ጠ/ሚኒስተር አብይ ‘ዕንደመርን’ የወረወሩት ይህንን ሳይረዱ ይሆን?
ዕንደመር፦
1. ከመሰረታዊ የሂሳብ ሚናውን ወጣ ብሎ የኢትዮጵያውያን የሰላምታ መግበያ ቋንቋ ይሆናል
2. የኢትዮጵያውያን ፖለቲካዊ ፦ ቧልት፣ምፀት፣ቀልድ፣ትወና ይሆናል/ይፈጥራል 3. (ግራ፣ቀኝ ፣ማሃል ግራ፣ማሃል ቀኝ) ዘመም ዕርዮት ያላቸው ፀሃፊዮች-ያከራክራል ፣ ያፋትጋል፣ ያፋጫል፣ የሃሳብ የብዕርና የወረቀት አቧራ ያስነሳል
4.ኢትዮጵያውያን የዕንደመርን ፦ባህላዊ፣ ታርካዊ ፣ቋንቋዊ ፣ብሄረሰባዊ …ፋይዳ ምንድነው? በማለት በየ-የኢትዮጵያ ኤምባሲዮች ተሰባስብው የሚያከራር አጀንዳ ወዘተርፈ ይሆናል ብሎ በማሰብና በማስላት ይሆን ‘ዕንደመርን’ የወረወሩት? ወይስ በግብታዊነት?
የማሃል ግራዎችና የማሃል ቀኝ ዘመሞችን የክርክር ቅኝት ለግዜው ትቼ የግራና የቀኝ ዘመም አስተሳሰብ ካላቸው ተክራካሪዮች የሚሉትን ከሁለቱም አንዳንድ ለናሙና እነሆ፤
ሀ) የቀኝ ዘመሞች ክርክር ፦ ዕንደመር ፍቅር ነው ፣ዕንደመር ብዝህ ነው፣ ዕንደመር አብሮነት ነው፣ ዕንደመር የተፈጥሮ ህግ ነው <መዋለድ> ነው ፣ ስለሆነም ያለገደብ ያለአጥር ፣ያለጥያቄ ፣ያለቅድመ ሁኔታ መደመር ያስፈል ጋል ይላሉ
ለ) የግራ ዘመሞች ክርክር (ሃቅ ፈላጊዮች)፦ለመደመር ቅድመ-ሁኔታዎች መኖር አልባቸው ፣ መደመር በገደብ ፣ እንዴት ቂጥኝ ፣ኤድስ፣ የሳምባ ፣የአባለዘር ወዘተርፈ በሽተኞች ታክመው ሳይፈወሱ ከሰፊው ሕዝብ ጋር ይቀላቀላሉ ይላሉ ። በሌላ አነጋገር ወንጀለኞች፣ ፀረ-ሕዝቦች፣ፀረ-አገረኞች ግፈኞች፣ ዘራፊዮች ወዘተርፈ ለፈፀሙት ጥፋት ተጠያቂ መሆን አለባቸው! ለሕግ ይቅረቡ! ፍትህ ይሰጥ! ፍትህ አልባ ይቅርታ ቀልድ ነው! ስለሆነም ዕንደመር በገድብ መሆን አለበት ይላሉ ።
የዕንደመር፣ተደመሩ ትርጉም በእኔ ታይታ
የዕንደመር ተደመሩ መልዕክት ኢትዮጵያውያን የተሳሳተ ትርጉም ሰጥተው ሲጠቀሙበት እሰማለሁ ።ጥሪው ለኢትዮጵያ አውደ ሕብና ከአውደ ሕዝባ ቸው ጎን ተሰልፈው ለታገሉትና መሰዋዕትነት ለከፈሉት አይደለም ።እው ነተኛ ጥሪው እንደሚከተለው ነው።
• ከወያኔ/ህወሃት ጋር ተሰልፈው፦አገር ላስገነጠሉ፣የባህር በሮቻችን ላስወሰዱ፣በጎሳ ቋንቋ ሕዝብ ላካለሉ/ላጠሩ፣አንድ ጎሳ በሌላ ጎሳ ላይ ላዘመቱ፣ ለገደሉ/ላስገደሉ፣ ለገረፉ/ላስገረፉ፣ ላሰሩ/ላሳሰሩ፣የእምነትና የሃይማንት ድርጅቶችን የከፋፈሉ፣የኢትዮጵያ ታርክ የመቶ ዓመት ታርክ ነው ብለው ላስተማሩ/ለሰበኩ፣ ባንድራችን ጨርቅ ነው ብለው ለፈረጁ ወዘተርፈ ፤
• በባዕዳን አገራት ቤተክርስቲያናትን፣መስጊዶችን ፣ምዕምናንን፣ ኮምኒቲዮችን ፣የስፖርት ተቋማትን ወዘተርፈ በመከፋፈል የወያኔ ተልዕኮ ላስፈጸሙ በሰፊዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተሸንፈናልና ኑ ወደ አወደ ሕዝቡ ተደመሩ፣ እንደመር ማለታቸው ነው ፤ማለት ጠ/ምኒስተር አቢንም ጨምሮ ።
• ተደመሩ፦ ከደርግ ጋር ተሰልፋችሁ -የአንድ ትውልድ ወጣት የመተ ራችሁ ፣አገር ምሁር አልባ ያደረጋችሁ፣ወላጅ ልጅ አልባ ያደረጋች፣ ገድላችሁ እሬሳ የሽጣችሁ ፣በብዙ ሺዎች ላይ ሰቆቃ የፈፀማችሁ፣ ብዙ ሺዎች ዘር አልባ ያደረጋችሁ፣የብዙ ሺዎችን አካለ ያጎደላችሁ፣ ብዙ ሺዎች በረንዳ አዳሪ ያደረጋችሁ፣ ብዙ ሺዎች የአእምሮ በሽተኛ ያደረጋችሁ፣ሽማ ግሌዎች ፣አሮጊቶች፣አዛውንቶችና አረጋውያን ያሰቃያችሁ ፣የገረፋችሁ ፣ያዋረዳችሁ፣ የገደላችሁ፣ የማኅበረሰቡን ሕይወት ያመሰቃቀላችሁ ፣የማኅበረሰቡን ቅስምና ስነ-ልቦና ያዘቀጣችሁ፣ያንኮታኮችሁ ፤
