ከአገር ውጭ ነዋሪ የኢሮብ ተወላጆች ለለኢ.አ.አ መመስረት የድጋፍ መግለጫ rayaman 5 years ago የኢሮብ ህዝብ የሩቁን የጣልያን ወረራ ጊዜ አገርን ከግፈኛ የውጭ ወራሪ ለመከላከል የዓሲምባ ተራራና በረሃን ደጀኑ በማድረግ ለነፃነት የከፈለውን መስዋእትነት ለታሪክ ፀሓፊዎች ትተን የቅርቡን ካነሳን በ1966 ዓ. ም. ኢ የኢትዮጵያ ህዝብ የነበረውን ባላባታዊ ስርዓት ለመለውጥ ያካኸደው ስር-ነቀል እንቅስቃሴ በወታደራዊ ደርግ መቀልበሱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ፣ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረት፣ . . .ወዘተ. የመሳሰሉ ዋና ዋና የደርጉ ተቀናቃኝ ኃይሉችን በማስተናገድ በሕይወት፣ በጉልበትና በአቅርቦተ-ንዋይ ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈለና ህዝብ መሆኑ ታሪክ የዘገበው ሓቅ ነው።