Site icon Dinknesh Ethiopia

የሰሞኑ ጥቃት! – አለማየሁ አበበ

– አለማየሁ አበበ

የጥላቻ ንግግር በህግ የሚያስጠይቅ ከሆነ በቅድሚያ ብዙ የኦሮሚያ ቁንጮ የመንግስት ባለስልጣናትና ካድሬዎች ላይ ጉድ ሊፈላ ይሆን ?

ይህን የምለው በግምትና በጥርጣሬ ሳይሆን ቢያንስ ባለፈው አንድ አመት በተለያዩ ኢቨንቶች ; ስብሰባዎችና የመሣሠሉት ጊዜያት በአፋን ኦሮሞ ለታዳሚዎቻቸው በሚያደርጉት ንግግር ; በማህበራዊ ሚዲያ በሚፅፉት ፅሁፍ : ምናልባትም ለመወደድና ለኦሮሞ ፍፁም ወገንተኞች ናቸው እንዲባሉ የሚጠቀሙበት ቃላቶችና አባባሎች በግልፅ ጥላቻን የሚያንፀባርቁ ናቸው ። ሕጉ ወደኋላ ላለፈው የሚሠራ ቢሆን ኖሮ መረጃውና ማስረጃው ሺህ ነበር ።

በጣም የሚገርመው ደግሞ እነኚህ ተናጋሪዎች ወይም ፀሀፊዎች እንዲያ ሲናገሩና ሲፅፉ ከኦሮሞ ውጪ ሌላ ማንም አፋን ኦሮሞ መናገር : መስማት : መፃፍና ማንበብ የሚችል ያለ አይመስላቸውም፨ ሁሉም ጨርሶ የማይችል ይመስላቸዋል እንዴ ? ለአብነት ያህል እንደምሣሌ የሚጠቀሙባቸው ቃላቶች ብንጠቅስ የኦሮሞ ሕዝብ ኦሮሞ ያልሆነን ሌላ ኢትዮጵያዊ በኦሮሞ ዘንድ እንደ ጠላት : እንደ ክፉ ባላንጣ እንዲታይ : እንዲጠረጠርና ጭራሽ ለኦሮሞ ጭቆና ;ምዝበራና ሰቆቃ ምክንያት እንደሆነ ተደርጎ በኦሮሞዎች ጭንቅላት እንዲቀረፅ ሆን ብለው የሚናገሩና የሚፅፉ ይመስላል ።

ምሣሌ ብንጠቅስ ዘወትር በተደጋጋሚ ከንግግራቸውና ከፅሁፋቸው የማይጠፋው “ዲኒ ” “ዲኒ ኬኛ” የሚለው ኦሮምኛ የአማርኛ ትርጉሙ “ጠላት ” ጠላቶቻችን ” የሚለው መቼም ጣሊያንን ወይም እንግሊዞችን ነው የሚሉት አትሉኝም ። ሌላው ዘወትር ከአፋቸው የማይጠፋው “ጀሪ ” የሚለው ኦሮምኛ ሲሆን የአማርኛ ትርጉሙም ” ሰዎቹ (non-oromos” ወይም እንደ አረፍተ ነገሩ አገባብ “የኛ ያልሆኑት ሠዎች” ማለት ሲሆን ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያኖች ለኦሮሞ ወገንተኛ አንደማይሆኑ የሚፈረጁበትና ለኦሮሞ ጥሩ አመለካከት ያሌላቸው ናቸው የሚል እንድምታ ያለው ነው ። ሌላው በጣም የተለመደውና የሚያሣዝነው ቃል “አለጋ” የሚለው ሲሆን ትርጉሙ “ባዕድ” ማለት ነው ።

በንግግራቸውና ፅሁፋቸው አገባብ ደግሞ ኦሮሞ ያልሆነ ሠው ወይም ስብስብ ወይም ቡድን ሁሉ ለኦሮሞ እንደ ባዕድ የሚቆጠርና የሚፈረጅ የጥላቻ ስሜት ያዘለ ነው ። በጣም ያሣዝናል ። ኦሮሞ በባህሉ አቃፊና ሰው ከኦሮሞ ባይወለድም በጉዲፈቻም ሆነ በሌሎች የባህሉ ትሩፋቶች ኦሮማይዝ የሚያደርግ ነው እየተባለ ጊዜ አገኘን የሚሉ ባለስልጣናትና ካድሬዎች ይህን የጥላቻ መርዝ ሲረጩ ምን ይባላል ? ከፊሉ በኦሮምኛ የተናገሩት ነገር ተተርጉሞ ሲወጣባቸው ይቅርታ እንደመጠየቅ ስም ለማጥፋት ነው ገለመሌ እያሉ ይከራከራሉ ።

እስቲ ይህን የኔን ትዝብት ኦሮምኛ የምትችሉ ሰዎች ሌሎችን የለየላቸውን ሚዲያና አክቲቪስቶችን ብቻ ሳይሆን ባለስልጣናትና ካድሬዎችን በኦሮምኛ ሲናገሩ ተከታተሉና አዳምጧቸው ወይም በማህበራዊ ድረገፅ ላይ የኦሮምኛ ፅሁፋቸውን አንብቡና ፍረዱ ።

የጥላቻ ንግግርና ፅሁፍ ህጉ ያለምንም አድሎ የሚፈፀም ከሆነ የመጀመሪያ ሰለባዎቹ ማን እንደሚሆኑ ለማየት ያብቃን ።ሰሞኑን እየደረሰ ያለው ጥቃት እኔ ላይ እንደደረሰ ነው የምቆጥረው ለሞቱት ነብስ ይማር ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ።

Exit mobile version