• ምርጥ ወታደራዊ መኮንኖችን በመመንጠርና በመጨፍጨፍ ኢትዮጵያ ኤርትራን ፣አሰብና ምጽዋን እንድታጣ አስተዋጾ ያደረጋችሁ ወዘተርፈ ፀር-ሕዝብና ፀረ-አገር ደርጎችና የደርግ ካድሬዎች ኑ ወደ ሰፊው ሕዝብ ተደመሩ፤ ሕዝብ ሃያልና አሸናፊ ስለሆነ ተሸንፈናል ስለሆነም ለሰፊው ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንበርከክ ፤ተምበርከኩ ማለታቸው ነው ።
ያለገደብ መደመር ወይስ በገደብ ?ጥያቄ ላይ የእኔ አቋም
• በየትኛውም አገር በአእምሮ ጤና የታወኩ የማኅበረሰቡ አባላት-በዜጎች ላይ አድጋ እንዳያደርሱ ከሰፊው ሕዝብ ተነጥሎና እርቀው እንዲቀመጡ ይደረጋል ወይም በቤተሰብ ቁጥጥር ሥር ይውላሉ
• በኢኮኖሚና በሁለ-ገብ ዘመናዊ ሥልጣኔ አደጉ የምንላቸው እንደ አሜሪካና እንግሊዝ የመሳሰሉ አገራት ወይም መንግሥታት ለውጌያ ወደ ቬትናም፣ ካምቦዲያ፣ ላዎስ፣ ኢራቅ፣ አፍጋኒስታን ወዘተርፈ የላክዋቸው ወታደሮቻቸው ወደ አገራቸው ሲመለሱ በቀጥታ ከአውደ ሲቪሉ ሕዝብ ጋር አይቀላቀሉም ።ምክንያቱም የጦርነቱ ቴያትር ቁጡ፣ጠበኛ፣ብስጩ፣ አመጸኛ ወዘተርፈ ስለሚያደርጋቸው በሕዝብ ላይ አደጋ ያደርሳሉ ተብሎ ስለሚታመንና ሃኪማዊ ጭብጥ ነትም ስላለው። ስለሆነም ከሰፈው ሕዝብ አርቀው ያስቀምጥዋቸውና የአእምሮ ህክምናና ዋግምት/ትራፒ ከሰጥዋቸው በኋላ ከሕዝብ ጋር ተቀላቅለው መኖር ይጀምራሉ።
• በኢኮኖሚና በሁለ-ገብ ዘመናዊ ሥልጣኔ በተጎናጸፉ ምዕራባዊያን ሃገራት እንዲታደኑ በህግ ከተደነገጉ- የዱርና የሜዳ እንስሳት ውጭ ህግ ጥሶ/ተላልፎ እንስሳ/ትን የገደለም ሆነ ያቆሰለ በእስር ወይም በገንዘብ ይቀጣል ። ከመብዛታቸው የተነሳ በአካባቢ የተፈጥሮ ሃብት ላይ ጥፋት ያስከትላሉ ተብለው የተፈረጁትን እንስሳት ለስፖርት ኤላ ማ መለማመጃና ለመዘናኛ የሚታደኑ ተብለው ይፈረጃሉ (animals can be hunted for sport and recreation)
• የዲሞክራሲ እምብርት እንደሆነ በሚነገረለት አሜሪካ አንድ ሰው – ሰው መግደሉን በማስረጃ ከተድርሰበት ፤ሟቹና ገዳዩ እንደሚኖሩበት ክ/ሃ ወይም እስቴት በሞት ወይም በዕድሜ ይፍታህ እሥር ይቀጣል
• የአሜሪካ መንግሥት አንድ ሰው ወይም ቡድን በኅብረ-አሜሪካም ሆን በአንዱ የአሚሪካ ግዛት ላይ ክህደት የፈፀመ/ምች መሆኑን/መሆ ኗን በማስረጃ ከተረጋገጠባቸው በግዲያ ይቀጣሉ ።የሚከተለውን የእንግሊዝኛ ትርጉም ተመልከቱ፦
Treason laws in the United States
In the United States, there are both federal and state laws prohibiting treason.[1] It was defined in Article III, Section 3 of the United States Constitution. Most state constitutions include similar definitions of treason, specifically limited to levying war against the state, “adhering to the enemies” of the state, or aiding the enemies of the state, and requiring two witnesses or a confession in open court.[2] However, fewer than thirty people have ever been charged with treason under these laws.[3]
Constitutionally, citizens of the United States owe allegiance to at least two sovereigns. One is the United States, and the other is their state. They can therefore potentially commit treason against either, or against both.[4] At least fourteen people have been charged with treason against various states; at least six were convicted, five of whom were executed. However, no person has ever been executed for treason against the federal government [www.wikipedia,free encyclopedia]
በእኔ አስቦት ፤መሆን ያለበት ወይም ቅድመ መፍትሄ ዎች
አለባብሶ ቢያርሱ በአረም ይመለሱ ዓይነት እንዳይሆን፤ ለመደመር ገደብ ይበጅለት እላለሁ ። ለመደመር የብሄራዊ እርቅና ሰላም ኮሚሽን መሰየም ያስፈልጋል ። የማኅበራዊ እርቅ ኮሚሽን ኮሚቴ አባላት ከማኅበረሰቡና ከተለያዩ ለአገርና ለሕዝብ ከቆሙ ድርጅቶች የተውጣጡ እንጂ የኢህ አድግ ወኪል መሆን የለባቸውም። ከበርካታ ወደ መደመር ከሚወስዱን መሥፈርቶች ወይም መንገዶች አንዱ የሚከተሉትን መልክ ቢዝ ወይም ቢሆን ፥
1.አንድ ሰው በሃሜት ወይም በጥርጣሪ ወንጀለኛ ስለማይባል ፤ተጠርጣሪ ዮቹ የብሄራዊ እርቅ ኮሚሽን አምኖ በመረጣቸው በወንጀል መርማሪ ሞያተኛ ቡድን ማስመርመርና ማጣራት
2. ወንጀሉን/ሎችን የተፈጸመው/ሙት አእምሮ በመታወክ ወይም በሥልጣን መከታ መሆኑንን ማጣራት
3. በሥልጣን መከታ የተፈጸሙትን ወንጀሎች በ [1ኛ፣2ኛ፣3ኛ …]በሚል በደረጃ ማስቀመጥ
4.የሰዎቹ ስም ፈጸሙት ከተባሉት ወንጀል ዝርዝር ጋር ለብሄራዊ እርቅ ኮሚሽን ማቅረብ
5.የብሄራዊ ዕርቅ ኮሚሽን ወንጀሉ የተፈጸመው በአእምሮ በሽታ ምክንያት ነው የተባለውን/ባሉትን ወደ እውቅ የአእምሮ ህመም ሊሂቃን መምራት ና እነሱ የሚሰጡትን የምርመራ ውጤት ተመርኩዞ ለውሳኔ መድረስ
6.የብሄራዊ ዕርቅ ኮሚሽን ከመካከለኛ እስክ ትላልቅ ወንጀል/ሎች የፈጸሙትን ወደ ፍትህ/ዳኝነት አካል መምራት/መላክ
7.ትናንሽ ወንጀል የፈጸሙትን ለሰፊው የኢት/ ሕዝብ ተገልጾና ተነጋግሮ፣ አጥፊዮችም ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅር እንዲላቸው ተማጽነው ፤ ለብሄራዊ ዕርቅና ስላም ሲባል ከሕዝብ ጋር እየተመካከረ ምህረት ማድረግ
ዝምብላችሁ ተደመሩ፣ዝም ብለን እንደመር ሲባል ፦
1) አገር ማስገንጠል ፣የብሄራዊ ባህር በር ማስነጠቅ ፣ብሄራዊ አንድነት ማናጋት ፣ሕዝባዊ አንድነት መሸርሸር፣ማፈናቀል፣የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ ፣ በአጠቃላይ በዜጎችና በአገር ሉዓላዊነት ላይ ከፍተኛ ደባና ክህደት መፈጸም ወዘተ..ምንም ዓይነት ዋጋ ላያስክፍል ነውን?
