Site icon Dinknesh Ethiopia

የናዚዎች የኑረንበርጉ የጋብቻ ክልከላ ህግና በሀገራችን ውስጥ እየተደመጠ ያለው ተመሳሳይ አስፈሪ ጥሪ

NurembergRaceLaw

Background

Two distinct laws passed in Nazi Germany in September 1935 are known collectively as the Nuremberg Laws: the Reich Citizenship Law and the Law for the Protection of German Blood and German Honor. These laws embodied many of the racial theories underpinning Nazi ideology. They would provide the legal framework for the systematic persecution of Jews in Germany.

Adolf Hitler announced the Nuremberg Laws on September 15, 1935. Germany’s parliament (the Reichstag), then made up entirely of Nazi representatives, passed the laws. Antisemitism was of central importance to the Nazi Party, so Hitler had called parliament into a special session at the annual Nazi Party rally in Nuremberg, Germany.

 

 

ማርች 8 በሚታስብበት በአል አንድ የቪዲዮ ቅጂ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀ መንበርና ምክትላቸው ፐሮፌስር መረራና ኦቦ በቀለ ገርባ በተገኙብት አንድ ወጣት ሴት ከአሁን በኹላ ኦሮሞ ከአማራ (ነፍጠኛ ይላሉ) ጋር መጋባት የለበትም አሁን ያገባችሁ ብትኖሩም ነፍጠኛን (አማራን ማለት ነው) ፍቱ በማለት ቅስቀሳ ሲካሄድ ያሳያል።

ወጣቷ ይህን ሰትናገር ኦቶ በቀለ ገርባና ፐሮፊሰር መረራ የታየባቸው መገርምና መረበሽ ሳይሆን እየተሾካሾኩ ይሰቁ እንደነበርም ቪዲዮው በግልጽ ያሳያል። በቦታው የነበረውም ተመልካች ድጋፉን በጭብጨባና በሳቅ ሲገልጽ ይታያል ይደመጣል።
ይህ “ንጹህ የአሮሞ ዘር” መኖር አለበት የሚል አባዜ ካሁን በፊትም በአቶ በቀለ ገርባ ሲቀነቀን የተደመጥ አንደሆነ አናስታውሳለን። ከዚያም አልፎ ፐሮፊስር መረራም ሆኑ ጀዋር ገብረጉራቻና ደብረሊባኖስ አካባቢ ባደረጉት የህዝብ ስብሰባ ላይ ከሌላ ብሄር ጋር ተጋብተው የተዋለዱትን የኦሮሞ ተወላጆች “ዲቃሎች” በማለት ሲያጥላሉና እንደ ጎደሎ ሰያቀርቧቸው ከስማን ሁለት ወር አልሞላም።

ይህ “የንጹህ ዘር ፍላጋ” አባዜ ዛሬ እየተቀነቀነ ያለው መንግስታዊ የፖለቲካ ህይልና ሰልጣን በሌላቸው ሆኖም ግን ያንን ለማገኘት ሌት ተቀን በሚሰሩት ብዙ ተክታይ ባላቸው ፖለቲከኞች በአነ በቀለ ገርባ: ፐሮፌስር መረራና ጀዋር መሆኑን ሰመለከት አጅግ ያሳስበኛል።

ዛሬ ስልጣን ሳይይዙ አንዲህ የሚናገሩ ፖለቲከኞች ነገ በክልልም ይሁን በሀገር ደረጃ ሰልጣን ቢይዙ ደግመው ደጋግመው “አትጋቡ “ “ዲቃላ” እያሉ በሚናገሩትና ክሌሎች ሁሉ ሊነጥሉት በሚጥሩት ህዝብ ላይ ምን ሊያድርጉ ይችላሉ ብየ ሳስብ እጅግ ይረብሽኛል።

የነዚህ ፖለቲከኞች ቅስቅሳና ትርክት ላይ የተመሰረተው አካሄድ አስካሁንም ስንት “ነፍጠኛ “ እንዳፈናቀለ፣ ገደል አንዳስወረወረ ፣ ቤት ንበረቱን አንዲቃጠል አንዳደረገ ለምናውቅ ሁሉ፣ ቀጣዩ እርምጃ ከረዠም አምታት የጥፋት ዘመቻ የተረፈውን ሙልጭ አድርጎ ማጽዳት እንዳይሆን ያሰጋናል።

ክዚህ አንጻር ከላይ የተገለጠው አይንት ቅስቀሳ የሚያመቻችውን የጥፋት መደላድል አና ሊሆን የሚችሉትን አስፈሪ ሁኔታዎች ለመገንዘብ ወደታሪክ ዘወር ማለት ተግቢ ነው።

ለትምህርት ያክል በናዚ ጀርመን “የአርያንን ዘር ንጹህነትና ክብር ለመጠበቅ “ ፣ በሚል፣ መነሻ የዚህን ዘር ከሌሎች በተለይም ከነገደ እስራኤሎች (jews ክጀዎች ) ጋር መጋባትን በሀግ የሚከልክል “ የኑረንበርግ ህግ the Nuremberg Laws የተሰኘ ድንጋጌ በአውሮፓወያኑ አቆጣጠር በሲፐትምበርር 15፣ 1935 በሂትለር ፓርቲና መንግስት ደንግጎ ነበር።

የሀጉ ጭብጥ የነገደ አስራኤል ዝርያ ያለው ማንኛወም ስው ከሌላ የጀርመን ዜጋ ጋር አንዳይጋባ የሚደነግግ ነበር።ይህ ነገደ እስራአኤሎች (jews ጀዎች ) በጀርመን ውስጥ ለማጥቃት፣ ንብረታችውን ለመንጠቅና መጨረሻም ክሁሉም የአውሮፓ አህገሮች በመስብስብ በሚሊዮን የሚቆጠሩትን በጋዝ አፍኖ ዘር ማንዘራችውን ለማጠፋት መስረት የጣለ ዘግናኝ ህግ ነበር።

አጅግ የሚገርመው ይህ እስክ ስድስት ሚሊዮን የሚቆጠሩ ነገደ እስራኤሎችን (jews) በግፍ ለማጥፋት የህግ መሰረት የጣለው ድንጋጌ የተረቀቀው በከፊል ወሳኔ ሰጨዎቹ ህጉ ምን ያክል መጠንክር አንዳለበት ሃሳብ የተቀያይሩት በአንድ ምግብ ቤት ተሰብስበው ሲመግቡ በምግብ ማወጫው ሜኑ ካርድ ላይ በመቦጫጨር በደረሱብት ስምምነት እንደነበር ታሪክ መዝግቦታል። ይህ የሚያሳየው በጠላቻ የተመረዙ ፖለቲከኞች “ለሚጠሉት” ወገን ምን ያክል ግድ የሌሽ እንደሆኑና የዚያን ህዝብ ስብእና እነርሱ የሚያዩት እጅግ ዝቅ ባለ መልክ እንደሆነ ነው። ይህ ታዲያ ሊሰነዘር የሚችለውን የአደጋ ደረጃ አጅግ ከፍ ያደርገዋል፡

ገና ከመጀመሪያው እነ ሂትለርን ጭምሮ ፖለቲከኞቹ ነገደ እስራአኤሎች (jews ጀዎች) የጀርመን ህዝብ ችግር ዋናው መሰርት አድርገው ፣ ጭራቅ አስመስለው በሰሩት ስፊ ቅስቀሳ የተነሳ የጀርመንም ህዝብ ለነገድ እስራኤሎች (jews ጀዎች ) ያለው አስትሳስብ ተምርዞ ነበር። አናም ጭፍጭፋው ሲጅመር ብዙ ጀርመኖች ያለማመንታት ግብረአበር ሆነው ተሳተፉ፡፡ የነገድ እስራኤሎችን (jews ጀዎች ) ንብረት በመንጠቅ፣ የተደበቁብትን በመጥቆም ወዘተ የሂትለር ፖሊሲ አስፍጻሚ ሆኑ።

በሀገርችን ሁኔታም ከእማራም ሆነ ከሌሎች የተለያዩ ብሂር ተወላጆች ጋር ተጎራብቶ፣ ተጋብና ተዋልዶ የኖረውን ህዝብ ለፖለቲካ ጥቅም ማስባስቢያ ሲባል የዚህ አይነት ዘር የማጸዳት ቅስቀሳ ማካሄድም ሆነ ሲካሂደ አየሳቁ ዝም ብሎ ማየት ሊያስክትለው የሚችለው አደጋ አጅግ ሰፊ መሆኑን ልሂቃኑ ሊገነዘቡት ይገባል። ይህ በመንግስትም ይሁን በሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲሁም በተራ ዜጉች ዘንድ በቸልታ የሚታለፍ ሊሆን አይገባውም።

ይህን አርኩስ ተግባር ለማወግዝ የሚነሳን በዘር ፈርጆ “ጸረ” በሚል ማስፈራሪያ ለማሽማቀቅ መሞክር ደግሞ የሚሰራ አይደለም። በዝምታ ማለፍ አጅግ ስፊ አደጋን ይጋብዛልና።ሰለዚህም ይህ አደገኛ ተግባር አንዲቆም ሁላችንም ጥሪና ግፊ አናድርግ ፣ ፖሊቲከኞቹም አውነተኛ ገጸታቸውን ይበልጥ ማወቅና በአግባቡ ተጠያቂ ማድረግ ጊዜው የሚጠቀው ተግባር ነው። ለተቃዋሚው ሁሉ በጅምላ ድጋፍ መስጫው ጊዜ አልፏል።

ተቃዋሚዎች መመዘን ያለባችውም መንግስትን በመቃወማቸው ሳይሆን በሚያራምዱት አጀንዳና በተግባር በምናየው ስራቸውም መሆን የኖርበታል።

ሰለዚህ ጉዳይ ይበልጥ ለመረዳት በድረ ግጾች ውስጥ እጅግ በቀላሉ ብዙ መረጃ ማግኘት ይቻላል።የሚከትሉት ጥቂቶቹ ናችው ።

https://www.jewishvirtuallibrary.org/background-and-overview-of-the-nuremberg-laws

https://encyclopedia.ushmm.org/content/en/article/the-nuremberg-race-laws ፣https://www.thoughtco.com/the-nuremberg-laws-of-1935-1779277

Exit mobile version