የኢትዮጵያውያንመረዳጃማህበርበኮሎኝናአካባቢው
Hilfsverein der Äthiopischen Gemeinschaft in Köln und Umgebung e.V
በታላቁ የዐባይ ሕዳሴ ግድብ፣ የመንግሥትንና የሕዝብን አቋም እንደግፋለን
በዓለም ውስጥ በርዝማኔ የአንደኝነቱን ደረጃየያዘው ነጭ ዐባይ፣ በተለይ ደግሞ 86% የሚሆነውን የውሃ አስተዋጽዖ የሚያደርገውና ለምአፈር በማጋዝ ለሱዳንና ግብፅ ታላቅ ሲሣይ ሆኖ እጅግ ሲጠቅማቸው የኖረው ጥቁር ዐባይመሆኑ እሙን ነው። ይህ አመንጪዋን ሀገር ኢትዮጵያን በመጉዳት የታችኞቹን የተፋሰሱ ሃገራት ሲያደልብየኖረው፣ በቅዱሱ መጽሐፍ ገነትን ከሚያጠጡ ፫ ወንዞች መካከል አንደኛው
መሆኑ የሚነገርለት ዐባይ፣ ፈለገ ግዮን በመባልምይታወቃል።
በፈርዖኖች ዘመን የጥንት ግብፃውያን ጥቁር ዐባይ የሚመነጭባትን ኢትዮጵያን «የፈጣሪ ማደሪያ» እያሉ ነበረ የሚያወሷት። የሕይወት መሠረትየሆነው ውሃ በገፍ እየመነጨ ግብፅን በመታደጉ ጥንታውያኑ ኑዋሪዎቿ፣ የውሃው ምንጭ መገኛ የሆነችውን ሀገር «የፈጣሪ ማደሪያ» ብለው መጥራታቸው፣ ገለታቢሶች እንዳልነበሩ ይጠቁማል ማለትይቻላል። ይሁንና በዓለም ታሪክ ውስጥ ከ 19 ኛውክፍለ ዘመን ወዲህ ይሉኝታን ያጠፋ ሁኔታ ሳይከሰት አልቀረም። የአፍሪቃ ክፍለ ዓለም በአውሮፓውያን ቅኝገዥዎች ሥር የወደቀበት ያ ክፉ ዘመን፣ ጉልበት እንጂ ፍትሕ እንደማይበጅ
የተሣሣተ ምልከታን አስጨብጦ ይመስላል ያለፈው። የአፍሪቃ አህጉር(አገሮች) ከቅኝ አገዛዝ ነጻከወጡ በኋላም ቢሆን፣ በአንዳንድየክፍለ ዓለሙ ሃገራት ዘንድ የቀድሞ ቅኝ ገዥዎች መርሕ፣ እንደ ትክክለኛ አሠራርም ሆነ ደንብ የተወሰደ ይመስላል።
በዘመናችን፣ ይህንአመለካከት ከሚያንጸባርቁ ሃገራት መካከል አንዷ፣ እ.ጎ.አ. የካቲት28 ቀን1922 ዓ ም ከብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ነጻየወጣችው ግብፅናት።ግብፅ፣ በ
1929 ዓ ም ከብሪታንያ ጋር፣ በ1959 ደግሞ ከሱዳን ጋር የጥቁር ዐባይን ውሃ መንጪዋን
ኢትዮጵያንም ሆነ የነጭ ዐባይንተፋሰስ አገሮች ሳታነጋግር፣ ውሃው የሁለቱ አገሮች ብቻ እንደሆነ አስመስለው ውልመፈራረማቸውየሚታወስነው።
ኢትዮጵያ፣ ጥቁር ዐባይ እርሷን እየጎዳ የታችኛውን ተፋሰስ አገሮች ግን የቱን ያህል እንደጠቀማቸው ብታውቅም፣ ዐቅም በማጣት ለብዙ ዘመናትየበይተመልካች ሆና መቆየቷ የማይታበል ሐቅ ነው።
ሆኖም፣ ጊዜው ሲደርስ፣ የሕዝቧንም ቁጥር እጅግመናር አገናዝባ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት፣ ልማቷን ለማፋጣን፣ ድህነትን በሰፊውለመቅረፍ ዋና መፍትሔ አድርጋ የተመካችው በሕዳሴው ግድብ ላይ ሆኗል።ከአሥር ዓመትገደማ በፊት መገንባት የጀመረው ግድብ አሁን በመገባደድ ላይሲሆን የውሃ ሙሌቱ በሀምሌ ወር ይጀመራል ተብሎ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በታላቅ ጉጉት በመጠበቅ ላይነው።
ኢትዮጵያ፣ ከግዛቷ የሚመነጨውን ውሃ ለልማት ማዋል የተፈጥሮ መብቷ ቢሆንም፣ የታችኛው የዐባይ ወንዝ ተፋሰስ ሃገራት እንዲያውቁት፣ ሁሉም ፍትሓዊ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ፣ ከ፭ ዓመት በፊት በጋራ፣ በሱዳን መዲና በካርቱም፣ የሦስቱ ሃገራት፣ማለትም የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ መሪዎች ታሪካዊ የተባለለትን፣መሠረታዊ የፍትሐዊ ተጠቃሚነት የመርሕ ሰነድ መፈረማቸው የሚታወስ ነው።
ይሁን እንጂግብፅ፣ ከኢትዮጵያና ሱዳን ባፈነገጠ መልኩ የሕዳሴው ግድብ ሥራ እንዲስተጓጎል ውሃውም፣ ያለኔ ወይም ያለ ሦስታችን ፈቃድና ስምምነትእንዳይሞላ በማለት የዲፕሎማቲክ ዘመቻ ስታጧጡፍ ከመክረሟም በላይ፣ ወታደራዊ ዛቻ ጭምር እስከማሰማት መድረሷየሚታበል አይደለም።
ግብፅ፣ የዐረብ መንግሥታትን ማሕበር ብቻ ሳይሆን፣ የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር፣ እንዲሁም የታወቁ «ዓለም አቀፍ» የገንዘብ ተቋማት በኢትዮጵያላይ ጫናእንዲያሳርፉ ያደረገችው ውትወታ የመተግበሩ ምልክት እየታዬነው። በዓለም ዙሪያ፣ የገለልተኛ መንግሥታት ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪቃ ሕብረትና የዐባይ ተፋሰስ ሃገራት ፍትሓዊ የአቋምጽናትየሚጠበቅቢሆንም፣ውዝግቡን በድል አድራጊነት ለመወጣት፣ ከኢትዮጵያ በኩልየሚፈለገው፣ ሉዓላዊነትን አስከብሮ በነጻነት ጽኑ አቋምንና ብልሃትን የሙጥኝ ብሎ የሚንቅሳቀስ የመንግሥት አመራርና የሕዝብ አንድነት ነው። ይህደግሞበሀገር ወስጥና በውጭ ሀገራትየሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን ዜጎችንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ
ይመለከታል።
ስለሆነም፣ እኛ በጀርመን ሀገርየምንገኝ፧ በኮሎኝና አካባቢዋ የኢትዮጵያውያን ማሕበር አባላት የኢትዮጵያን ተፈጥሮአዊናታሪካዊ መብት መንስዔ በማድርግ፣ የሕዳሴው ዓላማና ተግባር፣ በታቀደው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር ይደረግ ዘንድድጋፋችንን ስንገልጽ ተከታዮቹን ምክረ ሐሳቦች ጭምር በማቅረብነው።
1. ኢትዮጵያ፣ ሉዓላዊነቷን በማስከበር ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ መብቷን በመጠቀም የሕዳሴውን ግድብየውሃ ሙሌት ታካኺድ ዘንድ ሙሉ ድጋፋችንን እንገልጻለን።
2. የሕዝባችን ኑሮና ዕድገት እንዲቀየርና ይበልጥ እንዲሻሻል አጥብቀን የምንሻ ሲሆን፣ይህን ለማን ብርሃን፣ ረሃብን በበቂ የእኽል ምርት በመለወጥ፣ መሠረታዊ የሕዝብን በልማት ተጠቃሚ የመሆን ፍላጎት ለማርካት ኢትዮጵያየያዘችውን እቅድ ተፃራሪ የሆነውን የግብፅን ጭፍን አቋም በጥብቅ እንቃወማለን።
3. ኢትዮጵያ፣ በታሪኳ ነጻነቷን አስከብራ የኖረችው በመሪዎቿ ጽኑ አቋምና በሕዝቧ ጸረ ባዕዳዊ አገዛዝ በመሆኑ፣ በአድዋው ዘመቻና ድል እንደታዬውሁሉየሕዝብን የልብ ትርታ በማዳመጥ፣ መንግሥት ሕዝቡን «በድየኻለሁወይ?» ብሎመጠየቅና በአግባብ የተከፋውን ይቅርታ ጠይቆ፣ የተበደለውን ክሶ፣ ከጎኑ ሊያሰልፈውይገባል እንላለን።
4. ከሁለት ዓመት በፊት የተከሰተው አስደማሚ የለውጥ ኺደት አቅጣጫውን ሳይስት፣ ፍትሕ ርትእና ሰላም እንዲሠፍን፣ የዴሞክራሲ ተቋማት በቋሚነት እንዲደራጁ፣ እኩልነትንና ሕዝባዊ አንድነትን የተጎናጸፈ ማሕበረሰብ እንዲገነባ ለዚህም ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲታይ እንጠይቃለን። ቀጣይነቱም እንዲረጋገጥእናበረታታለን።
5. በሕዝብ ዘንድ በታወቁ ግለሰቦችና በተለያዩ ብሔር–ብሔረሰብ አባላት ላይ፣ በጋጠወጥም ሆነ ጽንፈኛ ኃይሎች የሚፈጸም ማፈናቀልን፣ ግድያንና ንብረትማውደምን፣ መንግሥት በጽናት በመቆም፣ ወንጀለኞችን በሕግ ተጠያቂያደርግ ዘንድ እንጠይቃለን። የተገደሉ ሰዎች ሁኔታ በሚገባ እንዲጣራ፣ የታገቱ ተማሪዎችም ጉዳይችላሳይባል ትኩረት ተሰጥቶት እንዲለቀቁ ጥረት ይደረግ ዘንድ እንጠይቃለን።
6. በመዲናይቱ በአዲስ አበባ፣ በየጊዜው የሚከሠት የመሬት ቅርምትና የአንድን ወገን ተወላጆች ብቻ ለመጥቀም በማዘጋጃ ቤትበኩል ኢፍትኀዊ ድርጊት ይፈጸማል የተባለበት ቅሬታም ሆነ ክስ ተጣርቶ ፍትሓዊ እርምጃ እንዲወሰድ፣ ለሥራ ፍለጋምየሙያ ምሥክር ወረቀትና ብቃት ሳይሆን የብሔር ማንነት ቅድሚያ ይሰጠዋል መባሉ በሚገባተጣርቶ ይስተካከል ዘንድ ለማሳሰብ እንወዳለን።
7. በዓለም ዙሪያ፣ በኢትዮጵያም ጭምር ያጋጠመውን እጅግ አደገኛ የሆነውን የሳንባ ቆልፍ ተኀዋሲ ወረርሽኝ (Corona Virus Pandemic) መንስዔ በማድረግ፣ ምርጫ ቦርድ ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ ም ቀጠሮ ተይዞለትየነበረውን አጠቃላይ ምርጫ ማከናወን እንደማይቻል ካሳወቀ በኋላ ወደፊት እንዲገፋ መንግሥትና አብዛኞቹ የተቃውሞ ድርጅቶችእንዲሁም ህዝቡ የደገፈውን የመንግሥት ውሳኔ፣ እኛም ትክክለኛ ድርጊት መሆኑንእንደተቀበልን ማሳወቅ እንሻለን።
8. ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ ም፣ አዲስ አበባ ውስጥ በታዋቂው የኦሮምኛ አቀንቃኝ፣ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ላይ ግድያመፈጸሙን በጥብቅ እናወግዛለን። የተሰማንን ሐዘንም እየገለጽን፣ ለዚህ ዕውቅ የኪነ ጥበብ ሰው ቤተሰብ፣ቤተዘመድ፣ ወዳጆችና የሙዚቃው አፍቃሪዎች ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን። ግድያው ከተፈጸመበኋላ በአርሲና ሐረርጌ ውስጥ፣ በተለያዩ ቦታዎች፣ ከወንጀል ድርጊቱ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት በሌላቸው፣ በአመዛኙ የአማራና ጉራጌ ነገድ ተወላጆች እንዲሁም የኦርቶዶክስተዋሕዶ
ሃይማኖት ተከታዮች በሆኑዜጎች ላይ የተፈጸሙ አረመኔያዊ ግድያዎችን አጥብቀን እናወግዛለን።
ሕሊናቸው በጥላቻ ከታወረ ጥፋት አድራሺዎች አንፃር፣የግድያ ዒላማ የተደረጉ ጎረቤቶቻቸውን በመደበቅ የታደጉ ኦሮሞዎችን ጥረት እያደነቅን፣ ይህ ሰብአዊ ርኅራኄና ኢትዮጵያዊጨዋነት ምንጊዜም ጸንቶ መቀጠል ያለበት እሴት ነውእንላለን።
በ ሕ ወ ሓ ት መራሹ የአገዛዝ ሥርዓት አበረታችነት፣ ባለፉት30 ዓመታት ገደማ፣ በአንድ ነገድ ላይ ሲሰበክ የነበረ ጭፍን የዘረኞች የሐሰት ትርክት፣ ትውልድን የበከለ በመሆኑ፣ መንግሥት ዐቢይትኩረት በመስጠት፣ በት/ቤቶች የሚሰጥ የታሪክ ትምህርት በእርምት እንዲስተካከል ያደርግ ዘንድ እንጠይቃለን።
«የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ» እንደተባለው፣ የቆዬ ታሪክ ማስታወሻ የሆኑ የሐውልት ቅርሶችን በአገር ውስጥና በውጭም ሀገር የማውደም ዘመቻ፣ አስነዋሪ ተግባርና ወንጀልምመሆኑን በማስገንዘብ፣ ይህን ዓይነቱን እንቅሥቃሴ፣ በሕግአስከባሪዎችና ሕብረተሰብ ትብብር መግታት ይገባል እንላለን።
9. በትውልድ ሀገራችን በኢትዮጵያ ትርምስ እንዲፈጠር፣ ጊዜ ጠብቀው፣ ከጠላት ጎን በመሰለፍ የባንዳነት ሥራ የሠሩትን ኃይሎች እያወገዝን «ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር» ነውና መላው ኢትዮጵያ Ωዝብ፣ በውጭሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምጭምር የተጠቀሱትን የጥፋትኃይሎች በማጋለጥና በመታገል የሀገርወዳድነት ድርሻቸውን ያበረክቱ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።
10. ማንም ኢትዮጵያዊ፣ በዜግነቱ ሳይከፋ፣ ሳያኮርፍ፤ በእኩልነት፣ በወንድማማችነትና ፍቅር ተሣሥሮና ተከባብሮ በአንድነትከተሰለፈ፣ በሀገራችን ላይ እኩይ ዓላማ አንግቦ የሚነሣ ማንኛውም ምድራዊ ኃይል፣ ራሱይጠፋ እንደሁ እንጂ ኢትዮጵያ እንደማትጠፋ እናምናለን።
ድልለኢትዮጵያ ሕዝብ!
ኢትዮጵያ በነጻነትና ክብር ለዘለዓለምትኑር!
Allerweltshaus, Koerner Str. 77, 50823 Koeln 1