በትግራይ ክልል የሽረ ሕዝብ
News

በትግራይ ክልል የስሜን ምዕራብ ዞን ሽረ አካባቢ የሚገኙ 8 ወረዳዎች ሕዝብ ተቃውሞ‼

መረጃ! – በትግራይ ክልል የሽረ ሕዝብ ተቃውሞ‼
በትግራይ ክልል የስሜን ምዕራብ ዞን ሽረ አካባቢ የሚገኙ 8 ወረዳዎች ሕዝብ በህወሓት አመራሮች ትዕዛዝ እንዲሰበሰብ ጥሪ ቢቀርብም ከ40 ሽማግሌ አዛውንትና እናቶች ውጭ ሌላ ሰው ሊገኝ አልቻለም። ወጣቱ ሙሉ በሙሉ በሰበሰባው ካለመገኘቱ በላይ በየወረዳዎቹ የሚገኙ ሚሊሻዎችም ከእናንተ በላይ ጠላት የለንም እናንተ ናችሁ (ህወሓቶች) አንድነታችን እያፈረሳችሁት ያላችሀት እናንተን ነው መታገል ያለብን በማለት አስጠንቅቀዋል።
.
የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የታችኛውን አመራር ህዝቡን እንዲያሳምኑ እያሰማራ ቢሆንም ህዝብ አልሰበሰብም ስላላቸው <<ሕዝቡ ተሰላችቷል አልሰበሰብም እያለ>> ነው በማለት ካድሬወቹ ቅሬታ እያቀረቡ ነው። በዚህ የተበሳጨው የላይኛው የህወሓት አመራር ታችኞቹን ካድሬወች በበረሃ ዘመን ህግ በድርጅት መስመር ከስራቸው እንዲባረሩ ማስጠንቀቅያ እየሰጠ ይገኛል። <<ይቅር በሉን፣ አጥፍተናል፣ በውስጣችን ያለው ችግር የመልካም አስተዳደር በመሆኑ ለሁሉም መፍትሄ እንፈልጋለን ነገር ግን አሁን ሊውጠን የተዘጋጀ ጠላት ስላለ እሱን አብረን እንምታው>> በማለት በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሕዝቡን እያስጨነቁት ይገኛሉ።
.
በሰበሰባቸው ሕዝቡ እንደማይገኝ ሲያውቁ ወደ ቤተ ክርስትያን ገብተው ህዝቡን ለመስበክ እየቀሰቀሱ ነው። ህወሓት ይከበርልኝ ተናደብኝ የምትለውን ህገ መንግስት አንቀፅ 11 እምነት ተቋማት ላይ ፖለቲካ በመስበክ በጠራራ ፀሃይ እየረገጠቹ ትገኛለች። የህወሓትን አፈና ጥሰው ተቃውሟቸውን በመግለጻቸው የአካባቢው ነዋሪወች ሊታገዙና ሊበረታቱ ይገባል። የማፍያዎች ሴራ እንዲከሽፍ የፌደራል መንግስት ሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የዜግነት ግዴታ አለበትና ከሕዝቡ ጎን ሊቆሙ ይገባል በማለት የመረጃ ምንጮቻችን ገልፀዋል።
.
ህወሓትን ከተቃወሙ የሰሜን ምዕራብ ዞን ወረዳዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል
1 ወረዳ ታሕታይ ቆረሮ።
2 ወረዳ መዳባይ ዛና።
3 ወረዳ አስገደ ፅብላ።
4 ወረዳ ላዕላይ አድያቦ (ከተማ ዒድ ዳዕሮ)
5 ወረዳ ታሕታይ አድያቦ (ኸባቢ ከጠር ሸራሮ)
6 ወረዳ ከተማ ሸራሮ!
7 ወሰዳ ፀለምቲ!
8 ወረዳ ከተማ ሽረ እንዳስላሰ !
.
የሽረ ሕዝብ በፀጉረ ለወጥ የህወሓት አመራሮች አንተዳደርም፣ አንሰበሰብም፣ ራስን በራስ የማስተተዳደር ህገ መንግስታዊ መብታችን ይከበርልን፣ እናንተ አታስፈልጉንም ሲሉ ተደምጠዋል።
ከሽረ ነዋሪ የተገኘ መረጃ ነው

Source: ZeHabesha

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *