ጃዋር መሃመድ
News

ከጃዋር መሃመድ ጋር ተያይዞ የተነሳው ሁከትና ብጥብጥ ኦነግ ከህወሓት ጋር በመተባበር የተጠነሰሰ ሴራ

በትላንትናው ዕለት ከጃዋር መሃመድ ጋር ተያይዞ የተነሳው ሁከትና ብጥብጥ ከህወሓት ጋር በመተባበር የተጠነሰሰ ሴራ እንደሆነ ነግሬያችሁ ነበር። እንሆ ዛሬ አንድ ማንነቱ ካልተገለፀ የደህንነት መስሪያ ቤት ባልደረባ በደረሰኝ መረጃ መሰረት በእርግጥ የትላንቱ ግምቴ ትክክል እንደነበር አረጋግጧል። ይህ ከታች ያለው መረጃ ከህወሓት ሥራ አስፈፃሚ አባል ከሆነው አቶ ጌታቸው ረዳ ኢሜል ሃክ ተደርጎ የተገኘ ነው። በዚህ የኢሜል መልዕክት መሰረት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደርን ጨምሮ ለተለያዩ ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናት የተላከ ነው።

በመረጃው መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እ.አ.አ. ጥቅምት 22/2019 ከፓርላማ ስብሰባ በኋላ ወደ ውጪ ሀገር እንደሚሄዱ በመጥቀስ በተነጋገሩት መሰረት እቅዳቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጃዋር መሃመድ በእለቱ በመኖሪያ ቤቱ እንደሚገኝ ይጠቅሳል። በዚህ መሰረት በጃዋር መሃመድ ላይ ጥቃት ሊፈፀም ነው በሚል የተፈጠረው ሁከትና ግርግር በዋናነት በህወሓቶች የተቀነባበረ ሴራ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። በመሆኑም ማንኛውም ዜጋ በዚህ መልኩ ወያኔ በቆፈረለት ጉድጓድ ራሱንና ሀገሩን ከመክተት እንዲታቀብ ለማሳሰብ እወዳለሁ ::

ስዩም ተሾመ

 

መረጃውን ይመልከቱ:  ኦነግ ከህወሓት ጋር በመተባበር የተጠነሰሰ ሴራ

 

Source: ZeHabesha

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *