Dinknesh Ethiopia

በትግራይ ክልል የተፈጠረው ምንድን ነው?

ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች ነዋሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ተቃውሞ በማሰማት ላይ እንደሆኑ በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ሲነገር ቆይቶ ነበር።

Source: https://www.bbc.com/amharic/

ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይም ጉዳዩን በተመለከተ በሽሬ እንደስላሴ እና በዋጅራት አካባቢዎች የመልካም አስተዳደር፣ የመሰረተ ልማት እንዲሁም ከሥራ ዕድል ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎችን በማንሳት የተቃውሞ ሰልፎች እንደተካሄዱ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያውን ጨምሮ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ይህንንም ተከትሎ የትግራይ ክልል መንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በየትኛውም ቦታ “የተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ የተፈጠረ የሰላም መደፍረስና ግርግር ፈፅሞ ያልተሰማና መሬት ላይ የሌለ ነው” በማለት ዘገባዎቹን አስተብብሏል።

መግለጫው ጨምሮም “በሽረ እንዳስላሰና አከባቢው እንዲሁም በዋጅራትና አከባቢው ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ፣ ፍትህ መጓደል አለ የሚባለው የተፈበረከ ሐሰተኛ፣ የበሬ ወለደ ወሬ ነው” ሲል አጣጥሎታል።

በተጨማሪም “ሐሰተኛ ወሬ በማሰራጨት፣ የተጠመዱት” ባለቸው የመገናኛ ብዙሃን ላይ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንም “በሚዲያዎቹ የተሰራጨውን ሐሰተኛ የበሬ ወለደ ወሬ አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ” የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ጠይቋል።

ቢቢሲ ከወጀራትና ከሽረ እንዳስላሰ 70 ኪሎሜተር እርቃ ከምትገኘው ማይሃንሰ አስተዳዳሪዎችና ከነዋሪዎች እንደተረዳው በአካባቢዎቹ ጥያቄዎችን በማንሳት ለቀናት የዘለቀ ተቃውሞዎችና የመንገድ መዝጋት ክስተቶች አጋጥመዋል።

የተቃዋሚው አረና ትግራይ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አምዶም ገብረስላሰ በማይሃንሰን እና ወጀራት በተባሉ የትግራይ ክልል አካባቢዎች የተነሱ ሕዝባዊ ጥያቄዎች አሁንም አንዳልበረዱ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

አቶ አንዶም ገብረስላሰ እንደሚሉት ለተቃውሞዎቹ መቀስቀስ ምክንያቶቹ ከዚህ ቀደምም ሲንከባለል የቆየ የወረዳነት ጥያቄ ሲሆን ተገቢ ምላሽ አላገኘንም ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ምዕራባዊ ዞን የሚወስደውን የዳንሻ መንገድ ከዘጉ ዘጠኝ ቀናት አስቆጥረዋል፤ አሁንም ቢሆን “ጥያቄውም አልተፈታም፤ መንገድም አልተከፈተም” ብለዋል።

መነሻ

ለዚህ ሁሉ እንደመነሻ የሚጠቀሰው የወረዳ ማዕከል እንሁን በሚል የሁለት ቀበሌ ነዋሪዎች ያነሱት ጥያቄ ነው። ጥያቄ የቀረበባቸው ቀበሌዎች በሰሜን ምዕራብ ትግራይ የሚገኘው ማይ ሓንሰ እና በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ የሚገኘው ባሕሪ ሓፀይ መሆናቸውን የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል።

ሽረ አካባቢ የምትገኘው የማይሃንሰን ሕዝባዊ ቅዋሜ ከወረዳነት ጥያቄ በዘለለ፥ በስፍራው በተመደቡ አስተዳዳሪዎች ቅር መሰኘትንም ያካትታል ይላሉ የተቃዋሚ ፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ። በደደቢት እና አደጋ ሕብረትም ተመሳሳይ ድርብ ጥያቄዎች መነሳታቸውን ነው አቶ አንዶም የሚናገሩት።

