Dinknesh Ethiopia

የዳንጋላ ኦፕሬሽን እና ፋኖ የሰበረው የሾህ አጥር

Mengistu Musieመንግስቱ ሙሴ (ዶ/ር)

December 23, 2023

ከዳላስ ቴክሳስ

ድፍን 50 አመታት ተቆጥሯል። የትግራይን ሕዝብ ከአማራ ወንድሙ እና እህቱ ለማለያየት የተሰራው ሰይጣናዊ ስራ በተግባር ተተርጉሞ ሁለቱን በባህል፤ በቋንቋ መሰረት፤ በሐይማኖት እና ተውፊት የማይለያዩ እንዲለያዩ ከተደረገ። ይህን ለሽሆች አመታት ቅድስት ሐገራችንን እንድትቀጥል እና በአለም ላይ ለተገፉ አገራት በግፍ ተይዘው ቅኝ ለተገዙ ሕዝቦች ተምሳሌት የሆነችን ሐገር መስራች የሆኑ ሕዝቦችን ለያይተው ያዋጉ እና በሐገሪቱ የወደፊት ቀጣይነት ጥያቄ ውስጥ ያስገቡት በህወሓት ስር የተሰለፉ የትግራይ ልሂቃን ስህተት ነው ይበሉት ወይንም ሌላ ነገር ታቅዶ፤ ተጠንቶ እና ተሰልቶ የተሰራ ክፉ ስራ እነዚህ ሁለት ወንድማማቾች/እህታማች ሕዝባችን በመለያየት ሰርተዋል። በሽሆች አመታት የታሪክ ሰንሰለት የተጋመዱ ብዙ ክፉም ደግም አጋጥሟቸው ሁሉንም እንደአመጣቱ የተቀበሉ እና ክፉን በትግል የመከቱ የአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በአንድ ቆመው ታሪክን ሰርተው እስከ 1967 ዓም ህወሓት እስከተመሰረተችበት ግዜ ድረስ አብረው ኖረው የዘለቁ አንድ ህዝብ ነበሩ።

የነዚህ ወገኖች ታሪክም አፈታሪክ ሳይሆን በእውን አለም የተሰራ የ 3000 አመታት የታሪክ ሰንሰለት እና ገድል መሆኑን ከዘመነ ወያኔ በፊት የተደረሱ ታሪካዊ መዝገቦች ያሳያሉ። የታሪክ ተማራማሪወች ምሁራን፤ የቤተክህነት ጠቢባን ሁሉ የዘገቡት ሰንደው ያስቀመጡት ገሐድ እውነትም ነው። አንዱ የሌላው ውህድ አካል መሆኑን ተጋብቶ፤ ተዋልዶ ተዛምዶ በመኖሩ አስይቷል። በቋንቋ፤ በሓይማኖት፣ በባህል ታሪክን በማስቀጠልም ሆነ የጋራ ታሪክ በመስራት ወደር የለሽ ትስሥር ያለው ሕዝብም ነው/ነበርም።ከሁሉም በላይ የቀይ ባህርን መንገዱ አድርጎ የመጣ ሁሉ የውጭ ጠላት የመጀመሪያው መዳረሻው ትግራይ እንደሆነ ሁሉ አማራው; አፋሩ ሽናሻውና ኦሮሞው ጋሞው እና ጉራጌ ሳይቀር የወገኑን የጥቃት ገፈት ተካፋይ ሆኖ ዘለቋል።

የትግራይ፤ እና የአማራ ሊቃውንት የቤተክህነት ሰወች፤ የቆሎ ተማሪወች አንዱ ወደሌላው በመሄድ ከዘመነ ስልጣኔ እና የዘመናዊ ትምህርት ከመስፋፋቱ በፊት ትምህርትን ይጋሩ እንደነበር እስከቅርቡ ዘመንም ለሽሆች አመታት እንደቀጠሉ የምርምር ውጤት መፈለግ ሳያስፈልግ አሁን በህይወት ያሉ አባቶች ከተራ ቀሳውስት እስከ ዛሬው ብጹ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ የእውን ምስክሮች ናቸው።

አማራ እና ትግሬ እንደትውፊታቸው ሁሉ የስርአተ መንግስታቸውም መነሻ ከንግስተ ሳባ እና ከቀዳማዊ ሚኒሊክ ይመዘዛል። እስከ ቅርቡ ዘመን ህወሓት እስከፈጠረው ትውልድ ድረስ ትግራውያን የንግስተ ሳባ ማንነትን ከአክሱማዊት ስልጣኔ ጅማሮ ጋር በኩራት ያያይዙታል። ይህን ታሪክ አማሮች እና አፋሮች ይጋሩታል። ሁለቱ አማራ እና ትግራውያን ከኩሽ የተደባለቁ እና ሴማዊ ዝርያ እንዳላቸው ታሪካቸውም ያትታል ከደቡባዊ አረብያ ፈልሰው ከኩሻዊው ነባር ሕዝብ ጋር መቀየጣቸው የማይክዱት ታሪካቸው ነው።

ይህን ታሪካዊ ትስሥር በ 1960 ወቹ ከትግራይ ከተማሪወች ንቅናቄ በአፈነገጡ የትግራይ ተማሪወች ተመስርታ ከ 17 አመታት የትጥቅ ትግል በኋላ ለስልጣን የበቃችው ድርጅት (ህወሓት) አንዴ ስትክደው ሌላ ግዜ ስታወግዘው ለ50 አመታት ዘልቃለች። የዚህን ለሽህ አመታት የተዋለደ በባህል፤ በቋንቋ እና በሁለመናዊ ትውፊቱ የተጋመደውን ሕዝብ በጠላትነት በመፈረጅ የ 27 አመታቱን የስልጣን ዘመን በጥላቻ አሳልፈዋለች።

ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው እና እጅግ ዘግናኝ የሆነውን ጦርነት በአረመኔው አብይ አህመድ ኦነጋዊ መንግስት እና በህወሓት መካከል ሲጀመር። የህወሓት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አመራር ሂሳብ የምናወራርደው ከአማራ ልሂቃን (ሕዝብ) ጋር ነው በማለት ጦርነቱን ወደወሎ እና ጎንደር አሻግረውታል። በዚያም ብዙ ጉዳት እንዲደርስ ሁኗል። ይህን የተረዳው የአብይ አህመድ መንግስትም ያሰበው እና ያለመው ተሟልቶለት ሁለቱን ብቻ ሳይሆን የአፋርን ሕዝብ ጨምሮ ቁጥረ ብዙ የሆኑ ዜጎች ጭዳ የሆኑበትን ጦርነት አካሂዷል። የደረሰ መኽር ተቃጥሏል፤ የጋማ ከብቶች ተገድለዋል፤ ቤት ንብረት እና ተቋማት ፈራርሰዋል። ዛሬ ይህ ጦርነት ካለፈ በኋላ እና አረመኔው አብይ አህመድ በአማራ ላይ የጀኖሳይድ ጦርነት ካወጀ ወዲህ እንደምናየው የኦነጋዊ ሰራዊት በጎጃም መኸር ማቃጠል ሴቶችን መድፈር እና ተመሳሳይ ወንጀሎች መፈጸሙን ቀጥሎበታል። ይህ ማለት ህወሓትም ሆነ የአረመኔው አብይ ሰራዊት ለትግራይ፤ ለአማራ እና ለአፋር ሕዝባችን የሚራራ ልቦና አላቸው ለማለት የማያስደፍር መሆኑን በዚህ የአምስት አመት ጦርነቶች እያየን ነው። የአማራ፤ የትግራይ፤ እና የአፋር ሕዝብ ጦርነቱም ቢቆም እንኳን የፈረሱ መሰረተ ልማቶችንም ሆነ የወደሙ ማምረቻ ተቋማትን መልሶ ወደነበሩበት ለመውሰድ አመታት የሚፈልግ መሆኑን ጄማል የተባለው የዋሽንግተን ፖስት ካሜራማን አሳይቶናል።

ሌላው ዛሬ የሚያሳዝነው ለ2000 አመታት የቆመችውን የሁለቱ ሕዝባችን የእምነት ቤት የሆነችውን ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ሳይቀር በመለያየት ዛሬ ሁለቱ ሕዝባችን በአንድ ቤተ እምነት ጸሎት ማድረግን ተነፍገዋል። ይህን በተመለከተ የኦሮሞ ልሂቃን እጅግ የሚያስመሰግን ስራ አሳይተዋል። የአረመኔው የአብይ አህመድ መንግስት ወታደሮች እና ጽንፈኛው ኦነግ በቤተክርስቲያኗ ምእመናን እና አባቶች ላይ የሚፈጽመውን ወንጀል እንዳለ ሆኖ ቤተክርስቲያኗ እንዳትከፈል ግን የቻሉትን ማድረጋቸውን አሳይተውናል የአርተመኔውን የኦሮሚያ ቤተክህነት የመመስረት አላማ አክሽፈውታል። ይህ በህወሓት የተሰራው ሐገራችንን ያስቀጠለች ቤተክርስቲያንን የትግራይ የኢትዮጵያ ተብላ እንድትከፈል ያደረገው ሂደት በዚህ የነሱ ዘመን መሆኑ በእጅጉ አሳዛኝ እና ታሪክ የሚታዘበው ድርጊት ነው።

የኦነግ/ህወሓት ስርአተ መንግስት

ህወሓት ከኦነግ ጋር በመሆን በመሰረተችው ስርአትም ሆነ ሁለቱ ዘረኛ ድርጅቶች በጻፉት ህገመንግስት ውስጥ በ 3000 አመት የተገነባች ኢትዮጵያን የካደ እና በውስጧ የበቀሉ ቋንቋወችን አገር፤ ሕዝብ ብሔር ብሔረሰብ እያለ የሰየመ እና ለሽሆች አመታት በደም ፍሳሽ በአጥንት ክስካሽ የተገነባችውን ሐገር ኦነግ እና ህወሓት አፍርሰው የዘር ክልሎች በማዋቀር አማራውን በማግለል እስከዚህ ጦርነት ዘልቀዋል።

በአማራ እና የትግራይ ሕዝብ መካከል መቸውም ጠላትነት ኖሮ አያውቅም። ህወሓታውያን ልሂቃን ግን የሌለ ታሪክ በመደርደር የአማራን ሕዝብ በማግለል እና አጥቅተው በማስጠቃት ለ 27 አመታት ተግተው ሰርተዋል። እነመምህር ገብረ ኪዳን አይነቱ ልሂቃን ኢትዮጵያን የምጠላት በአማራ መኖር ነው እስኪሉ እና ይህን ነውራቸውን በአደባባይ በመግለጽ አሰምተውናል። አማራን ለመጉዳት በሚል መንፈስ እና በቆየ የድርጅታቸው ዋና አላማ ከበደኖ እስከ ማይካድራ ገድለው አስገድለውታል።

ህወሓት ከኦነግ ጋር ሽርክና ፈጥራ የሰራችው ስርአት ዋና ውስጠ አላማው እና ሁለቱን ያቧደናቸው ቁልፍ ጉዳይ የጸረ አማራ እምነት ተጋሪ በመሆናቸው ነበር። ይህ የሁለቱ ጸረ አማራ አቋም ግን የማታ ማታ ህወሓት ከመሀል ተገፍትራ ከስልጣን ከተባረረች በኋላ ጉዳቱ በትግራይ ሕዝብ ላይ ሆነ። የትግራይን ሕዝብ ከወንድሞቹ ከአማራው እና ከአፋሩ ጋር አጋደሉት። ለማሳያ ኦነጋውያኑ የትግራይን ሕዝብ ለመውጋት እየተዘጋጁም እንኳን እነጌታቸው ረዳ ሂሳብ እናወራርዳለን ያሉት ከትግራይ ሕዝብ የቅርብ ወገን ከአማራው ጋር ነበር። ያሁለት አመት የወሰደ ጦርነት ምን እንዳደረሰ ዛሬ ሁሉም ዜጋ ያየው የታዘበው ያዘነበትም በመሆኑ ሌላ ትንታኔ አያስፈልገውም።

በማጠቃለያ የትግራይ ሕዝብ እና የአማራ ሕዝብ በህወሓት/ኦነግ የተሰራው ስርአት የጎዳው ሕዝብ ነው። ዛሬ የአማራ ሕዝብ እና የትግራይ ሕዝብ የዘር ፖለቲካ ተጎጅ ብቻ ሳይሆን የሌሎች የቂም በቀል መወጫ መሆኑን በግልጽ ያሳየ ነው። ይህን በሁለቱ ጠባብ ኃይሎች የተሰራ ስርአት ለማፍረስ ዛሬ የአማራ ወጣት ብረት አንስቷል። ይህ በሁለቱ ኃይሎች የተሰራ ስርአት በአማራ ሕዝብ ላይ ያስከተለውን ጉዳት ከበደኖ አርባ ጉጉ በተለይም ወላጋ እና መተከል በፈሰሰው ደሙ አይቶት እንዳይመለስ ቆርጦ እና ታጥቆ ተነስቷል። የብልጽግናው ካድሬወች እና ወዶ ገባ በውጭ የሚኖሩ ደጋፊወቻቸው እንደሚሉት ፋኖ የትቂት ልሂቃን አላማ አስፈጻሚ ሳይሆን ሕዝባዊ እና የተደቀነበትን የመኖር አደጋ የመቀልበስ ብሎም አያቶቹ ያቆሟትን ሐገር መልሶ የሕዝቧ መኖሪያ የማድረግ መዳረሻ የያዘ ታላቅ አላማ ነው።

የዘረኞችን ጎራ ያስደነገጠው ገድል

ይህን ከላይ ያለውን ተጨባጭ ኩነት ከዘረዘርሁ በኋላ እንደገና ተስፋ ሰጭ ዜና ከዳንግላ የአማራ ፋኖ በኩል የመጣ ዜና ስሠማ ህወሃት እና ኦነግ ከተመሰረቱ እና ሰፊውን የዘር ጥላቻ ዘመቻ ዘመን እቅድን ካወጡ በኋላ ቢያንስ ሁለት ትውልድ በማህል አልፏል። ይህ የአያቶቹ ልጅ የሆነው የአማራ ወጣት ህወሓት እና ኦነግ የሰሩትን የግፍ ሰንሰለት ለመስበር እና የአማራ ሕዝብን ሕልውና ለመከላከል የተደራጀው ትውልድ ማንም ሳያስተምረው የሕዝብን ታሪካዊ ትስስር በመገንዘብ

በሰሞኑ በዳንግላ የፋኖ ኦፕሬሽን የታየው የጀግንነት እና የብስለት ተግባር ለትግራይ ሕዝብ ያሳየው የቂም በቀል ሳይሆን ብስለት አርቆ አስተዋይነት እና የሁለቱ ሕዝቦች መሰረትን ያሳየ ያስረገጠ ተግባር በመሆኑ። በዚህ ሰብአዊ እና ወገናዊ ተግባር የአረመኔው የአብይ አህመድ መንግስት እና ድርጅትን ቢያበሳጭ አያስገርምም።ሆኖም ግን የህወሓት እምነት ያደረባቸውን የትግራይ ልሂቃን ያስደስታል ተብሎ የሚገመት አይደለም።

