Mengistu Musie
Opinion

የበቀለ ገርባ አስተሳሰብ የጃዋር ሀሰታዊ ታሪክ (ሕገመንግስቱ የወያኔ ሳይሆን የነኃይሌፊዳ ነው) ፟

ከመንግስቱ ሙሴ

ጃዋር በሰሞኑ ስለህገመንግስቱ አመጣጥ ታሪክ ብሎ ሲናገር ሕገመንግስቱ ወያኔ አልስጠንም የሰጡን እነ ኃይሌ ፊዳ፣ ሌንጮ እና መሰሎቻችን ናቸው አለን። ዛሬ በቀለ ገርባ በወጣቷ ትንታግ ገጣሚ የተደረሰውን ግጥም ተደፈርን አለ። ጃዋር በህገመንግስቱ አመጣት ታሪክ ብቻ አላቆመም የአብሮነት ታሪክ ኖሮን አያውቅም በሚል በድፍረት ነግሮናል። ምሁር ይሏል እንደጃዋር፣ ምሁር እንደ በቀለ ከሆነ አለማወቅ፣ አለመማር በስንት ጠአሙ እና ጭዋነቱ ሊመረጥ ይገባዋል። የጃዋር የምርምር መስክ ምን እንደሆነ ባላውቅም ስለታሪክ ያለው እውቀት ግን ያልተገራ ፈረስ አስመስሎታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዙ አኩሪ ታሪኮች አሉት። አብሮም ኖሮ ሀገር ሰጥቶናል። የአብሮነት ታሪካችንን ብዙ ባልሄድበት ይሻላል የተመራመሩ የታሪክ ሊቃውንት ስላሉ በነሱ ያምራል። የኦሮሞውን ባልታሪክ መሀመድ ኀሰንን መጻህፍቱን ቢያይ ይቀለዋል። አለማቀፍ እውቅና እና ምሁራዊ ድርሳኖቻቸውን ነፍሳቸውን ይማር የነ ታደሰ ታምራትን፣ ሪቻርድ ፓንክረስትን ማየት እንደሚበዛበት ግን አውቃለሁ።

ሌላው ጃዋር ሊሰማ የሚገባው መርዶ ልንገረው ግን እንደርሱ በጥራዝ ነጠቅ አዋቂነት አይደለም። ወይንም ከትምህርትቤት የአከዳሚክ መጥሀፍት ወስጀም ወይንም በታሪክ አንብቤም አይደለም። ያለፍሁበትን እና አሁንም በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ የትውልድ ተጋሪወቸም እንደሚያውቁት ንቀው በዝምታ ድባብ እንዳለፉት ጃዋር መሀመድ ሊያውቅ ይገባዋል እናም ኃይሌ ፊዳ ዛሬ ቢኖር የጃዋርን ሀሰት በቀላሉ ባጋለጠው ግን የለም ስለሌለም ነው በኦሮሞ ጽንፈኛ የሀሰት ምሁራን ባልሰራው የሚጠቀሰው።

እኔም ጸረ ኃይሌ ፊዳ ብሆንም የኃይሌፊዳን ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ግን ሀሰት ልል አልችልም። ኃሌ ፊዳ በኢትዮጵያ የተማሪ ንቅናቄ መሪወች አንዱ የነበረ፣ በኋላም የ “መላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ” አመራር የነበረ ምሁር ነው። የሀይሌ ፊዳ ግሩፕ ኢትዮጵያ ውስጥ እራሱን የቻለ ብሄር የለም። ኦሮሞም ብሄር ሳይሆን ብሄረሰብ ነው ያለ ነው። እናም ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት እንጅ የኦሮሞ፣ የትግሬ ወዘተ ብሄርተኝነት ሊኖር አይችልም ብሏል። በእርግጥ በዚያን ግዜ ኢሕአፓ የኦሮሞኛ ጋዜጣውን ሲያወጣ እና ሲቀሰቅስ ጽሁፉ በግእዝ ፊደላት መጠቀሙ እና የኃይሌ ፊዳ ግሩፕ ቁቤን ማስተዋወቁ በግዜው የሚታውስ ነው። ኃይሌ ፊዳ ቁቤን ማስተዋወቁ ግን የወያኔን ህገመንግስት ጻፈው የሚያሰኘው አይደለም። በድጋሚ ለጃዋር መነገር ካለበት በህይወት ያሉ የመኢሶን አመራሮች ብሄር የለም ያሉትን ያህል ጓዳቸው የወያኔን የፖለቲካ ሰነድ ቀረጸ የሚለውን ሀሰት በማለት እውነቱን መናገር ይኖርባቸዋል። እሩቅም ሳንሄድ ዶክተር መረራ የመኢሶን አባል እና ካድሬም ስለነበሩ ይህን የጃዋርን ንግግር ቢያስተባብሉ መልካም ነበር። በእርግጥ ብዙ የወለጋ ሰወች መኢሶኖች እንደነበሩ እና የኦነግ መሪወች ሳይቀር ከመኢሶን የወጡ መሆኑ ኃይሌ ፊዳን በሌለበት አድርጓል ሊአሰኘው ባልተገባ። የብዙ የወለጋ ሰወች መኢሶን መሆን እንደሚመስለኝ ያኔም እገምት እንደነበረው ኃይሌ ፊዳ ከወለጋ አባት እና ከአርመናዊ እናት መወለዱ ሳይሆን አይቀርም የሚል አስተሳሰብ አለ።

ሌላው የዛሬው ኦቦ በቀለ ገርባ ስልጣን ቢይዝ ስነጽሁፍን በአዋጅ እንደሚያቆም የሚያሳይ ንግግር አሳይቶናል። ትንታጓ ገጣሚ መንጋ አለችን ብሎም በኦምን ፕሮግራም ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል አየሁ። ሰውየው የነካካው መሆኑ ነው። ነሀሴ የሚያብድ ሰኔ ልብሱን መጣል ይጀምራል እንዲሉ በቀለ የጥላቻው ጥቅ እስከዚህ መድረሱ የሚገርም ነው። ግን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *