News

ህወሓት 8 ፀሃፊያን ቀጥሮ መጽሐፍት እያፃፈ መሆኑ ተሰማ‼ – በሙሉአለም ገ.መድህን

ህወሓት 8 ፀሃፊያን ቀጥሮ መጽሐፍት እያፃፈ መሆኑ ተሰማ – ከመጋቢት/2010 ጀምሮ ራሱን ጦርነት ላይ እንዳለ አድርጎ የሚቆጥረው ህወሃት የለውጡን አመራር ስም ለማጥፋት ሶሻል ሚዲያውንና ሳተላይት ቴሌቪዥኖችን በመጠቀም ላይ እንዳለ ይታወቃል። በተጨማሪነት ከአገር አቀፉ ምርጫ ወዲህ እንዲደርሱ የተፈለጉ መፅሐፍቶችን ለህትመት ለማብቃት÷ ghostwriters ቀጥሮ በማፃፍ ላይ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል ።

ይሄን የመፅሐፍት ዝግጅት ለመስራት ስምንት ፀሐፊያን የተመመሉ ሲሆን
1) ጌታቸው ረዳ ፕሮጀክቱን በበላይነት ይመራዋል
2) ናሁሰናይ በላይ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ነው:
3) ዳንኤል ብርሃነ [አክቲቪስት] የፕሮጀክቱ ተሳታፊ
4) ፍጹም ብርሃነ [አክቲቪስት] ተሳታፊ
5) ነጋ ዘሩ [ጋዜጠኛ] ተሳታፊ
6) መረሳ ፀሃየ [የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህር] ተሳታፊ

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ልዋሃድ እችላለሁ አለ

እንደሆኑ ሰምተናል። የመፅሐፍ ዝግጅቱ ይዘት መረጣ በህወሃት ሥራ አስፈፃሚ ደረጃ ተለይቶ የቀረበ ሲሆን በዋናነት የለውጡ አመራሮችን ስም ማጥፋት ነው። ስማቸውን ለማጥፋት ታርጌት ከተደረጉት ባለስልጣናት መካከል በዋናነት :-
.
1ኛ) ዶ/ር አቢይ አሕመድ
2ኛ) አቶ ደመቀ መኮንን
3ኛ) የደሕንነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ደመላሽ ገ/ሚካኤል
4ኛ) የINSA ኃላፊ አቶ ወርቁ ጋሸና
5ኛ) የኢሕአዴግ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም
6ኛ) ህወሃትን ተሰናብቶ የወጣው የራያው ዛዲግ አብርሃ እና
7ኛ) የኦዲፒ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ታየ ደንዳ ወዘተ
ላይ ያነጣጠረ የስም ማጥፋት ስራዎችን ያካተተ መሆኑን ሰምተናል።
.
ከላይ ስማቸው የተጠቀሱና ሌሎች አመራሮችን ስም ለማጥፋት የኋላ ታሪካቸውንና ስለሚመሩት ተቋም ስም ማጥፋት ÷
👉 በኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎች ውስጥ ሰፊ ቅራኔ ያለ አስመስሎ ማቅረብ ÷
👉 ውህደቱ አሃዳዊ ስርዓትን ለመፍጠር ያለመ ነው የሚሉ መከራከሪያዎች ÷
👉 የሕዳሴው ግድብ ለግብፅ ተሸጧል የሚል መከራከሪያ ÷
👉 ባለፉት ሃያ ወራት የነበሩ የውጭ ጉዳይ ግንኙነቶችን በተለይም ከተባበሩት አረብ ኢሜሬትስና ከሳውዲ ጋር የተደረጉትን እንደ አገር ክህደት አድርጎ ማቅረብ÷
.
የመፅሃፍት ዝግጅቶቹ ይዘት ከላይ በተመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮችና ላይ እንደሚያተኩሩ ሰምተናል። ከምርጫው በፊት እንዲደርሱ ተብሎ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን÷ የመፅሐፍት ህትመቱ ዋና ዓላማ የአመራሩን ስም ማጥፋት ብቻ ሳይሆን በአማራ እና በኦሮሞ ሕዝቦች መካከል መጠራጠርን የሚፈጥሩ የሐሰት መረጃዎች [ODP ለአማራ ተሸጠ Vs ዐቢይ አህመድ የኦነግ አጀንዳ አስፈፃሚ ነው የሚሉ ተቃርኖዎችን በተለያየ መፅሃፍት በማውጣት] የፖለቲካ ቅራኔ ለመፍጠር ያለመ የቅድመ ምርጫ ፖለቲካ መሆኑን ለኢትዮ-ዊክሊክ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

Source: ZeHabesha

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *