Site icon Dinknesh Ethiopia

በሰሜን አሜሪካ የሚንቀሳቀሰው የወላይታ ፅንፈኛ ጠባብ ብሄረተኛ ቡድን የወላይታን ዳያስፎራን ከቶውንም የማይወክል ነው።

ከአገር ወዳድ የወላይታ  ኢትዬጵያዊያን ዳያስፎራ አባላት የተሰጠ መግለጫ

February 2, 2020

 

መላው የኢትዬጵያ ሕዝብ ወላይታን የምያውቀው ለኢትዮጵያ አንድነት ፣ ሉዓላዊነትና ህልውናዋ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር  በእኩል የህይወት መስዋእትነት ሲከፍል መቆየቱንና ከሁሉም ኢትዬጵያዊ ወገኑ ጋር በአብሮነት በመኖር በእንግዳ ተቀባይነቱ ነው!

የወላይታ ህዝብ ሕወኃት ወጋጎዳ በሚል ጥቃት ሲፈፀምበት አቤት ያለውም ለኢትዬጵያዊ ወገኑ ነው!  ችግር እንኳን ሲገጥም ለአገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ድምዳሜ ለመድረስ በውይይትና በመግባባት በመፍታት ተቻችሎ የመኖር የዳበረ ባህልና አኩሪ ታሪክ ያለው ማህበረሰብ ነው።

ሆኖም ባለፈፉት ለ27 ግድም ዓመታት ተንሰራፍቶ  የነበረው የህወሀት/ ኢህአደግ ከፋፍለህ ግዛ ስርአት ከአብራኩ የወጡትን ጥቂት ሆድ አደር ካድሬዎችን በማሰማራት የወላይታን ህዝብ አሰቃይተዋል ፣ እምቢኝ ያሉትን ንብረትና መሬቱን ቀምተውበታል ፣ የመናገር የመደራጀት ነፃነቱን ገፈው አፍነው ገዝተውታል ፣ እስከ ዛሬ ለውጥ መጣ ቢባልም እነዚህ ካድሬዎች ከፍተኛ ሰንሰለት ከትላንት ገዳዬቻችን ዘርግተው ህዝቡን ዛሬም እያስጨነቁ የህወሀትን አጀንዳ እያስፈፀሙ ይገኛሉ።

በውጪ አገራት ከምንገኝ የወላይታ ተወላጆች ለህዝብ የቆሙ ግለሰቦች ተሰባስበው ከሌላው ኢትዬጵያዊ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለዲሞክራሲና ፍትህ ሲንጮህ በተቃራኒው ከአፋኙ ቡድን ተጠግተው የአርሶ አደሩን መሬት በነፃ ተቀራምተው እየወሰዱ የደለበ ሀብትና ንብረት በማፍራት በጊዜው የወያኔ ጉዳይ አስፈፃሚ ከሆነው በአሜሪካ የኢትዬጵያ ኤምባሲ ተብዬው ዲፕሎማቶች ጋር በመሆን የፈለጉትን እየፈፅሙ ለእውነትና ለህዝብ ልዕልና ይታገሉ የነበሩ የወላይታ ተወላጆችን ሽብርተኛ በማሰኘት ስማቸው በሕወኃት/ኢህአደግ የደህንነት ዝርዝር እንድመዘገብ ሲያደርጉ ቆይቷል።

ከዚህም አልፈው በዘር በጎሳና በሀይማኖት በመቆራኘት ስደተኛ ተወላጆች ተባብረው በአንድነት  በመቆም ማህበራዊ መተጋገዝን ለማጠናከር በጋራ ያቋቋሙት እድር ሳይቀር ሰርገው እየገቡ እርስ በርስ በአሉባልታ በማጋጨት እንዲበተን ሲያደርጉ የህዝብን አንደበት ለማሰማት ይቻል ዘንድ በጋራ ያቋቋምነውን የወላይታ ተወላጆች ወዳጆች ማህበር በሚል የመሠረትነውን ( አዋናንና ) እንደዚሁም የወላይታ ልማት ማህበርን  ከወያኔ እቅፍ ውስጥ በመውጣት በስደት ስም ወደ ሰሜን አሜሪካ የመጡ እነዚሁ ሰላዬች ሰርገውበት በመግባት እርስ በርስ ፀጉር የመሰንጠቅ ውዝግብ በማመፍጠር ተቆጣጥረዋል ፤ የዚህ ቡድን ቁንጮ በመሆን በአገር ቤት የሚገኙት ደግሞ አሁን በአገር  ቤት የለውጥ ጭላንጭል ሲታይና ወንጀለኛው ህወሀት መቀሌ እንደመሸገ እነዚሁ የወላይታ ካድሬዎች ከሕወኃትና እንደዚሁ ከእነ ጃዋር የኦሮሞ ፅንፈኞች ቡድን ጋር በመጎዳኘት የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ የተባለውን ፅንፍ ድርጅት በአገር ቤት ሲመሰርቱ መቀሌም እንደ ውኃ መንገድ በመመላለስ በፋይናንስ አጠናክረው በዚሁ ድርጅት ውጥን ተዋናዬቹ እነ አሰፋ ወዳጆ ፣ አስራት አሳሌና አልማዝ አንጁሎ የተባሉና ሌሎችም የህወሀት መልዕክተኞች ወላይታን በክልል ጥያቄ አሳበው እንደ አዋሳው በወላይታን ሕዝብ ላይ ቀውስ መፍጠርና ከተሳካላቸው ከሌሎች አካባቢዎች የመጡና ጥረው ግረው ለስኬትም የደረሱ ት ላይ እንደዚሁ ተመሳሳይ እልቂት እንድፈፀም ያወጡት እቅድ በአርቆ አስተዋዩ ሰላም ወዳድ የወላይታ ሕዝብና በመንግስት በኩልም ሰላማዊ ዜጎች በእነዚህ አጀንዳ የእርስ በርስ ጥቃት ሰለባ እንዳይሆኑ  የፀጥታ ጥበቃውን በማጠናከሩ አንዧቦ የነበረው አደጋ ልከሽፍ ችሏል፤

እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የአገር ቤት ክንፍ የሲዳማን ፈሊጥ በመከተል ክልል በራሳችን እናውጃለን በሚል የወጠኑት እቅድ ባለመሳካቱ ተቆጭተው  ትግራይ ሚድያ ሀውስ ቲቪ በሚባለው የሕወኃት ፕሮፓጋንዳ ሚድያ ላይ በመውጣት  መንግስት ፀጥታ ለማስከበርና ወታደር ለማዘዝ ስልጣን የለውም ወላይታ ማንንም ሳይጠይቅ ክልል መሆን ይችላል የሚል መግለጫ ሰጡ ፣  ከዚያም በመቀጠል በስሜን አሜሪካ በወላይታ ተወላጆች ስም ወላይታ ከደቡብ ክልል ጋር ያለውን ማንኛውንም ግኑኝነት አቁሞ በራሱ ክልል መሆኑን ማወጅ እንዳለበት በውጭ ሆነው የወላይታንም ይሁን የአገራችንንም ሰላም ለማወክ ውክልና ሳይኖራቸው በስሙ እየነገድበት አዛዥ በመሆን በየደረሱበት እነዚህ ጥቂት ሰዎች መግለጫ አውጥተዋል።

በዚህ ተልዕኮ ስር ያሉት ሰሞኑን ሚኒሶታ ግዛት ፅንፍ ከረገጡ  የጃዋር ጋሻ ጃግሬዎች ከሆኑ ጥቂት የኦሮሞ ተወላጆች ድጋፍ በማግኘትና በመታጀብ እናት አገራችን አሁን የምትገኝበት የህልውና አደጋ ሳያሳስባቸው ፣ የወጣቶቻችን ሴት እህቶቻችንን ጨምሮ ከ 50 ቀናት በላይ መታገትናና  መጨረሻቸው ሳያስጨንቃቸው የወላይታ ክልል ጥያቄ በአስቸኳይ እውን ይሁን በማለት የራሳቸውን ባንዲራ ይዘው ሚኒሶታ አደባባይ መውጣታቸው ምንስ ያክል ከፅንፈኞችም ከህወኃትም ጋር ተቧድነው በርብርቦሽ ኢትዬጵያን ለማዳከም እያደቡ እንደሆነ ማሳያ ነው።

