Site icon Dinknesh Ethiopia

ከኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) – በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ላይ የተሰጡ መግለጫዎች

የኢህአፓ አዲሷ ሊቀ መንበር ስለ ፓርቲያቸው

በቀጣዩ ምርጫና የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ከኢሕአፓ የተሰጠ መግለጫ ግንቦት 2012

  • https://youtube.com/watch?v=QULBAlyq6Qo

በአዲስ አበባ የተከሰተውን መፈናቀል እንቃወማለን

  • https://youtube.com/watch?v=16T5Vbii0pI

ዲሞክራሲያ ቅጽ 48 ቁ 2

  • https://youtube.com/watch?v=16T5Vbii0pI

ሃገራዊ ምርጫ ነሃሴ 2012 መራዘሙን ኢሕአፓ መደገፉን ገለጸ


የኮሮና ወረርሽኝን በመከላከል ዙሪያ ከኢሕአፓ የቀረበ ምክረ ሀሳብ

ሚያዝያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. 

በዓለም ላይ በተለያዬ ጊዜያት ልዩ ልዩ መቅሰፍቶች እየተከሰቱ በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድረሰዋል፤ በሽታው ከተወገደ በኋላም አገሮችን ከፍተኛ ወደ ሆነ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ህብረተሰባዊ ቀውስ እንደከትቷቸው ጥለውት ከሄዱት የታሪክ አሻራ እንረዳልን። ስለሆነም አገሮች እንደዚህ አይነት ወረርሽኝ ሲከሰት እንዴት ሊወጡት እንደቻሉ መርምረን አሁን በዓለም ላይ ህዝብ እየፈጀ ያለውን የኮሮና ወረርሽኝ (COVID-19) እንዴት መቋቋም እንዳለብን ስናስብ ከፍተኛ የሆነ የሰው ፤ የቁሳቁስና የስነ ልቦና ዝግጅት የሚጠይቅ ሆኖ አግኝተነዋል። ስልዚህም የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) መደረግ አለበት ብሎ ያመነበትን ዝግጅት ከተለያየ አቅጠጫ በመመልከት ለመንግሥትም ሆነ ለልዩ ልዩ ተቋሞች የበኩሉን ለማሳሰብ ይወዳል።

በዚህ አጋጣሚ ከመንግሥት በኩል ለተደረገው የትብብር ጥሪም ኢህአፓ ምላሽ ለመስጠት የሞከረ ሲሆን ለወደፊቱም የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁነቱን እየገለጸ ለሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ለፖለቲካ ድርጅቶችም ጭምር፣ አገራችን ያጋጠማትን ችግር በጋራ እንድንወጣ ጥሪውን ያቀርባል። ይህንን ወረርሽኝ ለመቋቋምም የሚከተሉት ተግባራት አስፈላጊ መሆናቸውን ያምናል፡

1. መንግስት ይህን ወረርሽኝ ለመቋቋም የባለሙያ የኤክስፐርቶች አስተባባሪ ቡድን ሊሰይም ይገባል። የጠቅላይ ሚኒሰቴሩ በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት መስጠት ተገቢ ቢሆንም፣ ዋናው አሳብ ከፖለቲከኞች ሳይሆን በሳይንስና መልካም ወጤት ካላቸው ተመክሮዎች ላይ አንዲሆን በዕውቀት፣ በጥናትና ምርምር ላይ የተመሠረተ ቁልፍ የኤክስፐርቶች ምክረ–ሃሳብ ለተግባራዊ ርምጃዎች በጣም አስፈላጊ ነው፣

2. ከግድ የለሽነትና ከባህላዊ ተጽኖው ባሻገር ሕዝቡ ተረጋግቶ እቤት እንዳይውል የሚያደርጉት ሁለት ምክንያቶች አሉ፡ መኖሪያ ቤት ያለመኖር እና መጠለያ ቢኖርም የሚበላ ያለመኖር ናቸው፡፡ መንግሥት ቤት ለሌላቸው ዜጎች ጊዜያዊ መጠለያ ማዘጋጀት ሲኖርበት በከፍተኛ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ ማህበረሰቦች የሚኖሩባቸውን አካባቢዎችን መለየት ያስፈጋል፡፡