ከጥቂት ዓመታት በፊት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፤ ‘ተሃድሶ’ ባካሄደበት ወቅት፤ በትግራይ የአስተዳደር መዋቅር ለውጥ እንደሚያደርግ አስታውቆ ነበር።

• በአዲስ አበባ ኮካና አብነት የሚባሉት ስፍራዎች የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት ቁጥጥር እየተደረገ ነው

• ከ81 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የአማራ ክልል አስታወቀ

ይህም አስተዳደራዊ ለውጥ ያልተማከለ አስተዳደር ለመፍጠር፣ ሥልጣንን በዋናነት ወደ ወረዳዎችና ጣብያዎች ማውረድ የሚል ነበር። በዚህም መሠረት አዲስ የወረዳ እና የጣብያ አደረጃጀት እንዲኖር ተደረጓል።

የአንድ ወረዳ ማዕከል የሚሆነው ቀበሌ የትኛው ይሁን? የሚለው ግን በአንዳንድ አካባቢዎች አወዛጋቢ ጥያቄን ማስከተሉንና አሁን ለተፈጠረው ነገር መነሻ እንደሆነ ይነገራል።

በሰሜን ምዕራብ ትግራይና በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ የሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ጥያቄ ያቀረቡትም እኛ የወረዳችን ማዕከል መሆን አለብን ብለው ነው።

በሰሜን ምዕራብ ትግራይ የወረዳ ምክር ቤት የወረዳው ማዕከል ብሎ የወሰነውን ቀበሌ ያልተቀበሉ የሌላ ቀበሌ ነዋሪዎች፣ መንገድ ዘግተው መኪና አናሳልፍም ብለው ለተቃውሞ መውጣታቸውን ከዘጋቢያችን ለመረዳት ችለናል።

በአካባቢው አዲስ የተዋቀረ አስገደ የሚባል ወረዳ አለ። በወረዳው ከሚገኙ ሕፃጽ፣ ዕዳጋ ሕብረት፣ ክሳድ ጋባ እና ማይ ሓንሰ የተባሉ ቀበሌዎች ለወረዳው ማዕከልነት ተወዳድረው ነበር።

የወረዳው ምክር ቤት ክሳድጋባ ማዕከል እንድትሆን ውሳኔ ቢያስተላለፍም፤ የማይ ሓንሰ ነዋሪዎች ውሳኔውን አልተቀበሉም።

መንገድ የዘጉ ወጣቶችImage copyrightDANIEL

ተቃውሞና መንገድ መዝጋት

በሰሜን ምዕራብ ዞን የማይ ሓንሰ ነዋሪዎች፡መንገድ በመዝጋት ተቃውሞ ማሰማት ከጀመሩ 11 ቀናት አልፎባቸዋል።

ነዋሪዎቹ የዞኑ አተዳዳር እና የፀጥታ አካላት ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም የሚሉ ሲሆን ጥያቄያቸው ከክልሉ መንግሥት መልስ እስካላገኘ ድረስ ወደ ቤታቸው እንደማይመለሱ ይናገራሉ።

የማይ ሓንሰ ነዋሪ የሆኑት አቶ አብርሃለይ ገብረእየሱስ “የወረዳው አስተዳዳሪዎች ለራሳቸው ወደ ሽረ እንዲቀርባቸው ክሳድ ጋባ ወረዳው ትሁን አሉ። ህዝቡ ደግሞ የተሰጠንን ወረዳ የመሆን መብት ለምን እንከለከላለን በማለት ነው የተቃውሞ ሰልፍ እያካሄደ ያለው” በማለት ገልፀዋል።

ሌላኛዋ የማይሓንሰ ነዋሪ ወይዘሮ ለተብርሐን ደግሞ “ውሳኔው በጉቦ እና በሙስና በድብብቆሽ የተደረገ ነገር ነው” በሚል ነዋሪው ለተቃውሞ እንደተነሳ ይጠቅሳሉ።

