Site icon Dinknesh Ethiopia

በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ ያንዣበበው የዘር ማጽዳት/ የዘር ማጥፋት አደጋና የእያንዳንዳችን ሀላፊነት

ከፋይል ማህደር

 

ታህሳስ 15፤12፣ 2010 (ዲሰምበር 24፣ 2017)

ከጊዜው ደረሰ

Gezew.derese@bell.net

መነሻ

በተለያዩ ሀገሮች የተካሄዱ የዘር ማጥፋት ወይም የዘር ማጽዳት ወንጀሎችን ስንመረምር በተደጋጋሚ ከሚታዩት ልዩ ልዩ ክስተቶች ውስጥ አንዱ ወንጀሉ ከተፈጸመ በኋላ ይህን አሰቃቂ ወንጀል በጊዜ ለማሰቆም ባለመቻላቸው ብዙዎች መጸጸታቸውን ነው። ለዚህ ደግሞ ከሚሰጡት መክንያቶች ውስጥ ስለሁኔታው በጊዜ አለማወቅ፣ የሰው ልጅ የዚህ አይነት ጭካኔ ሊፈጽም ይችላል ብሎ አለማመን፣ አደጋው እንዳይደርስ የማድረጉን ሀላፊነት ሌሎች ይወስዳሉ ብሎ መገመት፣ እኔ ምን ልሰራ እችላለሁ ብሎ የራስን ሀላፊነት ዝቅ አድርጎ መውሰድ… ወዘተ ጥቂቶቹ ናቸው።

በሩዋንዳ፣ በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ1994 የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ፣ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት በአውሮፕላን አደጋ እንደሞቱ ወዲያውኑ ይጀመር እንጂ፣ ወደዚህ ጥፋት የተደረገው ጎዞ ግን አዝጋሚና በብዙ ማሰጠንቀቂያ ምልክቶች ሲገለጥ የቆየ ነበር።

በሩዋንዳ የዘር ማጥፋቱ ተግባር ሰለባ የሆኑት የቱትሲ ማህበረሰብ አባላት በተለያየ መልክ አድሎና ጥቃት ሲፈጸምባቸው ብዙ አመታት የቆየ ነበር። የሀገሪቱ ዜጎች በብሄር ተለይተው በመታወቂያው ላይ ከየትኛው ብሄር አባል እንደሆነ መግልጽ ግድ ስለነበር፣ ግድያው ሲጀመር ሁትሲዎችን ለመለየት መታወቂያቸውን መመልከቱ ብቻ በቂ ነበር።

የ1994ቱ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ከመጀመሩ ቀደም ባሉት ሶስትና አራት አመታት፣ በሀገሪቱ ባለስልጣኖችና የፖለቲካ መሪዎች አነሳሽነት፣ 16 ያክል ጥቃቶች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚኖሩ የቱትሲ ማህበረሰብ አባላት ላይ ተፈጽመው ነበር፡፡ በነዚህ ጥቃቶችም በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሕይወታቸውን አጥተዋል፣ ንብረታቸውም ወድሟል፣ ከመኖሪያ ቦታቸው ተፈናቅለዋል። ሆኖም ግን ይህን ጥፋት የፈጸሙ ባለስልጣኖች ይህ ነው የሚባል ቅጣት አልደረሰባቸውም ነበር። አለም አቀፉ ህብረተሰቡም የሚሆነውን ሁሉ በትክክል በበቂ ደረጃ ቢያውቅም ቀጣዩን ጭፍጨፋ ለማስቆም ከመጣር ይልቅ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ማለፉን መርጦ ነበር።

እነዚህ ሁሉ እንዲቆሙ ያልተደረጉ ተግባሮች ተጠናክረውና  ሙሉውን ለማንበብ

Exit mobile version