Site icon Dinknesh Ethiopia

የኢትዮጵያ መንግስት ከህወሓት ወንጀለኞች ጋር ለድርድር አይቀመጥም – ደመቀ መኮንን

Demeke Mokonnen

አዲስ አበባ ህዳር 10 2013 (ኤፍ )

መንግስት ከህወሓት ወንጀለኞች ጋር ለድርድር እንደማይቀመጥ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

አቶ ደመቀ መኮንን ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አን ሊንዴ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ በውይይታቸው በዋናነት መንግስት በትግራይ ክልል እየወሰደ ባለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ትኩረት አድርገው መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አቶ ደመቀ መንግስት በትግራይ ክልል እየወሰደ ካለው ህግን የማስከበር እርምጃ ጋር ተያይዞም ሊኖር ስለሚችል ድርድር፣ በትግራይ ክልል ስላለው የመገናኛና የሃይል አቅርቦት እንዲሁም መንግስት እየወሰደ ካለው ህግን የማስከበር እርምጃ ጋር በተያያዘ ለተፈናቀሉና ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ስለሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ በተመለከተ ገለጸ አድርገዋል።

በማብራሪያቸውም የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ከህወሓት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማለሳለስ የሄደበትን ርቀት በተመለከተ ለሚኒስትሯ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

መንግስት ለህወሓት በአዲሱ የመንግስት መዋቅር ውስጥ እንዲሳተፍ የሰጠውን በቂ ጊዜና እድል ቡድኑ ሳይጠቀምበት መቅረቱንም ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ቡድኑ ከስልጣን ከተወገደበት ጊዜ ጀምሮ ህገ ወጥ አካሄዶችን በመከተልና ፅንፈኛ ቡድኖችን በማደራጀት፣ በማሰማራትና በገንዘብ በማገዝ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ሲያሰማራ መቆየቱንም አስረድተዋል።

ከዚህ ባለፈም ቡድኑ በህገ ወጥ መንገድ በማን አለብኝነት ክልላዊ ምርጫ ማካሄዱንም ጠቅሰዋል።

ቡድኑ በሰሜን እዝ የሰራዊት አባላት ላይ የፈጸመው ጥቃት መንግስት በጁንታው የህወሓት ቡድን ላይ እርምጃ እንዲወስድ እንዳስገደደው ጠቅሰው፥ መንግስት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድርድር እንዲደረግ ያቀረበውን ሃሳብ እንደሚያደንቅም አንስተዋል።

Source: https://www.maledatimes.com/

Exit mobile version