Site icon Dinknesh Ethiopia

“አቢይን ያመነ ጉም የዘገነ!” – ብለን ነበር ሰሚ ጠፋ እንጂ – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

አቢይ

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ – ከመጋላ ፌዴራሊ ኡመታ ኦሮሚያ ፊንፊኔ

ምዕመናን! “የፈሩት መድረሱ የጠሉትም መውረሱ” የነበረና ያለ ነው፡፡ የወደፊቱን ጊዜ በጭላንጭልም ቢሆን የምናይ ጥቂት ሰዎች ብዙ ተናግረናል፤ ለፍልፈናል፡፡ ይሁንና ሰዎች መስማት የሚፈልጉት መቃብር ውስጥ አሊያም ቁስላቸውን እያከኩ መሆኑ የማይወጡት ክፉ ዕጣ ሆነና እስካሁን ሰሚ አልተገኘም፡፡

“ከወደ ጅማ አንድ መልከ መልካም ሰባተኛ ንጉሥ በኢትዮጵያ ይነግሥና የትሮይን ፈረስ እየጎተተ ከህንድ ውቅያኖስ ወደ መሀል ደጋማው የኢትዮጵያ ክፍል ቀጥሎም ወደ ሰሜኑ ነባር አቢሲኒያ ያቀናል፡፡ በፈረሱ ውስጥ የተጫኑት መደዴና ዋልጌ አክራሪዎች ከፈጣሪ በተሰጠቻቸው በጣት የምትቆጠር የጥፋትና ውድመት ጊዜ ሁሉንም ነገር እንደ አንበጣ ይረመርማሉ፡፡

ከዚያም ንጉሣቸው ማር የተለወሰ መርዘኛ ምላሱን ተቆርጦ ወደ ታሪክ ጓዳ ሲወረወር የነሱ ጊዜም ያከትማል፡፡ በተረኝነት ስካር የጀመሩትን ጭፈራ ሳይጨርሱ ከምሥራቅ አቅጣጫ ባለከዘራው ንጉሥ ይመጣና መሀል አዲስ አበባ በምኒልክ ቤተ መንግሥት ይሰየማል፡፡ ያኔም የኢትዮጵያ የዘመናት ፍዳ አብቅቶ የዕዳ ደብዳዋም ተቀዳዶ ይጣልና ስደት ወደ ኢትዮጵያ ይሆናል፡፡”

የሚል ትንቢት ሰምቼ ቢሆን ኖሮ  በደስታ ተውጬ አሁኑኑ በዚህች አጋጣሚ እናገረው ነበር፡፡ ግን አልዋሽም አልሰማሁም – ቢያንስ በዚህ መልኩ፡፡

አንድ መሠረታዊ እውነት ግን ልናገር፡፡ አንድ ወገን ጠላት እያበዛ በሄደ ቁጥር የራሱን ኃይልና የደጋፊ ብዛት እያመናመነ ይሄዳል፡፡ ትዕቢትና ዕብሪት ደግሞ ጉዳታቸው በአንድ አዳር አይታወቅም፡፡ የደርግንና የወያኔን ድምበር-የለሽ ትምክህት ማሰብ ይገባል፡፡ ማንም አይነካንም ብለው በትዕቢት ታውረው ሳለ ባላሰቡት መንገድና ባልጠበቁት ሁኔታ ድምጥማጣቸው ጠፍቷል፡፡ ቀን ሲጥል እንዲህ ነው፡፡

የነዚህ “ሰዎች” ጅልነት ደግሞ መለኪያ አጣ፡፡ “ጅል አይሙት እንዲያጫውት” መባሉ ትክክል ነው – የኞቹ ጅሎች ጅልነት ከማሳቅና ከማሳቀቅም አልፎ የስቃያችን ምንጭ ሆነ እንጂ ክፋቱ (እንዴ! የማስተዳደር ችሎታ የላቸው፣ ፍትህ ርትዕ አያውቁ ….ከነዚያኞቹ ምሥጦች እኮ ዕጥፍ ድርብ የበለጡ አጋንንት ሆኑ!)፡፡

ባለፉት 20 ወራት ብቻ የሠሩትንና አሁን ትናንት ደግሞ የሰጡትን ወታደራዊ ሹመት ስናይ በርግጥም እነዚህ ሰዎች አብደዋል ያሰኛል፤ ይህም ብቻ አይደለም – ይሉኝታቢስነትና ሀፍረት የለሽነትም የሚኮረጅ ወይም በተጋቦት የሚተላለፍ መሆኑንም ታዝበናል፡፡ አንድ ሕጻን እንኳን እንደዚህ አያደርግም፡፡

የተሹዋሚዎችን የስም ዝርዝር ስትሰሙ በሀፍረት የምትገቡበትን ታጣላችሁ – እኔ በበኩሌ ስለነሱ በሀፍረት ተሸማቀቅሁ፤ ሰው ነኝ የሚል ፍጡር እስከዚህን የዘቀጠ ደረጃ አይወርድም፤ የሚጠራው ሁሉ ደጃሳና ጉርሜሳ፣ ጫልቱና ዱጋሳ ነው – አንድ ሻል ያለ መካሪ ሰው እንኳን የላቸውም? ስለአቢይ ኢትዮጵያዊነት ያሽቃብጡና ገና ሳያስነጥሰው መሀረብ ያቀርቡ የነበሩ አሽቋላጮች አሁን ምን እንደሚሉ መስማት እፈልጋለሁ፡፡ በመሠረቱ ሁሉም ሰርቤሳም ሆነ ጫልጪሳ ቢሆን ለኔ ችግሬ አይደለም – ችግሩ is the intention behind this modus operandi.

በአፄው ወይም በደርግ ዘመን ቢሆን ለምሣሌ አጋጣሚ ነው ብለህ እንዲሁ ታልፈዋለህ – ከናካቴውም ላታስበውም ትችላለህ፡፡ አሁን ግን የዘር ተዋፅዖ በገነነበትና ጠቀመም አልጠቀመም በዜጎች በጉጉት በሚጠበቅበት ሁኔታ እንዲህ ያለ ዕውርነት ውስጥ መግባት የራስን መቀበሪያ ጉድጓድ በይድረስ ይድረስ አርቆ መቆፈር ነው፡፡

መምህሮቻቸው ወያኔዎች ራሳቸው በአሽሙር ፈገግ ሳይሉባቸው አይቀሩም (አንድ ሕጻን ልጅ አባቱ ውሸት እንዲያስተምረው ይጠይቀዋል አሉ፡፡ ትምህርቱ ቀጠለ፡፡ በአባት ቀጭን ትዕዛዝ ሁለቱም ወደ ሰማይ አንጋጠጡ፡፡ አባት ለልጅ ‹ገበሬዎች በነጫጭ በሬዎች እያበራዩ ጤፍ ሲወቁ ይታዩሃል?› ከማለቱ ልጅ ቀበል አድርጎ ‹ውይይይ… አባዬ ጉድ ሆንኩልህ!› ብሎ ማልቀስ ይጀምራል፡፡ አባት ደንግጦ ‹ምን ሆንክ ልጄ?› ብሎ ቢጠይቀው ‹ዕብቁ ዐይኔ ውስጥ ገባ!› ይለዋል፡፡ ያኔ አባትዬው “አሃ! ከኔው በልጠህ የለም እንዴ! ምኑን ውሸት አስተማርኩህ ታዲያ!› በማለት የዕለቱን ክፍለ ጊዜና ጠቅላላ ፕሮግራሙን ዘጋው ይባላል፡፡ አባት ወያኔና ልጅ ኦህዲድ/ኦነግም እንደዚሁ ናቸው)፡፡ ያጠመዱት ፈንጅ ሁሉ በሙሉ ግርማ ሞገሱ ሲገለጥ የገፈቱ የመጀመሪያ ቀማሾች ግን እነሱው ናቸው፡፡ ያኔ እነሱን አያድርገኝ! ለቀንም ቀን አለውና ይህን እንጠብቅ፡፡

እንግዲክ ልበልና ነገሬን ልቀጥል እንደኃይሌ ገ/ሥላሤ – እንግዲክ ኦነግ ማለት ማሰብ የማይችሉ የነፈዞች ስብስብ ነው ማለት ነው፡፡ ሁሉንም ነገረ ሥራቸውን ስታዩ የሰው መዓዛና ሽታ የለባቸውም፡፡ የወለጋውን የተማሪዎች እገታ ድራማ፣ የወለጋ ባለሥልጣናትን ግድያ፣ ኦርቶዶክስን የማጥፋት ዘመቻ፣ ከነባሩ የሀገራችን ባንዲራና ከአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማቱም ጭምር ያላቸውን ጠብ ያለሽ በዳቦ፣ ጴንጤንና ሙስሊም አክራሪዎችን እየመረጡ ትላልቅ ሥልጣኖችን የማደል የቂል ተግባር፣ አማራ ጓዳ ድረስ በመግባት ያከናወኑትን ምርጥ አመራሮችን የመግደልና ምናልባትም የማገዳደል ሥራ፣ ኢንጂኔር ስመኘውን የማጥፋትና ራሱን በራሱ ነው ያጠፋው የማለት ሚዛን የማይደፋ ከንቱ ሙከራ፣ በጠ/ሚኒስትራቸው በኩል በየጊዜው የሚሰራጨው የውሸት መድብልና ጉንጭ አልፋ የተስፋ ዳቦ ቱሪናፋ (ለአብነት ነዳጅ ወጣ፣ ባመጠቅነው ሣተላይት “በቀን አሥር ጊዜ ልንመገብ” ተቃርበናል ዓይነት የቁጭ በሉ ቱሪናፋ፣…) … ሁሉ ሲቃኝ እነዚህ ሰዎች “ይች ሰው ቸኮለች ልታድር ነው መሰል” ያስብላሉ፡፡

 

ሙሉውን ለማንበብ

ምንጭ፡ ዘ-ሐበሻ

Exit mobile version