የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)
News

ሃገር የማዳን ጥሪ ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ገና ሲመሠረት ጀምሮ ኅብረብሄራዊ የሆነ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሉዓላዊነት፣ ለሃገሪቱ የግዛት አንድነት የማያወላውል አቋም በማንገብ አሁን ድረስ ያኔ የተነሱትን መሠረታዊ የፖለቲካ አቋሞቹን በማጠንከር ትግሉን ቀጥሏል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዋና ዋን አቋሞቹን በማንገብ ያለማወላወል ታግሏል፣ አታግሏልም።

    1. የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ማስከበር፣
    2. እኩልነት የሰፈነባትና ዜጎች በመፈቃቀድ አብረው የሚኖሩባት አገር መገንባት፣
    3. ሉዓላዊነቷን የጠበቀች ሀገር በሁሉም መስክ መገንባት፣
    4. ለሕዝባዊ መንግሥት ምሥረታ በቀዳሚነት በመታገል፣
    5. የመሬት ላራሹን ጥያቄ በማንሳት ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትኅ ጥያቄዎችን በማንሳት፣

አሁንም እነዚህን አቋሞቹን አጠንክሮ በመያዝ፣ በሀገራችን ውስጥ የተፈጠረውን ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ተጠቅሞ ትግሉን በሰላማዊ መንገድ ቀጥሏል። ነገር ግን ይህ አዲስ የተፈጠረው ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እየደበዘዘ መሄዱንም አስተውሏል። በተለያየ መልክ ይህን የመደብዘዝ ሁኔታ ለመንግሥትና ለሰፊው ሕዝብ በተደጋጋሚ ባወጣቸው መግለጫዎችና ቃለ መጠይቆች አመላክቷል።ይሁን እንጂ በመንግሥት በኩል ሁኔታውን ተገንዝቦ የሕግ የበላይነትን በማስከበር እርምት በመውሰድ ፈንታ በትዕግሥት ስም ዝም ብሎ ክቡር የሆነ የሰው ልጆች ሕይወት ሲጠፋና ንብረት ሲወድም ማየትን መርጧል። ይህ አካሄድ ግን ሕዝቧንና አገሪቱን ወደ ከፋ ሁኔታ እየወሰድ ነው። በአሁኑ ስዓት አገሪቱ ህልውናዋ አስጊ ሁኔታ ውስጥ ገብቷል፣ ሕዝቡም ወደ አሰቃቂና ዘግናኝ ግድያ፣ መፈናቀል ገብቷል።

ኢሕአፓ ይህንን ዘግናኝ ሁኔታ ዝም ብሎ የሚታለፍ ነው ብሎ አያምንም። ይህን ሁኔታ የፈጠሩት ኃይሎች ምን ዓይነት ኃይሎች መሆናቸው ለማንም ግልጽ ነው። አሁን ዋጋ እያሰከፈለን ያለው በ1981 ዓ. ም በህወሓት መሪነት ከሌሎች መሰል ድርጅቶች ጋር በመሆን የፈጠሩት ሕገ መንግሥት ሥርዓት ውጤት ነው። እኒህ ኃይሎች አክራሪ ብሄርተኞች በሥጋና በደም ተዋህዶ፣ ለዓመታት ተዋዶ፣ ተከባብሮ በአንድነት የአገሪቱን

ይቀጥላል …

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *