በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ጉሊሶ ወረዳ፣ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተፈጸመ ግድያ ዋና አላማ ያማራ ዘር ያላቸውን ሰዎች ያተኮረ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ሀቅ መሆኑ እየታወቀ በደፈናው በዜጎች ላይ የተፈፀመ በማለት መሸፋፈኑ መፍትሄ ሊሆን አይችልም፡ በተጻራሪው የዘር ተኮር የመጨፍጨፍ እኩይ ተግባር ለሚፈጽሙት ወንጀለኞች ወንጀላቸውን እንደተራ ወንጅል የሚያሳንስ ስለሆን መንግስት ዶማን ዶም ማለት መጀመር አለበት። ዶማ መሆኑ እየታወቀ ዶማ የሚመስል ማለት ዶማ አይደለም እንደማልት ይሆናልና።
በጋዋ ቃንቃ መንደር የተደረገውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ የተለመደውን የመንግስት “እርምጃ ይወሰዳል” አባባል ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የሰማናው ለንዴት ማብረጃ ያህል ከመሆን አልፎ ምንም ለዘለቄታ የፈየደው ነገር እንደሌለ ተመሳሳይ አሰቃቂ ድርጊት በተመሳሳይ አሸባሪዎች ሲፈጸም ማስተዋሉ በቂ ነው።
ለመሆኑ ርዳታ ለጠየቁ ዜጎች የጋዋ ቃንቃ አስተዳዳሪ በምጸት “ለምን ያርዷችኋል፡ አይበሏችሁ” በሎ በማፌዝ መልስ መስጠቱ እንደተራ ነገር ታይቶ የሚቀር ሳይሆን በቂ ምርመራን ርምጃ በገዋ ቃንቃ አስተዳዳሪ ላይ ተወስዶ ማየትና ወደፊትም በስተዳዳሪነት ላይ የተቀመጡ ከዚህ መሰለ ሃላፊት የጎደለው ተግባር እንዲታቀቡ ያስፈለጋል። ከዚህ በፊት በጉምዝ የተፈጸመውና በጋው ቃንቃ የተፈጸመው ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በኗሪዎች ለባለስልጣኖች በቅድሚያ ቢነገርም በሁለትም ስፍራዎች በችልተኝነት ወይም ከጭፍጫፊዎች ጋር በነበራቸው ግንኙነት ምክንያት የመጀመሪያው ምክንያት አሰፈላጊ ወይም በቂ ርምጃና ማስተካክያ ባለመወስዱ ሌላ አስቃቂ ድርጊት ተደገመ።
በቦታው የቆየውን ወታደራዊ እዝ ካምፑን ዘግቶ እንዲሄድ ማን አዘዘው፣ ለምንስ የተረጋጋ ሁኔታ በሌለበት ጦሩ ኢንዲለቅ ታዘዘ። ከጦሩ ውስጥ ይህንን ሁኔታ ከኦነግ ሸኔ ጋር ቅንብር የፈጠሩስ ይኖሩ ይሆን? ጦሩ በለቀቀ በስዓታት ውስጥ የኦንግ ሽኔ የነፍሰገዳዮች ስብስብ ወደ ጋዋ ቃንቃ በመጋባት የዘር ማጥፋት ዘመቻውን ለመፈጸም ቅድመ ዝግጅት እንደነበረውና ቢያንስ ከጦሩ ከቦታ መነሳት ጋር የተቃነባበረ አካሄድ ያለው ለመሆኑ ለመጠርጠር የሚያበቃ ሰፊ ክፍተት ይታያል።
በዚህ ላይ በአደባባይ በተዳጋጋሚ የአማራን ዘር ለማጥፋት በክፍተኛ ፍጥነት የሟቾች ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑ ግልጽ ሆኖ እያለ በወጥመዳቸው እንዳንገባ በሚል አጉል ፈሊጥ ሲባዛ ትርጉም ያጣና እጅ ሰጥቶ ከመሞት እየተከላከሉ መሞት የመዳንም እድል ስለሚፈጥር፡ ህዝብ በመንግስት ላይ ተስፋ ቆርጦ የራሱን ውሳኔ ከመውስዱ በፊት: ምክንያት መደርደር ቀንሶ ተጨባጭ ርምጃ በመውሰድ የህዝብን አመኔታን ማጎልበት የግድ ንው።
መንግስትና በመንግስት ዙሪያ ያሉ ሁሉ አስቃቂ ግድያዎችንና የሀገርን ሰላም የሚነሱ፡ ርስ በርስ እንድንጋጭ በሂደቱም ከቻሉ ሰልጣን ኮርቻ ላይ ለመውጣት የጀመሩት ሀገር የመግደል ዘመቻቸውን በመንግስትነት ስም ካልሆነም ያለ የሌለ ሃይላቸውን የውጭም እጅ ጨመረው ሀገራችንን ለማፍረስ የሚሰሩ የተለያዩ ቡድኖች እንዳሉና ያለምታከት የሰሩ መሆኑ ነገረውናል። ሆኖም ግን ከሃገሪቱ ጥላቶች ዝግጁነት አንጻር ቢያንስ በግልጽ ህዝብን አሳታፊ በሆነ መልክ ተጨባጭ ስራ እየተሰራ ከሆነ ስለምሆኑ በሙሉ ልብነት መናገር ያስቸግራል ወይም ለህዝብ ግልጽ አይደልምና ይታሰብበት::
መንግስት በተዳጋጋሚ የተሰጥውን እድልና የህዝብ አመኔታ መጠቀም ካልቻለ ከደርግና ከህወአት ታሪክ መማር ይኖርበታል። ሁሉም በአንድ ወቅት የህዝብ አመኔታ አግኝተው ነበር። ነግር ግን የህዝቡን አመኔታ እንደ አላዋቂነት፡ እንደፍርሃት፡ እንደሽንፈትና ደጋፋችውን በዘላለማዊነት በመቁጠር መሰረት የሌለ የራስ መተማመን አጎልበተው ሿ ብለው መንበረ ስልጣናቸውን አጡ። ሁሉም ስልጣናችውን ያጡት እነሱ በመጡበት ሳይሆን በናቁታን በአላሰቡት መንግድ ንው።
በመጨረሻም ማለት የምንሻው፡፡ መንግስት በየቦታው ይሚታየው የሀገር ጠላቶች መራወጥ በትዕግስት ብቻ የሚወግድ ስላለሞሆኑ ሁሉም የሚሳማማ ይመስልኛል፡ ተዕግስት ደግሞ ሲበዛ ታጋሽዋን ታጣለችና መንግስት በአፋጣኝ የሚመለከታቸውን የህበረትሰብ ተወካዮችና ባለድርሻ አካላትን በማሰባሰብ ከሚድያ ፍጆታ ባለፈ እውነተኛ ምክክር ማድረግና በውጭም በሀገር ውስጥ የሚገኙትን ወገኖች ማሰልፍ ያሚይስችል የብሔራው መነሳስትን መፍጠርና ሀገርና ህዝብን ለመታደጋ ሲባል ማንኛውን አስፈላጊ ዝግጁነትን ማጠናከርና ህዝብን ለወሳኙ ሀገር አድን ጥሪ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር