Source: ethio-online
ይህን የጠየቁት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሕብረት (ኢዴሕ)፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ)፣ የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ ፓርቲ (ኦነንፓ)፣ የአፋር ሕዝብ ነፃነት ፓርቲ (አሕነፓ) እና የአፋር ሕዝብ ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አሕፍዴፓ) ናቸው፡፡
‹‹በመላ ሀገሪቱ እየታሰሩ ያሉት የፓርቲ አመራሮችና አባላት ሰበብ እየተፈለገ የተወሰደው የእስር እርምጃ፣ ከዚህ ቀደም የአሸባሪነት ታርጋ በመለጠፍ ከተወሰደው ጋር ተመሳሳይነት ያለው በመሆኑ ድርጊቶ ቆሞ ንፁሀን ዜጎች ከእስራት ሊፈቱ ይገባል፡፡›› ብለዋል፡፡
እየተፈፀመ ያለው እስራት ዘርን መሰረት ያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ በባሕር ዳር እና በአዲስ አበባ በባለሥልጣናት ላይ የተፈፀመው ግድያም በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠይቀዋል፡፡
አዲስ አበባ የሁሉም ነዋሪዎቿ ነች ያሉት ፓርቲዎቹ ‹‹የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ይዞት የተነሳውን ጥያቄ ሕግን መሰረት ባደረገ ሁኔታ እንዲስተናገድ እንጠይቃለን፡፡›› ብለዋል ሰባቱ ፓርቲዎች በጋራ መግለጫቸው፡፡
ፓርቲዎቹ የሲዳማ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ ሕጋዊ ምላሽ እንዲሰጠው አሳስበዋል፡፡ ከያቄው ጋር በተያያዘ በንፁሃን ዜጎች ላይ ግድያ፣ ዝርፊያና ወከባ የፈፀሙ ቡድኖች ለሕግ እዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