Site icon Dinknesh Ethiopia

የኦሮሞ ብሄርተኝነት ለኢትዮጵያ ህልውና ግልጽ የሆነ አደጋ

የኦሮሞ ብሄርተኝነት

የኦሮሞ ብሄርተኝነት ለኢትዮጵያ ህልውና ግልጽ የሆነ አደጋ ያረገዘ መሆኑን ኦፍኮ የጀመረው የምርጫ ቅስቀሳ በግልጽ እያሳየ ነው

 

መራራ ጉዲና የነ አቢቹ አገር ላይ ቆሞ “ከተመረጥን በሚንልክ ቤተመንግሥት ላይ የታደሰ ብሩን ሃውልት እንገነባለን” ማለቱ የኦሮሞ ብሄርተኞች በለስ ቀንቶአቸው ቢያሸንፉ አገራችንን የሚከቱበት ትርምስና ጦርነት ምን ያህል የከፋ ሊሆን እንደሚችል አመልካች ነው።

የጀነራል ታደሰ ብሩ የትግል እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን የማፍረስ አለማ የነበረው ፣ ባንድራዋንና በነጭ ወራሪ ላይ የተቀዳጀቺውን ድል የሚያራክስ እንዳልነበረ ብዙዎቻችን ጠንቅቀን እናውቃለን።

የጀነራል ታደሰ ትግል ልክ አንደነ ጀነራል መንግሥቱ ንዋይ ግርማሜ ነዋይና ከነርሱም ቦኋላ የንጉሰነገስቱን ፊውዳላዊ አገዛዝ በጽናት እንደታገሉትና መስዋእት እንደሆኑት የተማሪዎች እንቅስቃሴ ፋና ወጊዎች በአድሃሪ አስተሳሰብና ብሄራዊ ጭቆና ላይ የነበረ ኣንጂ ቦኋላ ላይ የማርክሲስት ሌኒኒስት ርእዮት አራማጆች በሚናባቸው የፈጠሩት ከሀበሻ እራሷን ያገለለች ኦሮሚያን ለመፍጠር ወይም በአያቶቻችን የጋራ ገድል የተጻፈውን ታሪክ ለመካድ አልነበረም።

ይህንን ሃቅ ብሄርተኞቹ ወገኖቼ በሚገባ ያውቁታል። ተከታይ ለማፍራትና አላማቸውን ለማሳካት ሲሉ ግን አጣመው ሲጠቀሙበት ኖረዋል አሁንም ኣየተጠቀሙበት ነው።

ከጀነራል ታደሰ ብሩ የትግል አላማ አንዱ የኦሮሞ ህዝብ (በጊዜው በኣዲስ አበባ ዙሪያ የነበረውና ለቤተመንግሥቱ የቀረበው የሸዋው ኦሮሞ ለማለት ይቻላል ) የመማር እድል ኣንዲያገኝ ነው ። ለዚያውም በአማርኛ ቋንቋ። ለታደሰ ብሩ አማርኛ የፖለቲካ ሥልጣን ለመቆጣጠር መሣሪያ እንጂ ጠላት የሆነ ባለቤት(ማህበረሰብ ) ያለው ቋንቋ አልነበረም።

ጀኔራል ታደሰ ብሩ በብቃቱና በችሎታው ተመልምሎ ወታደራዊ ትምህርት ውስጥ አልፎ ከጀነራልነት ማእረግ እንደደረሰ አንድ የወቅቱ መኮንን ለኢትዮጵያ አንድነትና ለባንድራዋ ልዩ ፍቅርና ክብር የነበረው ብቻ ሳይሆን ሚንልክን የሚመለከተው በጥቁርና ነጭ የሰው ልጅ መካከል የሃይል የበላይነት ፈጥሮት የኖረውን ልዩነት ኣደዋ ላይ የሰበሩና በባርነት ቀንበር ሲሰቃይ ለነበሩ የጥቁር ዘር ሁሉ ኩራትና መመኪያ መሆናቸውን እንጆ በፈጠራ ትርክት እራሳቸውን አሳንሰው በበታቸኝነት ስሜት የሚሰቃዩ የኦፍኮ መሪዎች በተያያዙት የፖለቲካ ቅስቀሳ እንደሚያራግቡት ወራሪ ናቸው ብሎ ኣይደለም።