3. በማእከልና በየአካባቢው የሚሰበሰቡትን የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና ምግቦች ወደ ማዕከል በማምጣት፣ በተለዩት አካባቢዎች እስከማህበረሰብ የሚደርስ መዋቅር በመዘርጋት እንደ እድርና ሰንበቴ የመሳሰሉ የማህበረሰብ ተቋማትን እና የበጎ አድራጎት ቡድኖችን በመጠቀም አካላዊ መራራቅን በጠበቀ መልኩ የምግብ እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ እደላውን መምራት ያስፈልጋል፡፡ በመኖሪያ ቤታቸው ለሚኖሩ ዜጎች ያልተዘጋጁ ምግቦችን ማደል ሲቻል ወደ ጊዜያዊ መጠለያ ለገቡ ዜጎች የሚሰጠው ግን የተዘጋጀ ምግብ ግን ሊሆን ይገባዋል፡፡

4. በኤክስፐርት ቡድኑ እስከማህበረሰብ የወረደውን መዋቅር እስከአሁን የተሰበሰበውን ምግብና የጽዳት ቁሳቁስ ለማደል ብቻ ሳይሆን በየአካባቢው የምግብ ባንክ በማቋቋም ችግሩ እስካለ ድረስ ማህበረሰቡ ምግብ እንዲያመጣ ማድረግና ቀጣይነት ያለው የምግብ አቅርቦት ድጎማ እንዲያደርግ ማስቻልም ጭምር መሆን አለበት፡፡

5. መንግስትና ተፎካካሪ ፓርቲዎች በጋራ የሚሰሩበት፣ በወረርሽኙ ላይ ያተኮረ እካል መሰየም ያስፈልጋል፡፡ ትኩረቱም ህዝብን ማስተባብር፣ ስለወረርሽኙ ትምርት በሰፊው አንዲሰራጭ ማገዝ፣ አርዳታ ማስባስብ ወዘተ ይሆናል፡፡ መንግሥትና ተፎካካሪ ፓርቲዎች አብረው የሚሠሩበትን ማእቀፍ የሀገርንና የወገንን ጥቅም ባስቀደመ መልኩ በመመካከር ሊያዘጋጁት ይገባል፣

6. በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሲኖሩ በርካቶቹ ማህበራዊና፣ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሠሩም ይታወቃል፡፡ እነዚህ ተቋማት በአብዛኛው ከማህበረስብ ተቋማት ጋር እንደሚሠሩም እሙን ነው፤ ታዲያ እነዚህ ተቋማት በዚህ ወረርሽኙን በመከላከል ተግባር ውስጥ ትርጉም ያለው ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ ይገባል፡፡ እነዚህን ማህበራት የሚከታተለው ኤጀንሲም ሆነ ማህበራቱ ግን በዚህ ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስጋት በጋረጠ ወረርሽኝ ጊዜ ድምጻቸው እየተሰማ ባለመሆኑ ሊንቀሳቀሱ ይገባል ብለን እናምናለን፡፡ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ ደግሞ ሰፊ ሀብት በተለይም ዕውቀትና ልምድ ያለው የሰው ሃይል እንዳለ እሙን በመሆኑ ጥቅም ላይ ሊውል ይገባል ብለን እናምናለን፡፡

7. በሌላ በኩል ለወረርሽኙ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሂደት ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ማህበረሰቦችን በተለይም ሕጻናትን፣ እናቶችን እና አረጋውያንን የሚረዱ ድርጅቶች ትኩረት እየተደረገባቸው ባለመሆኑ የምግብና የጽዳት አቅርቦት ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን ለማየት ተችሏል፤ እነዚህን ተቋማት በመለየት እገዛ ማድረግ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት አካል ሊሆን ይገባዋል እንላለን፡፡

8. ምንም እንኳን ለህብረተስቡ በበሽታው ላይ መረጃ እየተሰጠው ያለ ቢሆንም፣ ጠለቅ ያለ ዕውቀት አንዲያዳብር የሚያስችል ሰፊና ተክታታይ የትምርት ዘመቻ ያስፈልገዋል፣ ትምህርቱም በጽሑፍ፣ በቪዲኦ፣ ስህበት ባላቸው አቀራረቦች የሜዲያ ክህሎት ባላቸው ባለሙያዎች አማካይነት ጭምር ሊሰጥ ይገባል፡

9. አደጋው በመላው አለም የንግድ፣ የቱሪዝም እና የአርዳታ መቀነስ እንደሚያስከትል እሙን ነው። በውጭ ሀገራት ያሉት የአገራችን ዜጎችም ስራ የማጣት እጣ ፈንታ እንደሚደርስባቸው መገመት ቀላል ነው፤ በመሆኑም ወደ ሀገር ቤት የሚላከውን ገንዘብ የመቀነሱ አደጋ አጅግ ሰፊና በተለይም የከተማውን ነዋሪ በእጅጉ የሚጎዳ ሊሆን ይችላል። በመሆኑም የሀገሪቱ አጠቃላይ ቅድሚያ ፍላጎት በድጋሚ ሊመረመር ይገባዋል ብለን እናምናለን፡፡ ይህም የፍላጎት ዳሰሳ የፖለቲካ ቡድነኛነት አመለካከት አንዳያጠቃው ታዲያ የኤክስፐርቶች ቡድን መሰየም ተገቢ ሊሆን ይችላል፣

