Dinknesh Ethiopia

የአዲስ አበባ የኢሕአፓ ኮሚቴ የአመራር አባል ፖለቲከኛና ጋዜጠኛ ይስሐቅ ወልዳይ  ከአርአያ ተስፋማርያም የአፈና ወይም ግድያ ሙከራ አመለጡ

¤ ከእገታና ሞት ተረፍኩኝ  —
ይስሐቅ ወልዳይየአዲስ አበባ የኢሕአፓ ኮሚቴ የአመራር አባል ፖለቲከኛና ጋዜጠኛ ይስሐቅ ወልዳይ

በዛሬዉ ቀን 19/02/17 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 7:10 አከባቢ ከአትላሰ ወደ 22 አከባቢ በግል ስራ ምክንያት በእግር እየሄድኩኝ ሳለ: ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቱት #አርአያ ተስፋማርያም የተባለ ግለሠብ #የመከላከያ ታርጋ የለጠፈ ፒክ አፕ መኪና በመያዝ ሲከታተለኝ ቆይቶ አመቺ ነዉ ባለዉ ቦታ መኪናዉን በመጠቀም ሊያፍነኝ ሞክረዋል። አፈናዉን ለመፈፀም በ5ሜትር በማይሞላ ልዩነት ርቀት ከያዘዉ #የመከላከያ ፒክአፕ ቀድሜ ስሮጥ እሱና ሌሎች ጭምር ከኋላዬ እየተከተሉ ሊይዙኝ ሲሉ ድንገት በአከባቢዉ የነበሩ የካራማራ ፖሊስ ጣብያ ሲቪል ክትትሎችን አስቁመዉን እኔም ከእገታ እሱም ከአጋችነት ማስቆም ችለዋል።
ይህ እንዳለ ሆኖ አሁንም አርአያ የተባለዉ ግለሠብ ለሲቪል ክትትሎች ” እኔ የመከላከያ አባል ነኝ ኮነሬል …… አታዉቁትም ወይ ይዘነዉ እንሄዳለን ስጡን ማለቱ አልተዉም። ይሁን እንጂ እነዛ የካራማራ ፖሊሰ ጣብያ ሲቪል ክትትሎች አስፈላጊ ከሆነም በህግ ጠይቁት በማለት ወደ ካራማራ ፖሊሰ ጣብያ ይዘዉን ሄዱ።
ካራማራ ፖሊሰ ጣብያ በደረስን ጊዜም ለሁለታችን በየግል በስርአት አዉርተዉን እሱ እየጮሀ ሲወጣ አይቼዋለሁ። በመቀጠል እኔንም የተወሰነ ሰአታት እንጠብቀዉ ካልመጣ ግን እንለቅሃለን አሉኝ። በተለይ ኢንስፔክተር አዳነ የተባሉት የካራማራ ፖሊሰ በተደጋጋሚ ለአርአያ ተስፋማርያም በመደወል ተሎ የማትመጣ ከሆነ ንፁህ ሠዉ የምናስርበት የህግ ማእቀፍ የለንም በማለት ሲያናግሩት ሰምቻለሁ። ከሦስት ሰአታት በላይ ብንጠብቀዉም አጋቼ ተመልሶ ወደ ፖሊሰ ጣብያዉ ድርሸ አላለም።
ይህንን የእገታ ተግባር(ወንጀል) በአንድ ግዙፍ በአዋጅ የታቋቋመ #የመከላከያ ሎጂስቲክ(መኪና) እና #የክብር አባልነት ስም ሽፋን በማድረግ ሲፈፀም ደሞ ለተቋሙም የሚሰጠዉ ገፅታ አሉታዊ ያደርገዋል። ስለዚህ በተለይ የመከላከያ ተቋም በባለቤትነት በያዛቸዉ መኪኖች እንዲሁ አንድ የተቋሜ አምባሳደር ይሆንልኛል ብሎ የሸለመዉ ሠዉ በጠራራ ፀሃይ አንድ በህጋዊ መንገድ የሚታገል የፖለቲካ ፓርቲ አመራር ለሆነ ዜጋን ለማገት መጠቀሙ ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑ የመከላከያ የንብረትና ሠዉ አስተዳደር እነዚህ ንብረቶቹ በየቀኑ እንደኔ ድምፅ ሳያገኙ ቀርተዉ ዜጎች እየታገቱበት እንደማይሆን እርግጠኛ መሆን ስለ ማይቻል ቁጥጥር ቢያደርግ እላለሁ።
በዚህ አጋጣሚ የካራማራ ፖሊሰ ጣብያ ስማቸዉን ያላወቅኳቸዉ ሲቪል ክትትል አባላት እኔ ከእገታ በማትረፍ ወደ ፖሊሰ ጣብያ በመዉሰዳቸዉ ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። እንዲሁ በፖሊሰ ጣብያ ከገባሁ በኋላም ኢንስፔክተር አዳነ የተባሉት የጣብያ የሆነ ዘርፍ ሃላፊም ከህግ ዉጭ እንዳልታሰር ሞያዊ ግዴታቸዉን በመወጣታቸዉ ምስጋናዬ ይድረሰ
N.B = በተለየ መልኩ ደግሞ ከእገታዉ ሙከራ ደቂቃዎች ጀምሮ ጉዳዬን በንቃት ሲከታተሉ የነበሩትን ጠበቃ Abera Nigus የፓርቲዬ #ኢሕአፓ ከፍተኛ አመራሮች ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት የትግራይ የኢሕአፓ አስተባባሪ ጓደኛዬም Gidena Medhin እንዲሁም የኢሕአፓ አዲሰ አበባ ኮሚቴ አባላት ምንም እንኳ ለአንድ የፓርቲ አመራራቸዉ ማድረግ የሚገባቸዉ ቢሆንም ከሚድያ ጀምሮ እስከ የሚመለከታቸዉ አካላት በማሳወቅ እንዲሁም ፖሊሰ ጣብያ ድረሰ በመምጣት እንድፈታ ላደረጉት ክብረት ይስጥልኝ ።
በቀጣይ በዛሬዉ ጉዳይ ፓርቲያችን ኢሕአፓ አስፈላጊዉን ነገር ከሚመለከታቸዉ አካላት እንደምሄድበት ይታወቅልን።
በተለየ መልኩ ከእገታዉ ሙከራ ጀምሮ በፍጥነት ድምፅ በመሆን እገታዉን በማጋለጥ የዜግነት ግዴታቸዉን የተወጡት ሚድያዎችም
#አሻም ቴሌቪዥን
#ምንጊዜም ሚድያ
#Ems
#Ethiopia reporter ሌሎች የዘነገኋቸዉ ሚድያዎችም አመሠግናለሁ
በመጨረሻ ከተያዝኩት ጀምሮ ሰምታችሁ ደምፅ በመሆን ለህግና ህጋዊነትን ዘብ በመቆም እገታዉን በማጋለጥ ድምፅ ለሆናችሁኝ ወዳጅ ጓደኞቼ ክብረት ይስጥልኝ
ከዝግጅት ክፍላችን።   አዲሱ የአር አያ ተስፋማርያም የሰራ ድርሻው አፈና ሆነ ማለት ነው።፡ ሲያልቅ አያምር
Exit mobile version