ግብጽ በአፍሪካ በርካታ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ያሉባት አገር ሆናለች
ግብጽ በአፍሪካ በርካታ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ያሉባት አገር ስትሆን ደቡብ አፍሪካና አልጄሪያ ደግሞ በሁለተኛና በሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
በግብጽ 166፣ በደቡብ አፍሪካ 62 እንዲሁም በአልጄሪያ 60 በኮረናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ይገኛሉ።
እስካሁን 30 የአፍሪካ አገራት ቫይረሱን በግዛታቸው ውስጥ መገኘቱን ሪፖርት አድርገዋል።
ይህ ካርታ እስካሁን ድረስ የኮሮናቫይረስ መገኘቱ የተረጋገጠባቸው አገራት ሲሆኑ የተያዙና በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል።