በዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ:-
የግዕዝ ትምህርት ነገር ብዙ እያስተዛዘበን ነው
ሰሞኑን የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ የግዕዝ ቋንቋ ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ በትምህርትነት እንዲሰጥ መወሰኑን ተከትሎ አንዳንድ ወገኖች ይኸማ መሆን የለበትም በማለት እየተቃወሙ ይገኛሉ። በምክንያትነት የሚያነሱትም በዋነኛነት የግዕዝ ቋንቋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ሀይማኖታዊ ትምህርትንና እሴትን የሚያስፋፋና ለኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካህናትና ዲያቆናት የስራ እድል የሚፈጥር ስለሆነ ሙስሊሙን ያገላል የሚል ነው።
እነዚህ ወገኖች በተለይም ጽንፈኛ የሆኑ ሙስሊሞች አጋጣሚውን በመጠቀም የአማራ ክልል ት/ቢሮ ልጆቻችንን ክርስቲያን ለማድረግና የክርስትና ሀይማኖትን የበላይነት ለማስፈን ጥረት እያደረገ ስለሆነ መቆም አለበት እስከማለት ደርሰዋል። የሚገርመው ነገር እነዚህ ወገኖች ልጆቻቸውን ከመዋዕለ ህጻናት ጀምሮ እንግሊዘኛ እንዲማሩ ፈቅደው፣ አንዳንዶቹ ፈረንሳይኛ ወይም አረብኛ የሚያስተምር ትምህርት ቤት አስገብተው እያስተማሩ የግዕዝን ትምህርት መቃወማቸው ነው።
በግዕዝ ትምህርት ላይ የተነሳውን ተቃውሞና ለተቃውሞው እየቀረበ ያለውን ምክንያት ስመለከት አንድ ነገር ትዝ አለኝ። የብሔር ፖለቲካ አራማጆች አንድን ብሔር ሕዝብ በጨቋኝነት ይፈርጁና ሌላውን ተጨቋኝ አድርገው ይሰብካሉ። ተጨቋኝ የሚሉት ብሔር ሕዝብ ልጆችም በቋንቋቸው እንዲማሩ ይሰብካሉ። ሆኖም የእነሱ ልጆች የሚማሩት በዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ነው። አሁን ላይ ተቃውሞ ከሚያቀርቡ ግለሰቦች መካከል የዚህ አይነት ሰዎች እንደሚኖሩ ይገመታል።
በሌላ አነጋገር የግዕዝ ቋንቋ በትምህርትነት መሰጠት የለበትም በማለት ጠንካራ ተቃውሞ እያቀረቡ ያሉ ግለሰቦች አንድም ልጆቻቸው በዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ወይም የዛ ተቀራራቢ በሆነ የግል ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ አሊያም የክልሉ ተወላጅ ያልሆኑ አዛኝ ቅቤ አንጓቾች ናቸው የሚሆኑት። በእርግጥ አንዳንድ ወገኖች ሀሳቡ በደንብ ሳይገባቸው ለሀይማኖታቸው ካላቸው ቀናዒነት ተቃውሞውን ተቀላቅለው ሊሆን ይችላል።
እናም የግዕዝ ትምህርት በተቻለ መጠን ከሀይማኖት ተጽዕኖ ነጻ በሆነ መልኩ ተዘጋጅቶ በቋንቋነቱ ብቻ ሊሰጥ ይገባል ማለት የወግ ነው። ከዛ አልፎ መሰጠት የለበትም ብሎ መቃወም በተለይም የይኸ ተቃውሞ ተቋማዊ በሆነ መልኩ ሲቀርብ ግን አንድም ትምህርት ከሀይማኖት ጣልቃገብነት በጸዳ መልኩ መሰጠት አለበት የሚለውን ህገ መንግስታዊ መርህ ይጥሳል።
ለማንኛውም የግዕዝ ቋንቋን የማወቅ ጠቀሜታን በመገንዘብ በትምህርትነት እንዲሰጥ ያደረጉ የዓለም አገራት እና የትምህርትና የምርምር ተቋማት የሚከቱሉት ናቸው።
ሰሜን አሜሪካ (ዩኤስ አሜሪካና ካናዳ)
- ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ (USA);
- አቢለኒ ዩኒቨርሲቲ (USA);
- ፕሪንሰተን ዩኒቨርሲቲ (USA):
- ቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ (Canada);
- ፔንሲልቫኒያ ዩኒቨርሲቲ (USA);
- የአሜሪካ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ (USA);
- UCLA ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ (UCLA, USA)፡
አውሮፓ
- ሀምቡርግ ዩኒቨርሲቲ (ጀርመን);
- ሉድዊግ–ማክሲሚላን ዩኒቨርሲቲ (ጀርመን);
- ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ (እንግሊዝ);
- ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ (እንግሊዝ);
- ሌይደን ዩኒቨርሲቲ (ኔዘርላንድስ);
- ሳፒንዛ ዩኒቨርሲቲ (ጣሊያን);
- ፓሪስ ዩኒቨርሲቲ (ፈረንሳይ);
- ዋርሶው ዩኒቨርሲቲ (ፖላንድ);
በኢትዮጵያ ውስጥ
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና
- ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣
ሲሆኑ ሌሎች በርካታ የትምህርትና የምርምር ተቋማት በትምህርትነት ይሰጡታል። ይኸ የሆነበት ምክንያት የግዕዝ ቋንቋ ጥንታዊ በመሆኑ በረዥም ዘመን አገልግሎቱ ያከማቻቸው ጠቃሚ እውቀቶችና ጥበቦችን ስለያዘ እነዚህን እውቆቶችና የግዕዝ ትምህርት ነገር ብዙ እያስተዛዘበን ነው!
ምንጭ፡ ግሸን ሚድያ ፌስቡክ ገጽ