አረመኔው አብይ አህመድ እና የብልጽግናው ወታደራዊ መሪወች ለአለፉት አመታት ደጋግመው የነገሩን በትግራይ እና አማራ ሕዝብ መካከል የማይታረቅ በቀል ፈጥረናል የምትለዋ እና የእነሱ ስልጣንን ለማስቀጠል ሁለቱን አንድ ባህል ሃይማኖት የሚጋሩ ወገኖችን ማጋደል እና ጠላቶች አስደርጎ ማስቀጠል ተስፋን ያቀጨጨ እና ያስደነገጠ ተግባር መሆኑ ነው።ይህን የአረመኔውን ሁለቱን በማጋደል ስልጣኑን ማስቀጠል የሚለውን እሳቤ ማምከን የሚቻለው የህወሓትን አሁንም አማራ ጠላቴ ነው የሚለውን ሀሳብ ማስኬድ ወይንም ማደስ ሳይሆን የኦነግን/ህወሓትን ስረ እምነት በመቃረን ባቻ ነው።

ይህን አስመልክቶ “ከፈረሱ አፍ” እንዲሉ ከዳንግላ ወህኒ ቤት በፋኖ ተለቀው ቤታቸው የገቡት ታሳሪወች ለሚዲያ በሰጡት ቃለ ምልልስ በሰጡት ቃል በእስር ላይ እያሉም በዙሪያቸው አብረዋቸው የታሰሩ አማሮች ያደረጉላቸውን ድጋፍ እና ትብብር በጥሩ ቃል መስክረዋል። ይህ አማራ ጠል ለሆነው መንግስትም ሆነ ስርአት አስደንጋጭ ቢሆን ሊያስገርመን አይገባም። የልቅ የትግራይ ልሂቃን የህወሓትን አላማ ይዘው እስከዛሬ ከአማራ እራስ ያልወረዱት ለሕዝባቸው ሲሉ እራሳቸውን ከፖለቲካ ቢያገሉ እና ለ 50 የተጓዙበት ጸረ አማራ የሆነውን የዘር ፖለቲካቸው ላይጠገን የፈረሰ መሆኑ ቢረዱ ለትግራይ እና ለማራ ሕዝባችን መልካም የተስፋ ግዜን ይፈጥራል። መልካምነቱ ደግሞ ቆመንለታል ያሉት የትግራይን ሕዝብ በተግባር ያስጨፈጨፉ ብሎም ለርሐብ ስደት እና ሞት የዳረጉ በመሆናቸው የነሱም የፖለቲካ አላማ እንደአረመኔው አብይ አህመድ ከዚህ በኋላ የማይሰራ መሆኑን ተረድተው ለሕዝባችን ለሚሉት ውለታ ሊውሉ ካሰቡ ነጻነቱን መስጠት እና ከወንድም እህቱ የአማራ የአገው እና የአፋር ሕዝብ ጋር ሆኖ ይህን ክፉ ዘመን እንዲለውጠው ቢለቁለት የተሻለ እና ክፉ ታሪካቸውን የሚጠግንላቸው ይሆናል።

የዘረኛውን ስርአት የገነቡት የህወሓት አመራር አሁንም እና ከዚህ እልቂት እና መከራ በኋላ ሀሳባቸውን አለመለወጣቸው እና የገነባነው ዘር ተኮር ስርአት አያዋጣም ለሰራነውም “ይቅርታ እንጠይቃለን” ከማለት ይልቅ በሰሞኑ የእህወሓት ስብሰባ “ህወሓት ስትራቴክ መሪ የላትም” ማለታቸውን ከነሱ ከባቢ የወጡ ዜናወች አድርሰውናል። ሆኖም ህወሓት የእስትራቴጅክ መሪ ማጣት ብቻ ሳይሆን እስትራቴክ የሆነ አላማ የለሽ እና የሰሩት ስርአትን አፍርሰው አለም የሚመራበትን የስርአተ መንግስት ግንባታ እስካልተቀበሉ ድረስ ጥፋቱ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ ጀኖሳይድ በኋላ ኢትዮጵያን እንደሐገር የምናጣት መሆኑን መገንዘብ ይገባቸዋል። መገንጠል ትናንት ለኤርተራ ሕዝብ የነጻነት፤ እኩልነት፤ እድገት እና ብልጽጋን እንዳላመጣ ሁሉ። ለትግራይ ሕዝብ የባሰ መከራ ድህነት እና ሌላ ጦርነት የሚያስከትል ነው።

ለማጠቃለል በሰሞኑ የታየው ዘረኞች የሰሩትን የእሾህ አሜካላ አጥር ሰብሮ ይህ ታጋይ እና ትንታግ አዲስ ትውልድ በዳንግላ ወህኒ ቤት ታስረው ከ 18 አመት እስከ እድሜ ልክ የተፈረደባቸው ወታደራዊ መኮ0ንኖችን ፈትቶ እና ሸኝቶ ለቤታቸው ማብቃት የቆሸሸው ዘር ተኮር ስርአት የፈጠረው መሆኑን እና ያነን ማፍረስ አላማ የያዘ ትግል ፋኖ እያካሄደ መሆኑን አስረግጦ ማሳያ ነው!!

ድፍን 50 አመታት ተቆጥሯል። የትግራይን ሕዝብ ከአማራ ወንድሙ እና እህቱ ለማለያየት የተሰራው ሰይጣናዊ ስራ በተግባር ተተርጉሞ ሁለቱን በባህል፤ በቋንቋ መሰረት፤ በሐይማኖት እና ተውፊት የማይለያዩ እንዲለያዩ ከተደረገ። ይህን ለሽሆች አመታት ቅድስት ሐገራችንን እንድትቀጥል እና በአለም ላይ ለተገፉ አገራት በግፍ ተይዘው ቅኝ ለተገዙ ሕዝቦች ተምሳሌት የሆነችን ሐገር መስራች የሆኑ ሕዝቦችን ለያይተው ያዋጉ እና በሐገሪቱ የወደፊት ቀጣይነት ጥያቄ ውስጥ ያስገቡት በህወሓት ስር የተሰለፉ የትግራይ ልሂቃን ስህተት ነው ይበሉት ወይንም ሌላ ነገር ታቅዶ፤ ተጠንቶ እና ተሰልቶ የተሰራ ክፉ ስራ እነዚህ ሁለት ወንድማማቾች/እህታማች ሕዝባችን በመለያየት ሰርተዋል። በሽሆች አመታት የታሪክ ሰንሰለት የተጋመዱ ብዙ ክፉም ደግም አጋጥሟቸው ሁሉንም እንደአመጣቱ የተቀበሉ እና ክፉን በትግል የመከቱ የአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በአንድ ቆመው ታሪክን ሰርተው እስከ 1967 ዓም ህወሓት እስከተመሰረተችበት ግዜ ድረስ አብረው ኖረው የዘለቁ አንድ ህዝብ ነበሩ።

የነዚህ ወገኖች ታሪክም አፈታሪክ ሳይሆን በእውን አለም የተሰራ የ 3000 አመታት የታሪክ ሰንሰለት እና ገድል መሆኑን ከዘመነ ወያኔ በፊት የተደረሱ ታሪካዊ መዝገቦች ያሳያሉ። የታሪክ ተማራማሪወች ምሁራን፤ የቤተክህነት ጠቢባን ሁሉ የዘገቡት ሰንደው ያስቀመጡት ገሐድ እውነትም ነው። አንዱ የሌላው ውህድ አካል መሆኑን ተጋብቶ፤ ተዋልዶ ተዛምዶ በመኖሩ አስይቷል። በቋንቋ፤ በሓይማኖት፣ በባህል ታሪክን በማስቀጠልም ሆነ የጋራ ታሪክ በመስራት ወደር የለሽ ትስሥር ያለው ሕዝብም ነው/ነበርም።ከሁሉም በላይ የቀይ ባህርን መንገዱ አድርጎ የመጣ ሁሉ የውጭ ጠላት የመጀመሪያው መዳረሻው ትግራይ እንደሆነ ሁሉ አማራው እና አገው ሽናሻውና ኦሮሞው ጋሞው እና ጉራጌ ሳይቀር የወገኑን የጥቃት ገፈት ተካፋይ ሆኖ ዘለቋል።

የትግራይ፤ የአማራ እና አገው ሊቃውንት የቤተክህነት ሰወች፤ የቆሎ ተማሪወች አንዱ ወደሌላው በመሄድ ከዘመነ ስልጣኔ እና የዘመናዊ ትምህርት ከመስፋፋቱ በፊት ትምህርትን ይጋሩ እንደነበር እስከቅርቡ ዘመንም ለሽሆች አመታት እንደቀጠሉ የምርምር ውጤት መፈለግ ሳያስፈልግ አሁን በህይወት ያሉ አባቶች ከተራ ቀሳውስት እስከ ዛሬው ብጹ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ የእውን ምስክሮች ናቸው።

አማራ ትግሬ እና አገው እንደትውፊታቸው ሁሉ የስርአተ መንግስታቸውም መነሻ ከንግስተ ሳባ እና ከቀዳማዊ ሚኒሊክ ይመዘዛል። እስከ ቅርቡ ዘመን ህወሓት እስከፈጠረው ትውልድ ድረስ ትግራውያን የንግስተ ሳባ ማንነትን ከአክሱማዊት ስልጣኔ ጅማሮ ጋር በኩራት ያያይዙታል። ይህን ታሪክ አማሮች እና አገወችም ይጋሩታል። ሁለቱ አማራ እና ትግራውያን ከኩሽ የተደባለቁ እና ሴማዊ ዝርያ እንዳላቸው ታሪካቸውም ያትታል ከደቡባዊ አረብያ ፈልሰው ከኩሻዊው አገው ጋር መቀየጣቸው የማይክዱት ታሪካቸው ነው።

ይህን ታሪካዊ ትስሥር በ 1960 ወቹ ከትግራይ ከተማሪወች ንቅናቄ በአፈነገጡ የትግራይ ተማሪወች ተመስርታ ከ 17 አመታት የትጥቅ ትግል በኋላ ለስልጣን የበቃችው ድርጅት (ህወሓት) አንዴ ስትክደው ሌላ ግዜ ስታወግዘው ለ50 አመታት ዘልቃለች። የዚህን ለሽህ አመታት የተዋለደ በባህል፤ በቋንቋ እና በሁለመናዊ ትውፊቱ የተጋመደውን ሕዝብ በጠላትነት በመፈረጅ የ 27 አመታቱን የስልጣን ዘመን በጥላቻ አሳልፈዋለች።

ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው እና እጅግ ዘግናኝ የሆነውን ጦርነት በአረመኔው አብይ አህመድ ኦነጋዊ መንግስት እና በህወሓት መካከል ሲጀመር። የህወሓት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አመራር ሂሳቤ የምናወራርደው ከአማራ ልሂቃን (ሕዝብ) ጋር ነው በማለት ጦርነቱን ወደወሎ እና ጎንደር አሻግረውታል። በዚያም ብዙ ጉዳት እንዲደርስ ሁጅኗል። ይህን የተረዳው የአብይ አህመድ መንግስትም ያሰበው እና ያለመው ተሟልቶለት ሁለቱን ብቻ ሳይሆን የአፋርን ሕዝብ ጨምሮ ቁጥረ ብዙ የሆኑ ዜጎች ጭዳ የሆኑበትን ጦርነት አካሂዷል። የደረሰ መኽር ተቃጥሏል፤ የጋማ ከብቶች ተገድለዋል፤ ቤት ንብረት እና ተቋማት ፈራርሰዋል። ዛሬ ይህ ጦርነት ካለፈ በኋላ እና አረመኔው አብይ አህመድ በአማራ ላይ የጀኖሳይድ ጦርነት ካወጀ ወዲህ እንደምናየው የኦነጋዊ ሰራዊት በጎጃም መኸር ማቃጠል ሴቶችን መድፈር እና ተመሳሳይ ወንጀሎች መፈጸሙን ቀጥሎበታል። ይህ ማለት ህወሓትም ሆነ የአረመኔው አብይ ሰራዊት ለትግራይ፤ ለአማራ እና ለአፋር ሕዝባችን የሚራራ ልቦና አላቸው ለማለት የማያስደፍር መሆኑን በዚህ የአምስት አመት ጦርነቶች እያየን ነው። የአማራ፤ የትግራይ፤ እና የአፋር ሕዝብ ጦርነቱም ቢቆም እንኳን የፈረሱ መሰረተ ልማቶችንም ሆነ የወደሙ ማምረቻ ተቋማትን መልሶ ወደነበሩበት ለመውሰድ አመታት የሚፈልግ መሆኑን ጄማል የተባለው የዋሽንግተን ፖስት ካሜራማን አሳይቶናል።

ሌላው ዛሬ የሚያሳዝነው ለ2000 አመታት የቆመችውን የሁለቱ ሕዝባችን የእምነት ቤት የሆነችውን ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ሳይቀር በመለያየት ዛሬ ሁለቱ ሕዝባችን በአንድ ቤተ እምነት ጸሎት ማድረግን ተነፍገዋል። ይህን በተመለከተ የኦሮሞ ልሂቃን እጅግ የሚያስመሰግን ስራ አሳይተዋል። የአረመኔው የአብይ አህመድ መንግስት ወታደሮች እና ጽንፈኛው ኦነግ በቤተክርስቲያኗ ምእመናን እና አባቶች ላይ የሚፈጽመውን ወንጀል እንዳለ ሆኖ ቤተክርስቲያኗ እንዳትከፈል ግን የቻሉትን ማድረጋቸውን አሳይተውናል የአርተመኔውን የኦሮሚያ ቤተክህነት የመመስረት አላማ አክሽፈውታል። ይህ በህወሓት የተሰራው ሐገራችንን ያስቀጠለች ቤተክርስቲያንን የትግራይ የኢትዮጵያ ተብላ እንድትከፈል ያደረገው ሂደት በዚህ የነሱ ዘመን መሆኑ በእጅጉ አሳዛኝ እና ታሪክ የሚታዘበው ድርጊት ነው።

የኦነግ/ህወሓት ስርአተ መንግስት

ህወሓት ከኦነግ ጋር በመሆን በመሰረተችው ስርአትም ሆነ ሁለቱ ዘረኛ ድርጅቶች በጻፉት ህገመንግስት ውስጥ በ 3000 አመት የተገነባች ኢትዮጵያን የካደ እና በውስጧ የበቀሉ ቋንቋወችን አገር፤ ሕዝብ ብሔር ብሔረሰብ እያለ የሰየመ እና ለሽሆች አመታት በደም ፍሳሽ በአጥንት ክስካሽ የተገነባችውን ሐገር ኦነግ እና ህወሓት አፍርሰው የዘር ክልሎች በማዋቀር አማራውን በማግለል እስከዚህ ጦርነት ዘልቀዋል።

በአማራ እና የትግራይ ሕዝብ መካከል መቸውም ጠላትነት ኖሮ አያውቅም። ህወሓታውያን ልሂቃን ግን የሌለ ታሪክ በመደርደር የአማራን ሕዝብ በማግለል እና አጥቅተው በማስጠቃት ለ 27 አመታት ተግተው ሰርተዋል። እነመምህር ገብረ ኪዳን አይነቱ ልሂቃን ኢትዮጵያን የምጠላት በአማራ መኖር ነው እስኪሉ እና ይህን ነውራቸውን በአደባባይ በመግለጽ አሰምተውናል። አማራን ለመጉዳት በሚል መንፈስ እና በቆየ የድርጅታቸው ዋና አላማ ከበደኖ እስከ ማይካድራ ገድለው አስገድለውታል።

ህወሓት ከኦነግ ጋር ሽርክና ፈጥራ የሰራችው ስርአት ዋና ውስጠ አላማው እና ሁለቱን ያቧደናቸው ቁልፍ ጉዳይ የጸረ አማራ እምነት ተጋሪ በመሆናቸው ነበር። ይህ የሁለቱ ጸረ አማራ አቋም ግን የማታ ማታ ህወሓት ከመሀል ተገፍትራ ከስልጣን ከተባረረች በኋላ ጉዳቱ በትግራይ ሕዝብ ላይ ሆነ። የትግራይን ሕዝብ ከወንድሞቹ ከአማራው ከአፋሩ እና አገው ጋር አጋደሉት። ለማሳያ ኦነጋውያኑ የትግራይን ሕዝብ ለመውጋት እየተዘጋጁም እንኳን እነጌታቸው ረዳ ሂሳብ እናወራርዳለን ያሉት ከትግራይ ሕዝብ የቅርብ ወገን ከአማራው ጋር ነበር። ያሁለት አመት የወሰደ ጦርነት ምን እንዳደረሰ ዛሬ ሁሉም ዜጋ ያየው የታዘበው ያዘነበትም በመሆኑ ሌላ ትንታኔ አያስፈልገውም።

በማጠቃለያ የትግራይ ሕዝብ እና የአማራ ሕዝብ በህወሓት/ኦነግ የተሰራው ስርአት የጎዳው ሕዝብ ነው። ዛሬ የአማራ ሕዝብ እና የትግራይ ሕዝብ የዘር ፖለቲካ ተጎጅ ብቻ ሳይሆን የሌሎች የቂም በቀል መወጫ መሆኑን በግልጽ ያሳየ ነው። ይህን በሁለቱ ጠባብ ኃይሎች የተሰራ ስርአት ለማፍረስ ዛሬ የአማራ ወጣት ብረት አንስቷል። ይህ በሁለቱ ኃይሎች የተሰራ ስርአት በአማራ ሕዝብ ላይ ያስከተለውን ጉዳት ከበደኖ አርባ ጉጉ በተለይም ወላጋ እና መተከል በፈሰሰው ደሙ አይቶት እንዳይመለስ ቆርጦ እና ታጥቆ ተነስቷል። የብልጽግናው ካድሬወች እና ወዶ ገባ በውጭ የሚኖሩ ደጋፊወቻቸው እንደሚሉት ፋኖ የትቂት ልሂቃን አላማ አስፈጻሚ ሳይሆን ሕዝባዊ እና የተደቀነበትን የመኖር አደጋ የመቀልበስ ብሎም አያቶቹ ያቆሟትን ሐገር መልሶ የሕዝቧ መኖሪያ የማድረግ መዳረሻ የያዘ ታላቅ አላማ ነው።

የዘረኞችን ጎራ ያስደነገጠው ገድል

ይህን ከላይ ያለውን ተጨባጭ ኩነት ከዘረዘርሁ በኋላ እንደገና ተስፋ ሰጭ ዜና ከዳንግላ የአማራ ፋኖ በኩል የመጣ ዜና ስሠማ ህወሃት እና ኦነግ ከተመሰረቱ እና ሰፊውን የዘር ጥላቻ ዘመቻ ዘመን እቅድን ካወጡ በኋላ ቢያንስ ሁለት ትውልድ በማህል አልፏል። ይህ የአያቶቹ ልጅ የሆነው የአማራ ወጣት ህወሓት እና ኦነግ የሰሩትን የግፍ ሰንሰለት ለመስበር እና የአማራ ሕዝብን ሕልውና ለመከላከል የተደራጀው ትውልድ ማንም ሳያስተምረው የሕዝብን ታሪካዊ ትስስር በመገንዘብ

በሰሞኑ በዳንግላ የፋኖ ኦፕሬሽን የታየው የጀግንነት እና የብስለት ተግባር ለትግራይ ሕዝብ ያሳየው የቂም በቀል ሳይሆን ብስለት አርቆ አስተዋይነት እና የሁለቱ ሕዝቦች መሰረትን ያሳየ ያስረገጠ ተግባር በመሆኑ። በዚህ ሰብአዊ እና ወገናዊ ተግባር የአረመኔው የአብይ አህመድ መንግስት እና ድርጅትን ቢያበሳጭ አያስገርምም።ሆኖም ግን የህወሓት እምነት ያደረባቸውን የትግራይ ልሂቃን ያስደስታል ተብሎ የሚገመት አይደለም።

