ከዚህ በታች ያሉትን መረጃዎች ከራያ ራዩማና ከጎዳዳ ፌስ ቡክ የተገኘ መሆኑ አንባብያን እውቅና ከምስጋና ጋር ይስጡልን፥፥ ወደፊት ለህዝብ መድረስ ያለባቸውን መልዕክቶች በ dinkinfo@dinkneshethiopia.com በትልኩልን በቀጥታ ይደርሰናል፥፥
Mohammed Kenya
ከአላማጣና አካባቢው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቆቦና ሌሎች ከተሞች እየገቡ ነው።
የሰብዓዊ ቀውሱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነው።
የመንግሥትን ትኩረት ይፈልጋል‼
Abuki Musa
በቆቦ ከተማ በተለያዩ ት/ቤቶች ተጠልለው የሚገኙ የራያ አላማጣ ዋጃና ጥሙጋ ተፈናቃዮች በምግብ እጥረት ምክኒያት ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች መጋለጣቸውን ገልፀዋል።
አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንዲደርግላቸውም ጠይቀዋል።
ከራያ አላማጣ ፤ ከሙኽኒ፤ ከኮረም ፤ ከዋጃ እና ከጥሙጋ ከሀያ ሺህ በላይ ነዋሪዎች የሕወሓትን ጥቃት በመሸሽ ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ገብተዋል ።
አብዛሀኛዎቹ ሕጻናት እና ሴቶች ሲሆኑ ወጣቶች እና ጎልማሶች በሕወሓት ታጣቂዎች እየተጋዙ የጉልበት አግልግሎት እየሰጡ መሆኑን እየተሰማ ነው።
Moha Mohammed is feeling sad.
ትኩረት ለራያና ለዓፋር ህዝብ የመንግስት ዝምታ እስከመቼ ነው!!
Moha Mohammed is feeling sad.
ትኩረት ለራያና ለዓፋር ህዝብ የመንግስት ዝምታ እስከመቼ ነው!!
Eyassu Berhie Chekole · በራያ ህዝብ ላይ በትህነግ የሚፈፀሙ ግፎች በትንሹ
1. የትህነግ ወታደሮች ህብረተሰቡን በቀንም በለሊት መዝረፍ ፣መድፈር ፣መግደል ፣ማሰር (የት እንደሚወሰዱ አይታወቅም)
2. በሓይል ወስን (ከቤት ወንድ ይሁን ሴት እስከ ሳስት ልጅ እንዲዘምቱ ማስገደድ) ፡ መዋጮ(ገበሬው እስከ አንድ ኩንታል ጤፍ እንዲሁም በብር 600-1500 ) አውጣ
3. ህብረተሰቡ የጤና ግልጋሎት አንዳያገኝ ማረግ በአሁኑ ሰዓት አዲስ ወረርሺኝ ተከስቷል ልክ ወባ አይነት ዝምድና ያለው ። በአሁኑ ሰዓት ሆስፔታሉ ስራ አቁሟል:: የሚወልዱ እናቶች ፡ የቆየ ህማም ( ስኳር ፡ ደም ግፊት ፡ HIV እና የልብ ህመምተኞች) መድኃኒት እጦት እየረገፉና እየተሰቃዩ ነው፡፡
4. የኑሮ ወድነቱ በርበሬ 1500 ፣ጨው 330 ፣ዘይት 5 ሌትር 1700፣ ሻማ 70፣ ሳሙና ላይፍ ቦይ 50፣ኪርቢት 25 ወዘተርፈ …
5. በፈለጉበት ሰዓት መብራትና ወሃ ማጥፋት ፡ ህብረተሰብን ወሃ እንዳያገኝ በተላላፊ በሽታ እንዲጠቃ ማድረግ
6.አከባቢው የጦር ቀጠና እንዲሆን ራያ ውስጥ በዶዘር የተቆፈረ ከባድ ምሽግ የተሰራባቸው አካባቢዎች ዝርዝር ፤ ጨርጨር፣ ባላ፣ ገደራ ጎቱ፣ ኩቢድርባ፣ ኅብረት፣ ህሞ( ማሩ)፣ ከረን ኩቤ ጣፌ፣ ጫማሮ፣ ቃርሶሌ፣፣ ታኦ፣ አዲስቅኝ፣ ባሶ፣ ኮስም፣ባንድራ፣ ጋውር ሻምተ፣ ገንዳ ጃላ፣ ጎልአጆ፣ ጋርጃለ እና ጠጠቻ ናቸው።
7.ከጋርጃለ እስከ ፋጫ ሃራ በዶዘር የተሰራው ምሽግ ስፋቱ መኪና ያስኬዳል። ዲማ፣ ቆጫ፣ቃጅማ፣ ኩትቸ፣ ስፍራ አሞራ፣ ዓዳቦ ጎልጃ፣ ጋራካሱ – ጽልያ በተጨማሪ ከባድ መሳሪያና መድፍ የጠመዱባቸው አካባቢዎች ናቸው።
8.ህዝቡ በድሮን እንዲጨፈጨፍ ከተማው (ሆቴል ፣ትምህርት ቤት ፣ ፔንሲዮን )ውስጥ ካምፕ ማድረግና አዛዦች ማረፍያ ማድረግ እንዲሁም ገበያ ላይ ያሉት መጋዘኖች የጦር መከማቻ ማድረግ እናም በድሮን ህዝቡ እንዲጨፈጨፍ በማድረግ ፕሮፕጋንዳ መስራት (ካሁን በፊት በገበያና በንግድ ቦታና ሆቴል ቤቶች የተደረገው የንፅሃን ጭፍጨፋ በድምፅ ወያኔ ለፕሮፕጋንዳ ሲያውሉት ተመልክተናል)