2) 300,000 – 500,000 በሚደርሱ የቅይ ሽብር ተጠቂ ቤተሰቦች ፥ ሃዘን ፣ ቁስል ፣ህመም ፣ኅዋስ ፣አጥንት፣ ነፍስ/ሶል ፣ሥነ-ልቦና ወዘተ..ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ ማጋየት አይሆንምን?
በዜጎች ላይ ሰቆቃ መፈጸም ፣ ማስቃየት፣ዘርአልባ ማድረግ፣ አካለ ስንኩል ማድረግ፣ መግደል ፣ አስክሬን መሸጥ ወዘተርፈ እንደ መዝናኛ እስፖርት መቁጠር አይሆንምን? ዊኒ ማንዴላ ለአፓርታይድ ፖሊሶች ሚስጥር ያቀብላል በማለት አንድ ልጅ በማስገደሏ የገጠማትን ማኅበራዊ ተጽኖና ውግዘት ሰምተናል።
3) 70% ቱ ሕዝብ ፍጹም/አብሶልት ደሃ ከሆነበት ኢትዮጵያ 30,000,000,000 (ሰላሳ ብሊዮን) ዶላር በኢህ አድግ በተለይም በህወሃት ባለሥልጣናት ተዘርፎ በባዕዳን አገራት ባንኮች ማስቀመጥ እስዮ በርቱ ማለት አይሆንምን?
4) የኢትዮጵያ ህዝብ ሥርዓትና ሕግአልባ እንዲሆን፤ ያራዊት ሥርዓት እንዲከተል አይጋብዝምን?
5) ማኅበረሰባችን ኢ-ግብረገባዊ ፣ኢ-ኅሊናዊ ፣ኢ-ሰአባዊ ወዘተ..ባህልች እንዲከተል፣እንዲያዳብር አይጋብዝምን? በአጭሩ -በአገራዊና በሕዝባዊ ሉዓላዊነት ላይ ክኅደት የፈፀሙ፣ ንቃተ-ሊናው ከፍ ያለውን- ቢያንስ የሁለት ትውልድ ማኅበረሰብ አባላት እንድ አረም የመነጠሩ፣ የመተሩ፣ሬሳ የሸጡ፣ አገር ያስገነጠሉ፣ዳርድንበር ያስደፈ ሩ፣ የባር በር ያሳጠሩ/ያስወረሱ፣ ሃብት ንብረት የዘረፉ ውዘተርፈ የጥፋት ሃይሎች ያለ አንዳች ቅጣት (retribution) ከሰፊው ሕዝብ ጋር ተደባልቃ ችሁ ኑሩ ማለት፤ ለነገው ትውልድ የሚሰጠው ትምህርትና መልዕክት ምንድ ነው ? ?
ጠ/ምኒስተር አብይ በሚመሩት ሥርዓት ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ፣ ታማኝ እንጂ ተጠርጣሪ፣እድገት እንጂ ተኮርኳሚ፣ተሿሚ እንጂ ተሻሪ፣ተወዳ እንጂ ተጠይ ወዘተ..አልነበሩም። ስለሆነም ‘እንደመር’ የሥልጣን አጋሮቻቸውን – ላለማስቀየም፣ ላለማስከሰስና ከመወንጀል ነጻ ለማድ ረግ ያመጡት ፈልጥ ነው ብዬ እግመታለሁ ።