አረመኔው አብይ አህመድ እና የብልጽግናው ወታደራዊ መሪወች ለአለፉት አመታት ደጋግመው የነገሩን በትግራይ እና አማራ ሕዝብ መካከል የማይታረቅ በቀል ፈጥረናል የምትለዋ እና የእነሱ ስልጣንን ለማስቀጠል ሁለቱን አንድ ባህል ሃይማኖት የሚጋሩ ወገኖችን ማጋደል እና ጠላቶች አስደርጎ ማስቀጠል ተስፋን ያቀጨጨ እና ያስደነገጠ ተግባር መሆኑ ነው።ይህን የአረመኔውን ሁለቱን በማጋደል ስልጣኑን ማስቀጠል የሚለውን እሳቤ ማምከን የሚቻለው የህወሓትን አሁንም አማራ ጠላቴ ነው የሚለውን ሀሳብ ማስኬድ ወይንም ማደስ ሳይሆን የኦነግን/ህወሓትን ስረ እምነት በመቃረን ባቻ ነው።

ይህን አስመልክቶ “ከፈረሱ አፍ” እንዲሉ ከዳንግላ ወህኒ ቤት በፋኖ ተለቀው ቤታቸው የገቡት ታሳሪወች ለሚዲያ በሰጡት ቃለ ምልልስ በሰጡት ቃል በእስር ላይ እያሉም በዙሪያቸው አብረዋቸው የታሰሩ አማሮች ያደረጉላቸውን ድጋፍ እና ትብብር በጥሩ ቃል መስክረዋል። ይህ አማራ ጠል ለሆነው መንግስትም ሆነ ስርአት አስደንጋጭ ቢሆን ሊያስገርመን አይገባም። የልቅ የትግራይ ልሂቃን የህወሓትን አላማ ይዘው እስከዛሬ ከአማራ እራስ ያልወረዱት ለሕዝባቸው ሲሉ እራሳቸውን ከፖለቲካ ቢያገሉ እና ለ 50 የተጓዙበት ጸረ አማራ የሆነውን የዘር ፖለቲካቸው ላይጠገን የፈረሰ መሆኑ ቢረዱ ለትግራይ እና ለማራ ሕዝባችን መልካም የተስፋ ግዜን ይፈጥራል። መልካምነቱ ደግሞ ቆመንለታል ያሉት የትግራይን ሕዝብ በተግባር ያስጨፈጨፉ ብሎም ለርሐብ ስደት እና ሞት የዳረጉ በመሆናቸው የነሱም የፖለቲካ አላማ እንደአረመኔው አብይ አህመድ ከዚህ በኋላ የማይሰራ መሆኑን ተረድተው ለሕዝባችን ለሚሉት ውለታ ሊውሉ ካሰቡ ነጻነቱን መስጠት እና ከወንድም እህቱ የአማራ እና የአፋር ሕዝብ ጋር ሆኖ ይህን ክፉ ዘመን እንዲለውጠው ቢለቁለት የተሻለ እና ክፉ ታሪካቸውን የሚጠግንላቸው ይሆናል።

የዘረኛውን ስርአት የገነቡት የህወሓት አመራር አሁንም እና ከዚህ እልቂት እና መከራ በኋላ ሀሳባቸውን አለመለወጣቸው እና የገነባነው ዘር ተኮር ስርአት አያዋጣም ለሰራነውም “ይቅርታ እንጠይቃለን” ከማለት ይልቅ በሰሞኑ የእህወሓት ስብሰባ “ህወሓት ስትራቴክ መሪ የላትም” ማለታቸውን ከነሱ ከባቢ የወጡ ዜናወች አድርሰውናል። ሆኖም ህወሓት የእስትራቴጅክ መሪ ማጣት ብቻ ሳይሆን እስትራቴክ የሆነ አላማ የለሽ እና የሰሩት ስርአትን አፍርሰው አለም የሚመራበትን የስርአተ መንግስት ግንባታ እስካልተቀበሉ ድረስ ጥፋቱ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ ጀኖሳይድ በኋላ ኢትዮጵያን እንደሐገር የምናጣት መሆኑን መገንዘብ ይገባቸዋል። መገንጠል ትናንት ለኤርተራ ሕዝብ የነጻነት፤ እኩልነት፤ እድገት እና ብልጽጋን እንዳላመጣ ሁሉ። ለትግራይ ሕዝብ የባሰ መከራ ድህነት እና ሌላ ጦርነት የሚያስከትል ነው።

ለማጠቃለል በሰሞኑ የታየው ዘረኞች የሰሩትን የእሾህ አሜካላ አጥር ሰብሮ ይህ ታጋይ እና ትንታግ አዲስ ትውልድ በዳንግላ ወህኒ ቤት ታስረው ከ 18 አመት እስከ እድሜ ልክ የተፈረደባቸው ወታደራዊ መኮ0ንኖችን ፈትቶ እና ሸኝቶ ለቤታቸው ማብቃት የቆሸሸው ዘር ተኮር ስርአት የፈጠረው መሆኑን እና ያነን ማፍረስ አላማ የያዘ ትግል ፋኖ እያካሄደ መሆኑን አስረግጦ ማሳያ ነው!!

ድል ለተገፋው የአማራ ሕዝብ!!!

ድል ግፍ አንገሽግሾት መሳሪያ ለታጠቀው ፋኖ!!!

ምስጋናየንም ቀያሪውን የንዳንግላ ኦፕሬሽን ለመሩት

ለሻለቃ አለልኝ ባይህ እና ታጋይ ዘመን ተሻለ ከታልቅ አክብሮት ጋር!!!

Source: Mengistu Musie’s facebook account

Exit mobile version