ፕላኑ እንዲህ ነው። ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚባሉ የህወሓት ተቃዋሚዎች ይለያሉ።
“የዐብይ አሕመድ መንግስት በሰብአዊ መብት ጥሰት ሰበብ የትግራይ ክልል መንግስትን በመወንጀል በክልላችን ጣልቃ ገብቶ ሊቆጣጠረን ስለፈለገ የህወሓት ተቃዋሚዎችን ለመግደል ፕላን አለው”
ተብሎ በሰፊው እንዲሰራጭ፣ እንዲነገርና እንዲፃፍ ይደረጋል።
“ዐብይ እኛን ለማስወንጀልና ለመከፋፈል ፈልጎ የኛን ተቃዋሚዎች ለመግደል አቅዷል”
እየተባለ ፕሮፓጋንዳ ይሰራል።
ህወሓት ተቃዋሚዎቿን ትገድላለች።
ራሷ ገድላ “ይሄው ያልነው አልቀረም፤ እኛን ለማስወንጀል ዐብይ አስገዳላቸው” ይባላል።
ከዛ ህዝብን ለመቀስቀስና ተቃውሞን ለማስቆም ይረዳታል።
ከነሱ ያገኘሁት ነው። በደሕንነት ክፍሉ ተወያይተውበት ለበላይ አካል ተልኳል።
ከትግራይ ክልል እንድወጣም ተነግሮኛል። ግን አልወጣም!
ህወሓት አብርሃ ደስታ “በሌላ አካል ሊገደል ይችላል” ብላ ካሰበች ጋርድ ቀጥራ ትጠብቀኝ። ካልሆነ ግን ከህወሓት ውጭ ማንም አይገድለኝም!
አብርሀ ደስታ