ይህ በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው ፅንፈኛ ቡድን ዛሬም ለሰብዓዊ መብትና ለዲሞክራሲ የምታገሉትን የወላይታ ተወላጆች አንደበት ለመለጎም  በተካኑበትና በለመድት ህወኃታዊ የስም ማጥፋት ዘመቻና  ተራ አሉባልታ  እየነዙ ለዚህም ከህወሀት ለሽብርና ሰላማችንን ለማናጋት ተግባር እንዲውል  በሚሰጥ ድጎማ ወላይታ ዲጂታልና ሌሎችን ሚዲያዎችን በመክፈት ሕዝባችንን በማደናበር አሀዳዊያንን ( ጨፍላቂዎችን) ወላይታ አታስገቡ ፣ ስለ ክልል ስለመሆን እንጂ ሌላ ጥያቄ አታንሱብን ፣ ስለ ወላይታ ማንነት እንጂ የኢትዮጵያ ጉዳይ ቀዳሚ እንዳልሆነና ይህንን  የሚያዘናጉን ጠላቶቻችን ናቸው በሚል ለአንድነቱ ቀንዓይ የሆነውን ሕዝብ ወደ ጎሰኝነት ጥግ ለማስገባት የፕሮፓጋንዳ ስራ በሰፊው እየሰሩ ይገኛሉ።

ለዚህ ጉዳይ በውጭ እንደመንጠላጠያ የምጠቀሙት በቀደምት ካድሬዎቻቸው አደራጅተውና ሰንገው በልማት ስም በአዲስ የሰየሙት በስሜን አሜርካ የወላይታ ልማት ማህበርን ፣ እንደዚሁም ቀደም ሲል በጠንካራ አገር ወዳድ የወላይታ የአካባቢው ተወላጆች ተመስርቶ የነበረውን የወላይታና ወዳጆቹ ማህበር (አዋናን) በመሣሪያነት በመጠቀም ውክልና ባልሰጠው ማህበረሰብ ስም በመነገድ መግለጫ ይሰጣሉ ።

በዘመነ ሕወኃት የወላይታ የድሕንነት መዋቅር ቤተሰብ ከሚባሉት የቀድሞውሞው የሕወኃት/ኢሕአደግ የፓርላማው ሚንስትር ዴኤታ የነበረውና በአሁኑ ወቅት በደቡብ አፍርካ የኢትዬጵያ ዲፕሎማት የሆነው አማኑኤል አብርሃም ታናሽ ወንድሞች በወቅቱ ከነበረው አገዛዝ የተለያየ ድጋፎች ተሰጥቷቸው በርካታ ገንዘብ ሰብስበው በመንግስት ገንዘብ አንደኛ ማዕረግ አውሮፕላን ትኬት ተገዝቶላቸው ከዚህ ቀደም ሲል ዋሽንግተን ዲሲ መጥተው  ኑሮአቸውን ካደረጉት፤

1, በወቅቱ በዘመነ ህወኃት/ኢህአደግ የኢትዬጵያ ወጣቶች ሊግ አምባሳደር በሚል ስልጣን የነበረው አሸናፊ አብርሀም

2, እንደዚሁ የነዚሁ ወንድም የሆነው በዚሁ ዘመን የኢትዮጵያ ጋዜጤኞች ማህበር ፕሬዝዳንት የነበረውና በአንድ ወቅት ከጋዜጠኛ በተነሳ ጥያቄ ” አንድም ጋዜጠኛ በእስር ላይ የለም በማለት ” በመቶዎች ጨለማ ውስጥ ታጉረው ስቃያቸው እንዲቀጥል ሽምጥጥ አድርጎ የካደው አንተነህ አብርሃም፤

3, ከመቀሌው የህወሀት ቡድን ድጎማ እየተደረገ በዚሁ አካባቢ ሚዲያ ከከፈቱት የቀድሞ ስለላ መረቡ ተዋንያን ከነበሩት አንድ እሸቱ ፀጋዬና ኤርምያስ አሳሌ ሆነው ለሕዝብ አፈናና የመብት እረገጣ መሳሪያ ሆነው ያገለገሉ፣ ዛሬ ስደት በሚል ከአገር ወጥተው በዋሽንግተንና አካባቢው ተሰግስገው እናት አገራችን እነርሱን መሰል በማንነት ጥያቄ የሰከሩ ባለ አጀንዳዎች አስተባብረው ዛሬ አገራችን መረጋጋትና ሰላም እንዳይኖራት በበርካታ ቦታዎች የማያባራ ቀውስን እየደግሱ ያሉትን አጀንዳ የሚጋሩ እነዚህ ከላይ የገለፅናቸው ግለሰቦች ድብቅ ሴራቸውን ያልተረዱ መሰል ጢቂት ተከታዮች በመያዝ የወላይታን ህዝብ ከሌላው የኢትዬጵያ ሕዝብ ለመለየት ያለወትሮው በራሱ ጥያቄ ብቻ እንዲሰክር የርሱ ጥያቄም ዕውን የሚሆነው በቅድሚያ ዜጎቿ በየትም በሰላም ወጥተው የሚገቡባት የተረጋጋች የጋራ አገር ስትኖረን መሆኑን ግምት እንዳይሰጠው ጨለምተኛ የማድረግ መቆሚያ የሌለው የስነልቦና ጦርነት እያካሄድበት ነው፤

አሁን በአገሪቱ የምናየው የማንነት ጥያቄ ጥግ ደርሶ ክልል ልሁን ጥያቄ እንደ ተስቦ እየተስፋፋ የወደፊቷን ኢትዬጵያ ሰላም ክፉኛ እንደሚያናጋት መገመት ይቻላል።

ክልል የሚለው ቃል እራሱ እኔነትን እንጂ አብሮነትን፣አንድነትን ገላጭ ባለመሆኑ ጥያቄውን ከአገርና ከሕዝብ አንድነትና መስተጋብር አኳያ ይበልጡኑ የመጥበብ ሚና እንዳለው ሁሉ አገዛዙም ለሁሉም ጥያቄዎ ፈጣን መልስ ለመስጠት ፈታኝ እንደሆነበት መገመት ይቻላል!

አበው እንዳሉት ውሻ በቀደደው ሆነና የወላይታ ሕዝብም ሕዋታዊው ሕገመንግሥት ይህንን እስከፈቀደ ድረስ ጥያቄው ምላሽ እንዲሰጠን ማንንም አንጠብቅም በሚል የተፈለፈሉት መሰል ካድሬዎች ሕዝቡን ፋታ አሳጥተውታል።

ሆኖም ፅንፈኛ ፓለትከኞች ይህንን ጉዳይ ለዕኩይ ዓላማቸው ማስፈፀምያ ሲሉ በጉልበት፣ በሽብርና በአመፅ የንፁሐንን ሕይወት ዋጋ በሚያስከፍል እሚቢተኝነት ለማስፈፀም የምያደርጉትን ወከባ አጥብቀን ስናወግዝ እነዚህ ቡድኖች ጥላቻንና ጥፋትን የሚሰብኩ በማንኛውም ሰዓት አመቺ ግዜ እየጠበቁ እንደ ሕዝብ ተወካይ ፅንፍ መግለጫዎች እየሰጡ ሕዝባችንን የሚያዘናጉ ሁሌም ጥያቄውን በኃይል ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ በመጠየቅና ከሚመለከታቸው ጋር በመምከር መብቱን የሚጠይቀውን የወላይታ ሕዝብ ሰላሙን የሚያውኩ መሆናቸውን የኢትዮጵያው አገዛዝና ሰላም ወዳዱ ኢትዮጵያዊ እንድያውቅና ተገቢውን ጥንቃቄ እንድያደርግ እያሳሰብን በወላይታ ዲያስፓራ ስም በዚህ ቡድን የምወጡ ፅሁፎችም ሆኑ መግለጫዎች እነርሱ እራሳቸውን እንጂ ማናችንንም የማይወክሉ መሆኑን እናሳስባለን።

ኢትዮጵያ በክብር ለዘለአለም ትኑር!!

በስሜን አሜሪካ አገር ወዳድ የወላይታ ዲያስፓራ አባላት።

February 2nd, 2020

Washington DC.

በስሜን አሜሪካ ከምንኖር ትውልደ ቅማንት ጎንደሬ ኢትዮጵያዊያን ለጋሞ


Source: ZeHabesha

Exit mobile version