10. በዚህ ሁሉ መሀል ትልቅ ተስፋ የተጣለባቸው የሀገራችን ፐሮጅክቶች ለምሳሌም እንደ አባይ ግድብ የመሳስሉት በፍጹም አንዳይተጓጎሉ ማድርግ ያሻል፣

11. የፍትህ ስርአቱ አሁን በየ እስርቤቶች ከሚገኙት ታሳሪዎች መሀከል መፍታት የሚገባውን ሁሉ አንዲፈታ፣ በተጨማሪም በአነስተኛ ወንጀል የተከሰሱ ሰዎችን የእስር ብያኔ አንዲዘገይ፣ መፍታት የማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ወረርሽኙን ለማስፋፋት ተጨማሪ ምክንያት አንዳይሆን አቅም በፈቀደ መጠን የሚቻለው እንክብካቤ እንዲደረግ ያሻል፣

12. ይህን ወርርሽኝ ላማስቆም ከላይ ወደታች ትዕዛዝ ማንቆረቆእር ሳይሆን አካባቢያዊ ውሳኔ ክህዝቡ ተጨባጭ ዴሞግራፊ፣ የኑሮ ሁኔታና ችግር ጋር የተዛመደ አርምጃ ቢሆን፣ መሰረታዊ ቁም ነገሮቹ ተመሳሳይ ሆነው ምን ይደረግ ለሚለው ግን ማህበርስቡ ክራሱ ሁኔታ ተነሰቶ የሚሰጠው ሃሳብና የሚያደርገው ተሳትፎ ቢካተት ለውሳኔው እጅግ ጠቃሚ ይሆናል። ተግባራዊ ለማድረግ ቀላልና፣ ተጨባጭነትም ያለው ይሆናል።

13. ሁኔታው አጣዳፊ መሆኑ ቢታወቅም ሌሎች ያደረጉትን ኮርጆ ለማድረግ ከመሞከር በኅብረተሰቡ (በኮሚኒቲው) ውይይት ላይ ያተኮረ መፍትሄ አጅግ ጠቃሚ ነው እንላለን። ሰለዚህም መፍትሄ ፍለጋው ላይ አካባቢያዊ ምክክሩ አሁኑኑ መጀመር የኖርበታል። ህዝብ ያልመከረበትና ያልተቀበለው ውሳኔ የህዝብን ፍላጎት የማያንጸባርቅ ስለሚሆን ለመተግበር ከማስቸገሩም በላይ ውጤታማነቱም ዝቅተኛ ነው የሚሆነው፣

14. በህዝቡ ደህንነት፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ በኩል የሚደርሰው ቀውስ በሽታው ከተገታም በኋላ የተባባሰ ሊሆን ስለሚችል ከፌዴራሉ መንግሥትና ከእየክልሉ መንግሥቶች የህዝቡን ሠላምና ጸጥታ ለመጠበቅና ርሀብና ችጋር እንዳይመጣ ለመከላከል የእህል ክምችት ከአሁኑ መሰብሰብ ይገባቸዋል ብለን እናምናለን።

15. የበሽታውን አደገኝነት በዓለም ዙሪያ ካለው ክስተት ስንገመግም በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዝግጁነት የዳበሩ አገሮችም የገንዝብ አቅማቸውን የተፈታተን መሆኑ እያየን ነው፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግሥት ገንዝብ ሊያበድሩ ከሚችሉ ተቋሞች በአስቸኳይ ገንዝብ መበደር አለበት ብለን እናምናለን። አሁን እዳ ውስጥ የመግባትና ያለመግባት ጥያቄ ሳይሆን ህይወት የማዳን ጥያቄ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል።

16. በመጨረሻም፤ ምንም እንኳን ዲያስፖራው ሊገጥመው የሚችለውን የኑሮ ጫና ቀደም ብለን የገለጽን ቢሆንም እስከመጨረሻው አቅም ድረስ ከዚህ ቀደም ጥቅም ላይ ለማዋል በተሞከረው የአንድ ዶላር በቀን አስተዋጽኦ እንዲቀጥልና ባለው ማህበራዊ ትስስር ሁሉ በመጠቀም ለዚህ ከፍተኛ ሀገርንና ሕዝብን የማዳን ሥራ እንዲተጋ እንጠይቃለን፡፡

አገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅ

Phone : +251 94 422 3216

Email:eprp@eprp-ihapa.com

Exit mobile version