የወንድማማቾች መገዳደል ይቁም! – የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) rayaman 5 years ago የወንድማማቾች መገዳደል ይቁም! ኢሕአፓ: ህወሓት ከሃያ ስምንት ዓመት በፊት አገራችን ላይ የጫነው ጎሣን መሠረት ያደረገ ሕገ መንግሥት አሁንም በጥፋት ላይ ጥፋት እያስከተለ ነው። ባለፈው ዓመት በቤንሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያ፣ በሃዋሳ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በሐረር እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ ጎንደር በተፈጠረው ግጭት በርካታ የሰው ሕይወት ጠፍቷል። ግምቱ በውል ያልታወቀ ንብረትም ወድሟል። ንጹሃን ዜጎች ሃብት ንብረት አፍርተው ከኖሩበት ቀዬ ተፈናቅለዋል። እነዚህን ግጭቶች የቀሰቀሱት ጠባብ አመለካከት ያላቸው ጥቂት አክራሪ ብሄርተኞች መሆናቸውን መንግሥት በሚገባ ያውቃል። ነገር ግን ጠንከር ያለ ሕጋዊ እርምጃ ባለመውስዱ የጥፋት ኃይሎቹ ከተደበቁበት እየወጡ ጥፋት ከማድረስ ወደኋላ አላሉም። ዝም አንልም! – የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)