Site icon Dinknesh Ethiopia

‹‹ግብፅ የህዳሴ ግድቡ ለኢትዮጵያ አያስፈልጋትም የሚል ፍላጎት እንዳላት ነው ለእኛ የሚገባን›› ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)፣

ግብፅ

የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ከግብፅና ከሱዳን ልዑካን መሪዎች ጋር

ዮሐንስ አንበርብር

ግብፅ ኢትዮጵያና፣ ሱዳን የታላቁ የህዳሴ ግድብን የውኃ ሙሌትና አለቃቀቅ በተመለከተ ሲያካሂዱት የቆየው የቴክኒክ ድርድር ያለ ስምምነት መጠናቀቁ የሚሰጠው ትርጉም፣ ግብፅ ግድቡ ለኢትዮጵያ አያስፈልጋትም የሚል ካልሆነም ግድቡ በተገቢ ዓመታት ውስጥ በውኃ እንዳይሞላ ፍላጎት እንዳላት ነው ሲሉ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ተናገሩ።

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ የሦስቱ አገሮች ባለሙያዎች ለዘጠነኛና ለመጨረሻ ዙር በአዲስ አበባ ያካሄዱት የቴክኒክ ውይይት ሐሙስ ታኅሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ያለ ስምምነት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ይኼንንም ተከትሎ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

ሲካሄዱ በቆዩት የቴክኒክ ውይይቶች ያልተነካና ያልተመነዘረ የቴክኒክ ችግር እንዳልነበረ፣ በዚህም በሦስቱም ወገኖች በተለይም በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል የነበረው የቴክኒክ ልዩነት በጣም ከመጥበቡ የተነሳ ለመስማማት የሚያስችል ደረጃ ላይ ተደርሶ እንደነበር አስረድተዋል። ነገር ግን ስምምነት ላይ ለመድረስ አለመቻሉንና በግብፅ ወገን ውሳኔ ለመስጠት የሚችለው አካል በዚህ ድርድር ውስጥ አለመኖሩን እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

‹‹በዚህ መንገድ መስማማት ካልተቻለ ግድቡ ለኢትዮጵያ አያስፈልጋትም የሚል አመለካከት ግብፆች እንዳላቸው ነው ለእኛ የሚገባን፤›› ያሉት ሚኒስትሩ፣ ይህ ካልሆነ ደግሞ ግድቡ በተገቢዎቹ ዓመታት ውስጥ እንዳይሞላ ፍላጎት እንዳላቸው ያሳያል ብለዋል።

በአዲስ አበባ በተካሄደው በዚህ የመጨረሻ የቴክኒክ ውይይት ቀድሞ ስምምነት ተደርሶበት ከነበረው በተለየ፣ ግድቡ ከ12 እስከ 21 ዓመታት እንዲሞላ የሚያደርግ የጊዜ ሰንጠረዥ ግብፅ ማቅረቧን ተናግረዋል።

ሙሉውን ለማንበብ

Exit mobile version