የኮሮናቫይረስ ወረረሽኝ ባለበት በዚህ ወቅት ለተቃውሞ መውጣታቸውን በሚመለከትም ሲናገሩ “ሕዝቡ ስለተቸገረ እንጂ ወዶ አይደለም። ሞትም ቢሆን እንሙት። ፍትህ ማጣትም ሞት ነው፤ በኮሮና መሞትም ሞት ነው” ብለዋል።

የአስገደ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብቶም አበራ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የአካባቢው ወጣቶች ለሰባት ቀናት ያህል መንገድ ዘግተው ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል።

• ምዕራብ ኦሮሚያ፡ ለልጃቸው ስንቅ ለማድረስ ወጥተው አስከሬኑን መንገድ ላይ ያገኙት እናት እሮሮ

• በሞት የተቋጨው የልደት በዓል

“የወረዳው ምክር ቤት የወሰነውን የማይቀበሉ ከሆነ የክልሉን ኃላፊዎች ማነጋገር እንዳለባቸው ገልጸንላቸዋል። ቢሆንም ኃላፊዎች መጥተው ካላናገሩን እኛ ወደ ክልል አንሄድም ብለዋል” ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው አስረድተዋል።

የወረዳው አስተዳደር የአገር ሽማግሌና የሐይማኖት መሪዎች በማነጋገር፤ ወጣቶቹ በሰላማዊ መንገድ እንዲግባቡ ለማድረግ እየጣሩ መሆኑንም አክለዋል።

“ጥያቄያቸው በሰላማዊ እና ዲሞክራስያዊ መንገድ ለሚመለከተው አካል እንዲያቀርቡ እየሰራን ነው” የሚሉት አቶ ሃብቶም፡ መንገድ መዝጋት ግን ህጋዊ እንዳልሆነ እና ይህም ለህዝቡ በግልፅ እንዲነገረው ተደርጓል በማለት ስለሁኔታው አስረድቷል።

የአክሱም ዩኒቨርሲቲው መምህር ዳንኤል ዘሚካኤል,, ዪኒቨርሰቲው በተለያዩ ዞኖች በህብረተሰብ የኮሮናቫይረስ ግንዛቤ እንዲኖር እየሰራው ባለው ስራ በቡድን ወደ ምዕራባዊ ዞን ከላካቸው አንዱ ነው።

ዘጠኝ በመሆንም ወደ ምዕራባዊ ዞን በማይ ሓንሰ ሲጓዙ በዛ ማለፍ እንደማይቻል፣ በማይ ሓመንሰ ነዋሪዎች እንደተነገራቸው እና ይህን ብቻ ሳይሆን ወደ መጡበት አካባቢ እንዳይመለሱም ከቡድኑ እና መኪኖቻቸው ጋር በአካባቢው ነዋሪዎች እንዲታገቱ መሆናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በማይ ሓንሰ ወደ 30 መኪኖች ታግተው እንደነበረ እና ሌሎቸ አምልጠው በመውጣት አሁን 18 እንደቀሩ የሚናገረው መምህር ዳንኤል፣ ህዝቡ 24 ሰዓታት ተሰባስቦ እንደሚውል እና እንደሚያድር ይናገራሉ።

ለሊት በአስፋልቱ ዳር ዱንኳን ጥለው ከ 200 እስከ 300 ሰዎች አንድ ዱንኳን ላይ እንደሚያድሩ እና ይህም ለህዝቡ ጤና አደገኛ እንደሆነ ይናገራሉ።

በህብተረሰብ የኮሮናቫይረስ ግንዛቤ ለመፍጠር ተጉዘው በመንገዳቸው እንዳያልፉ እና እንዳይመለሱ የተደረጉት እነ አቶ ዳንኤል እና ባለደረቦቻቸው በማይ ሓንሰ ለሶስት ቀናት እንዲቆዩ ተገደዋል።

ለሶስት ቀናት በመኪናቸው እያደሩ፣ ህዝቡ ለበሽታው ያለውን ግንዛቤ እንደተረዱ ስለ ኮሮናቫይረስ የቀረፅዋቸውን የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶችን ማስደመጥ መጀመራቸውን ይናገራሉ።

“ቢሆንም እንድናጠፋው ተነገረን። ለሌላ አካባቢ ይዘነው የሄድነው መፀዳጃ አልኮል ለአካባቢው የጤና ሃላፊ ብንሰጥም ተወሰነ ለህዝቡ መስጠት በቢሮው ነው የቆለፈው። ህዝቡ ቀን ላይ ሲሰበሰብ እና ሲመክር ይውልና፤ ለሊት በጋራ ሲጨፍር ነው የሚያድረው” ይህ ቦታም አስጊ ነው በማለት ፍራቻቸውን ይገልጻሉ።

በማይ ሓንሰ ከታገቱት ከባባድ መኪኖች መካከል፣ ከጂቡቲ የመጡ 5 ሹፌሮች እንዳሉ እና ሙቀታችን ተለክተናል በማለት ብዙ ሰዎች ጋር መነካካት እንደነበራቸው ይናገራሉ።

የማይ ሓንሰ ነዋሪዎች ባንክ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች አግልገሎት እንዳይሰጡ በግዴታ እንዲዘጉ ስለተደረጉ ቆይታቸው ከባድ እንደነበረ ይገልፃሉ።

• የዓይን እማኞች በመቀለ በፀጥታ ኃይሎች ስለተገደለው ወጣት ምን ይላሉ?

• ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅ የሚያስችሉ ቀላል ተግባራዊ ስልቶች

የማይ ሓንሰ ነዋሪዎች ግን የዞን አስተዳደር እና ፖሊስ ጥያቄያቸውን ከመስማት ይልቅ እኛ ያልናችሁ ስሙ በማለት መፍትሄ እንዳልሰጣቸው ይገልፃሉ። የዞኑ ፖሊስም፡ ለአካባቢው ሚሊሻዎችም መንገድ በመዝጋት ተቃውሞ እያሰማ ያለውን ሕዝብ በመበተን መንገዱ እንደከፍቱ አልያም ሚልሻዎቹ ትጥቃቸው እንዲፈቱ ጫና በመፍጠር ላይ እንደሚገኝ ገልፀውልናል።

ወይዘሮ ለተብርሃን “ሚሊሻዎቹ፡ እኛ የህዝብ ነን፤ እናንተ አላስታጠቃችኑም። ህዝብ ያለን እንጂ እናንተ ያለቹን አንሰመማም። ከፈለጋቹ ወደ ህዝቡ ቅረቡ እና እንረዳዳ ሲሉዋቸው ግዜ፡ በሉ ፈርሙ ሲሉዋቸው ህዝቡ ይህን ስለአወቀ ውጡልን በማለት አባረርናቸው” በማለት በሚሊሻዎቹ እየተፈጠረ ያለውን ጫና ገልፀውልናል።

በማይ ሓንሰ ሚሊሻ የሆነት አቶ ገብረክርስቶስ ገብረኣረጋዊም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ተሰባስቦ ተቃውሞ ማሰማት ጥሩ እንዳልሆነ ሕዝቡን ለማስረዳት እንደሞከሩ ገልጸው “የዞኑ አስተዳዳሪዎች ከኮሮና የሚብሱ እንጂ የሚሻሉ አይደሉም” በማለት ሰሚ አለማግኘታቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

“የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝቡን የማትበትኑ ከሆነ ትጥቃችሁን እንድትፈቱ ብሎናል። እኛም ከእናንተ ጋር ትውውቅ የለንም ሕዝቡ ነው ያስታጠቀን፤ ሕዝብ ትጥቃች እንድትፈቱ ካለን እንፈታለን። ካልሆነ ግን ለእናንተ ብለን ትጥቅ አንፈታም ብለናቸዋል” በማለት ህዝቡ እያነሳ ያለው ጥያቄ ትክክል እንደሆነ ይናገራሉ።

ወጀራት

በተመሳሳይ ሁኔታ በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ወጀራትና ሕንጣሎ የተባሉ ከዚህ ቀደም አንድ የነበሩ፤ አሁን ግን ለሁለት የተከፈሉ ወረዳዎች አሉ። በወጀራት ወረዳ ከሚገኙት ባሕሪ ሓጸይ እና ዓዲ ቀይሕ የተባሉ ቦታዎች መካከል የወረዳ ማዕከል መሆን ያለበት ባህረሀፀይ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ጥያቄ አቅርበዋል።

የአረናው አባል አቶ አንዶም እንደሚሉት የወረዳነት ጥያቄ የተነሳበት የወጀራት ሕዝባዊ ተቃውሞ አራተኛ ቀኑን ይዟል። እዚህም አካባቢውን የሚያስተዳድሩት ‘የዞን እና የክልል መልዕክተኞች ናቸው እንጅ እኛን አይወክሉንም’ በሚለው ቅሬታ የተቃውሞው አካል ሆኗል ይላሉ። “ጥያቄው [ወረዳነት] ተፈቅዶልን እያለ፤ እንደገና ተከልክለናል የሚል ነው።”

የቀድሞው የወጀራት ወረዳ ማዕከል የነበረችው ጣቢያ ባሕሪ ሓፀይ ነዋሪዎቿ፤ ባሕሪ ሓፀይ የወረዳው ማዕከል ስለነበረች ከጣቢያ ዓዲ ቀይሕ ጋር መወዳደር የለባትም በማለት ይጠይቃሉ።

ይሁን እንጂ የወጀራት ምክር ቤት የወረዳዋ ማዕከል ማን ትሁን? በሚል ውሳኔ እንዳላሳለፈ የወረዳው አስተዳደር አቶ ዳርጌ ፀጋይ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በጣብያ ባሕሪ ሓፀይ ሰላዊ ሰልፍ ከማካሄድ ጥያቄ ከማቅረብ ውጪ በወጣቶቹ ላይ የተወሰደ እርምጃ እንደሌለ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

“ወጣቶቹ ሥርዓት ያላቸው ናቸው። እስከአሁንም በአካባቢው የደረሰ ችግር የለም። አሁን ከእነሱ ጋር ንግግር ጀምረናል። መንግሥት ጥያቄያችንን ሰምቶ የቀድሞ ወረዳችን ይመልስልን ነው የሚሉት” ብለዋል።

የወረዳው ምክር ቤት የትኛው ወረዳ ማዕከል እንደሚሆን ውሳኔውን ባያስተላልፍም፤ የባህረሀፀይ ነዋሪዎች ከዚህ በፊት የወረዳው ማዕከል ስለነበርን ከሌሎች ጋር መወዳደር አንፈልግም ብለዋል።

በክልሉ መዲና መቀለ ከሳምንት በፊት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት የወጣውን ደንብ ተላልፈዋል ከተባሉ ወጣቶች ጋር በተከሰተ አለመግባባት የአንድ ሰው ህይወት መጥፋቱ እታወሳል።

አቶ አንዶም እንደሚሉት በጸጥታ ኃይል አባላት በተተኮሰ ጥይት ከሞተው ወጣት በተጨማሪ ሁለት ሰዎች ከቆሰሉ በኋላ “በአካካቢ ባሉት 05፣ 06 በሚባሉ ቀበሌዎችና አይደር የሚባለ ሠፈር ተቃውሞዎች ተቀስቅሰው ነበር” ብለዋል።

 

Exit mobile version