ታደሰን የመሰለ በንጉሰነገስቱ ሥርእት ተምሮ ለዚያ ማእረግ የደረሰ የኦሮሞ ተወላጅ ሚንልክ አደዋ ላይ ጣሊያንን ድል አድርገው ባይመልሱ ኖሮ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደተቀረው አፍሪካዊያን ወንድሞቹ የራሱ በሆነው ቋንቋ የመናገር እድል ሊኖረው እንደማይችል አያውቅም ነበር ብሎ በስሙ መነገድ እርሱን ማዋረድ እንጂ የማጀገን ተልእኮ ሊኖረው አይችልም ።

ዘመኑ የሥልጣኔ ዘመን ነው። ከዚህ ሥልጣኔ አንዱ ግለሰቦች ስለራሳቸው ነጻነት የመወሰን መብት እንደመሆኑ የኦፍኮ መሪዎች በሚንልክ ባሪያ ሆነን ነበርን ብለው በዚያ የባርነት ሥነልቦና ውስጥ መኖር ምርጫቸው ከሆነ መብታቸው ነው። ምንልክን ኣስከነ አስተዳደራዊ በደላቸው የነጻነታችንና ብሄራዊ ኩራታችን መሰረት ናቸው ብለን እርሳቸው የመሰረቱትን አገር ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ አድርገን ለልጅ ልጆቻችን ለማስረከብ ለምንመኘው ሚሊዮኖች ኦፍኮም ሆነ ሌላው ብሄርተኛ አደጋ የመሆንና አገራችንን የመበታተን መብት ግን ሊኖራቸው እንደማይችል በዚህም ምክንያት ባንታገሳቸው ህግዊ መብታችን መሆኑን ሊያውቁልን ይገባል።

ስለዚህ በኢትዮጵያችን ህልውና ላይ የሚቃጣ ማንኛውም ቅስቀሳ በጊዘው አደብ ሊገዛ ይገባል። ዛሬ ኦፍኮ እንደጦር ጋሻ የሚመካበትን ቄሮ የፈጠረው ለዲሞክራስና ለእኩልነት ሁላችንም በየፈርጃችን ስናካህደው የኖርነው ጸረ ወያኔ ትግል ነው። በዚህ ምክንያት ሁላችንም ለቄሮ ፣ ፋኖና ዘርማ መፈጠር አስተዋጾ አድርገናል። ከሁላችንም በላይ ደግሞ በትግሉ መጨረሻ ከወያኔ ውስጥ ሆነው ለህዝባዊው የነጻነት ትግል ወገንተኝነታቸውን በጽናት ያስመሰከሩ በቅድሚያ በኦቦ ለማ፡መገርሳ ይመራ የነበርው ኦህዴድ ቦኋላ ላይ ደግሞ በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ይመራ የነበረው ብአዴን ከፍተኛውን ድርሻ አበርክተዋል።

ከኣዲስ አበባው ማስተር ፕላን ቦኋላ ኦህዴድ በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ አመጽ ውስጥ ለውስጥ እየገፋ ህወሃት ያሰማራውን ሠራዊት የመግደል ኣቅም ባያሽመደምደውና መረጃ የማግኘት አቅሙን ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ውጪ ባያደርገው ባዶ እጁን እስከ መጨረሻው ጥይት ተቋቁሞ አሁን የተቀዳጀነውን ድል የሚያስመዘግብ ቄሮ ማየት ባልቻልን ነበር። እንዲያውም ቄሮ ኦሮሚያ ውስጥ ከከፈለው የህይወት መስዋኣትነት የከፋ የጥይት እራት ሆኖ ህወሃት እንዳሰበቺው የመቶ ኣመት የመግዛት ህልሟን ለአመታት ባራዘመች ነበር።

ሲጠቃለል የቄሮ እንቅስቃሴ ከሚኒሶታ በተሰጠ መመሪያ አሁን ለደረሰበት እንዳልደረሰ ፣ በተለይም የፋኖ ድጋፍና በህወሃት አገዛዝ የተማረረው የአማራው ህዝብ አጋርነት ባይታከልበት ኖሮ የትም ሊደርስ ይችል ባልነበረ ድል መኮፈስና ለሰላማችን ስጋት ከመሆን መታቀብ የብስለት መግለጫ ኣንደሆነ ማወቅ ጠቅቅሚ ነው።

ምንጭ፡ ዘ-ሐበሻ

Exit mobile version