Site icon Dinknesh Ethiopia

እውን ምርጫ ቦርድ ነጻና ገለልተኛ ነው ? – ይናገር የነበረ(ከምድረ ኢትዮጵያ)

Ethiopia's electoral board

የምርጫ ቦርድ አባላት ምልመላ ስውር ድራማ ! እውን ምርጫ ቦርድ ነጻና ገለልተኛ ነው ? – ይናገር የነበረ(ከምድረ ኢትዮጵያ)

ይናገር የነበረ(ከምድረ ኢትዮጵያ). ይህ መጣጥፍ ዋና የምርምር ትኩረት በግንቦት ወር 2011 አም ማክተሚያ ላይ በጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ በኩል በኢህአዴግ ፓርላማ ፊት ቀርበው ከፍተኛ የሚባል ሀገራዊ ሃላፊነት የተጣለበትን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲመሩ የተመረጡት ወገኖችን እንዲሁም እነዚህን አዳዲስ የቦርድ አባላትን መልምለው አቀረቡ የተባሉ በመልማይ ኮሜቴ ስር የተደራጁ ወገኖችን ምንነትና ማንነትን በተመለከተ ከስር መሰረቱ የማውቀውንና በሚገባም ያወቅሁትን ግዙፍ ሀቅ አልፋና ኦሜጋ ያደረገ ነው፡፡

በእውቀትና ክህሎት የበሰሉ የፖለቲካና የህግ ምሁራንን ከምርጫ ቦርድ አባልነት ለማግለል የተደረገው የእነ አቢይ አህመድ ስውር ሴራ ለህዝብ በይፋ መገለጥ አለበት በማለት በበቂ ደረጃ ምክከር ተደርጎበት መግባባት ላይ ስለተደረሰ ይህንኑ መጣጥፍ አዘጋጅተናል፡፡ ከምንም በላይ በተለይ ከሰሞኑ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ እንሳተፋለን እያሉ በሚዲያ ሲያቅራሩ እየሰማን ነው፡፡

ይህ ደግሞ ስለ ምርጫ ቦርድ አመሰራረትና ገለልተኝነት በሚገባ ማጣራት ሲኖርባቸው የግል እና ቡድናዊ ፍላጎታቸውንና የንዋይ ለቀማ ህልማቸውን ገቢራዊ ለማድረግ በመጣደፍ መግለጫ መስጠታቸው ሀገሪቱ በእነማን ልትመራ እንደተዘጋጀት ከወዲሁ አመላካች ነው፡፡ አብንን ጨምሮ የታሰሩ አመራር አባላትን እንኳ ማስፈታት ያልቻሉ ቡድኖች ስለ ምርጫ ተሳትፎ ሽንጣቸውን ገትረው ሲናገሩ መስማቱ በበርካታ ዜጎች ዘንድ በፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ለመሳተፍ ያለውን ፍላጎት እንዳጨለመው አረጋግጦ መናገር ይቻላል፡፡

በወርሀ ግንቦት 2011 አም የምርጫ ቦርድ አባላት ሹመትና የተሾሙት ወገኖች ስነ ምልከታዊ ስብእናና ነባር ተሞክሮ የመዳሰሱ ውጥን ውጤትን ማስገኘት አለበት ብዩ በሚገባ አምናለሁ፡፡ ስለ ምርጫ ህግና ስርአት እሴቶች ከሚመለከታቸውም ሆነ ከማይመለከታቸው ወገኖች የተሰወረ ሆነም አልሆነ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አደረጃጀትን አስመልክቶ በምልአተ ህዝብ ማእቀፍ ስር የሚቀመጡት ዜጎች በዚህ መልክ መቀመጥ በማይችሉት ግና ስለ ተሾሙት ዜጎች ምንነትና ማንነት ማወቅ ይገባቸዋል ብዩ ያመንኩባቸውን ነጥቦችና አንገብጋቢ ጭብጦች መነሻ በማድረግ ሀቁን እንደ መድረሻ በመውሰድ ለማመላከት እንደምሞክር ከወዲሁ ለማስገንዘብ እሻለሁ፡፡ይህን መሰረት በማድረግ የተሰጠው ሹመት መነሻና የአመላመል ሂደት ምን እንደሆነ በየደረጃው ላመላክት፡፡

የምርጫ ቦርድ አባላትን የመለመሉ መልማይ ኮሚቴ አባላት እነማን ናቸው?
ለመሆኑ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አባላትን መልምለው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያቀርቡ በኮሚቴ መልክ የተመረጡት ወገኖች እነማን ናቸው ? የአመራረጣቸው አካሄድ ከህግና ከሞራል እሴቶችስ አኳያ እንዴት ይመዘናል ? ስለ ምርጫ ህግ፤ ደንብ፤መርህ፤እሴቶችና አጠቃላይና ዝርዝር ሲስተም (የአሰራር ፕሮሲጀር) ምን እውቀት አላቸው ? ለምልመላ የተጠቀሙበት መስፈርትስ ምን ያህል ፍትሃዊና ርእታዊ እሴቶችን ይወክላል ? በሚሉት አንኳር ጭብጦች ላይ ቀዳሚ ምልከታን በማሳረፍ መባል የሚገባውን ለማለት ቀዳሚ ምርጫ ወስጃለሁ፡፡

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አባላትን እንዲመርጡ የተሰየሙት የኮሚቴ አባላት ከሀይማኖት፤ከሲቪክና ከሙያ ማህበራት ወዘተ ተወክለው ሳይሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመርጠው የቀረቡ ናቸው፡፡ (1 ) ዶክተር መሸሻ ሸዋረገድ ሰብሳቢ ሲሆኑ ፤እርሳቸው የቀይ መስቀል ማህበር ዋና ጸሃፊ፤ የኦዴፓ አባል፤ ቀድሞ የኦሮምያ መስተዳድር ፕሬዚዳንት ጁኔዲን ሳዶ ጽ/ቤት ሃላፊ በመሆን የሰሩ፤ የክርስቲያን በጎ አድራጎት ኮንሶርሺየም( ሲአርዲኤ) ሊቀመንበር ሆነው የሰሩ፤ ቀደም ሲል በምርጫ ህግ፤ ደንብ፤መርህ፤እሴቶችና አጠቃላይና ዝርዝር ሲስተም (የአሰራር ፕሮሲጀር) ዙሪያ ምን ተሞክሮ እንዳላቸው በሰየማቸው አካል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያልተነገረ፤ ባለን መረጃና ማስረጃ መሰረት ይህ ለእርሳቸው እንደ ባእድ ተደርጎ የሚቆጠር መሆኑን በተመለከተ አነጋጋሪ አይደለም፡፡ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ናቸው::

ለተጨማሪ መረጃ ከሌሎች ተመክሮ–Ensuring the Integrity of Elections 1

Ensuring the Integrity of Elections 2

(2) አቶ ዘገየ አስፋው፤ የህግ ባለሞያ፤ በኦነግ አመራር ተጠርጥረው ለረዥም ጊዜ ያህል በደርግ ዘመን በወህኒ ቤት የነበሩ፤ ከእስር ከተለቀ ቁ በኋላ እስካሁን ድረስ ሁንዲ በሚባል ሀገር በቀል ድርጅት ውስጥ በሃላፊነት የሚሰሩ፤ ከፖለቲካው ርቀው የሚገኙና ከ1987 አም እስከ 2007 አም ድረስ ባሉት የምርጫ ሂደቶች በምንም ደረጃ ቢሆን ተሳታፊ ያልነበሩና ልምድ የሌላቸው፤የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ናቸው::

(3) አቶ ካሳሁን ፎሎ፤የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበር (ኢሰማኮ) ሊቀመንበር የሆኑ፤ የመለስ ዜናዊ፤ የህወሃት ቀኝ እጅ በመሆን የኢትዮጵያን ሰራተኞች ለባርነት ለመዳረግ ከባዱን ሚና የተጫወቱ፤ አሁን ተገልብጠው የአቢይ አህመድ አሟሟቂ ተብለው የተፈረጁ፤ ስለ ምርጫ ህግ፤ ዲዛይን ስርአት ወዘተ አንዳችም ሀገራዊም ሆነ አለም አቀፋዊ ተሞክሮ ጨርሶ የሌላቸው የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ናቸው::

(4) ወ /ሮ ብዙወርቅ የሚባሉ በእድሜ, ገፋ ያሉና በዩኒቨርሲቲ በመምህርነት እንደሰሩ የሚነገርላቸው በተመሳሳይም ስለ ምርጫ ህግ፤ ዲዛይን ስርአት ወዘተ አንዳችም ሀገራዊም ሆነ አለም አቀፋዊ ተሞክሮ ጨርሶ የሌላቸው ፣..የኦሮሞ ከፊል አማራ ብሄር ተወላጅ ናቸው (5) የእስልምና ጉዳዮች መሪ ሼህ ኡመር እንድሪስ፤ እንኳን በምርጫ ህግና ስርአት እንዲሁም አመራር ሂደት ይቅርና በፖለቲካ ጉዳዪችም ጨርሶ ተሳታፊ ሆነው የማያውቁ የሀይማኖት መሪ ናቸው፡፡የአማራ ብሄር ተወላጅ ናቸው::

ሙሉውን ለማንበብ

Exit mobile version