Site icon Dinknesh Ethiopia

ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ፣ – የኢዲኤፍ ወቅታዊ መግለጫ

እስከመቼ

እስከመቼ?

እስከመቼ ኢትዮጵያና ህዝባችን ለግል ዝናና ለስልጣናቸው ሲሉ ግለሰቦችና ቡድኖች በሚወስዱት የህዝብን ፍላጎት ያልጠበቀ እርምጃና ትርክት ስንንገላታና ስንጨነቅ፣ ስንፈናቀልና ስንሰደድ፣ ስንራብና ስንገደል እንኖራለን?

እስከመቼስ ህዝባችንን እንመራለን፣ እናስተዳድራለን ብለው ስልጣን በጨበጡና ለስልጣን በሚያንጋጥጡ ግን  በተግባራቸው  ለአንድነታችን፣ ለታሪካችንና ለቀጣይነታችን  ደንታቢስና ደካማ በሆኑ የመንግስትና የፓርቲ ተብዬ መሪዎች እንንገላታለን? ከነሱና ከነርሱ ብቻ መፍትሄስ እስከመቼ እንጠብቃለን?

እስከመቼ ድረስ ለራሳችን መቆም ተስኖን በራስ መተማመናችን መንምኖ ከውጪ አገር፣ አሜሪካ፣ አውሮፓ ወዘተ… መሪዎች ስለአገራችንና ስለውስጥ ጉዳያችን መፍትሄ እንጠብቃለን?

መቼ ነው በታላቅነታችን፣ የሰው ልጅ መገኛ የስልጣኔና የመንግስት አካልነት መጀመርያ፣ የታላላቅና ድንቅ ቅርሳቅርሶች፣ ኪነጥበብና ፍልስፍናዎች መፍለቂያ፣ የአንጋፋና ታላላቅ ሃይማኖቶች መናሀርያ፣ የአድዋ ድል ባለገድል፣ የጀግኖች አገር ተምሳሌት፣ ለሰው ልጆች ህይወት መልካም የሆነ የአየር ጸባይ ባለቤት፣ በትህትናችንና በአብሮነታችን የምንወደስ የብዙ ቋንቋ ባህልና ዜማ ህብር ፣ በቅዱሳን መጻህፍት ስሟ በተደጋጋሚ የተወሳ በፈጣሪ አምላክ ፍቃድ የቆመች፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየደመቀ፣ እየፈካ፣ እየጎለበተ በሚሄድ አብሮነት፣ በአረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለም ሰንደቅ አላማ የተሳሰርን አንድ ህዝብ መሆናችንን ተረድተንና አምነን እጅ ለእጅና ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፈን የምንቆመው መቼ ነው? እስከመቼስ ባልፈቀድነውና ባላወቅነው መለያየት ወደ እርስ በእርስ ግጭትና ወደ ጠቅላላ ጥፋት እሚያስገባን፣ የጎሳ ፖሊቲከኞች በሚያራምዱት ጽንፈኛ ዘር ተኮር ፖሊቲካ የምንመራውና የምንታመሰው? እኮ እስከ መቼ ? የኢትዮጵያውያን የመወያያና የመፍትሄ መድረክ (Ethiopian Dialogue Forum – EDF) ከላይ የሰፈሩትን ማመዛዘኛ ፍሬ ሃሳቦች ላይ ትውልዱ፦ ምሁራን፣ አክቲቪስቶች፣ የፖሊቲካና የህዝባዊ ድርጅቶች፣ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊን ወዘተ… እንዲነጋገሩበት ይጠይቃል።

ይህ እንዳለ ሆኖ፣ በተለይም በአዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች  ከሰሞኑ ሃላፊነት በማይሰማቸው፣ ጎሰኝነትንና የክልል ማንነትን በአክራሪነት በሚያራምዱ ጽንፈኞች፣ በገሃድም ሆነ ከበስተጀርባ ሆነው በሚመሳጠሩ ተከታዮቻቸውና እኩይ ተልዕኮ አቀናባባሪዎች አማካይነትና አዝማችነት ከ50 የማያንሱ ወገኖቻችን ላይ ለደረሰው ህልፈተ ህይወት የኢዲኤፍ (EDF) አመራርና አባሎች የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንገልጻለን። ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጆቻቸው ሁሉ መጽናናትን እንለምናለን።

በተከሰተው የሰላም ማጣትና እልቂት ለተሸበረውና ለተደናገጠው ለኢትዮጵያ ህዝብና ወዳጆች መረጋጋትን እንመኛለን!!

ግን እስከመቼ?

ስለሆነም:- መንግስት በህዝባችን ላይ ጽንፈኛ የዘር ፖለቲከኞች በወሰዱት ጸረ ህዝብ ህይወት የማጥፋትና ንብረት የማውደም እኩይ ተግባር የተሳተፉ፣ ያቀነባበሩና የመሩ ግለሰብም ሆነ ቡድኖች ላይ በአስቸኳይ የማጣራት ስራ በማድረግ ለፍርድ እንዲያቀርባቸው እናሳስባለን።

በኢትዮጵያ ህዝብና በአገራችን ልኡላዊነት ላይ በተደጋጋሚ ሴራ መሸረቡንና ጥቃት እየደረሰብን እንደሆነ ግልጽ ነው። ህዝብ መንግስትን የሚፈልገው ከሁሉም በላይ ሰላሙንና አገሩን እንዲያስጠብቅለት እንጂ ግለሰቦችን ደመወዝ እየከፈለ በስልጣን ላይ ተንደላቀው እንዲኖሩ አይደለም። መንግስት አገልጋይ እንጂ ተገልጋይ ሊሆን አይገባም። ለደረሰው እልቂትና ውድመት ተጠያቂዎችን በመልቀም ለፍርድ አሳልፎ የመስጠት ግዴታ በመንግስት ትከሻ ላይ የወደቀ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን። በቸልተኝነትም ሆነ በማድበስበስ የዜጋዎችን ደምና ንብረት ዋጋ ማሳጣት ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑ አይቀሬ ነው፣ የማጣራቱም ሂደት ሆነ የፍርዱም አካሄድና ውሳኔ ለህዝባችን ግልጽ መሆን አለበት በማለት ኢዲኤፍ (EDF) ከወዲሁ ያሳውቃል:-

“ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ፣ …

Exit mobile version