ዶ/ር መራራ
News

መራራ፤ እሬት ሆነ – በገ/ክርስቶስ ዓባይ – ዶ/ር መራራ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር መሆናቸው በስፋት ሲነገር ቆይቷል

በገ/ክርስቶስ ዓባይ
ታህሣሥ 30 ቀን 2012

“ጀብ ከማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ!” አለ ይባላል። ዶ/ር መራራ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር መሆናቸው በስፋት ሲነገር ቆይቷል። እርሳቸውም በአንደበታቸው ቀድሞ የአዲስ አበባ የፖሊስ ኮሚሽነር፤ በኋላም የውጭ ጉዳይ ሚንስትር፤ አሁንም የኢጋድ ጸሐፊ ሆነው የተሾሙትን ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን እንዳስተማሯቸው ተናግረዋል። ከዚህም የተነሳ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የነበራቸውን ሠፊ አገልግሎት ምክንያት በማድረግ እንደ ጓደኞቻቸው ሁሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ማግኘት ሲገባቸው መከልከላቸውን፤ አልፎ ተርፎም አንድ ዓመት ሙሉ ያገለገሉበት ደመወዛቸው እንዳይከፈላቸው መታገዱንና ለችግር እንዲጋለጡ መሆናቸውን ሲግልጹ እንደነበር ይታወሳል።

በተጨማሪም የአውሮፓ ፓርላማ ባደረገላቸው ግብዣ ብራሰልስ ቤልጂየም፤ በሄዱ ጊዜ ከግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጎን ተቀምጠው የታዩ በመሆናቸው ወደ አገራቸው ሲመለሱ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስመልክቶ ተደጋጋሚ ግፍ ተፈጽሞባቸዋል፤ በሚል በኢትዮጵያ ሕዝብ ልብ ውስጥ በግባታቸው አይዘነጋም።

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች እርሳቸውን ለማስፈታት ያላንኳኩት የዲፕሎማቲክ በር የለም። በማኅበራዊ ገጽም ቢሆን የትሕነግን አስከፊ የሆነ አምባ ገነንነትና የሰብአዊ መብት ጥሰትና ረገጣ፤ ለኃያላን መንግሥታትና ለዓለም ሕዝብ ለማሳወቅ ያልተደረገ ጥረት አልነበረም።

ለዚህ ትግል በተለይ የአማራው ሕዝብ ጎንደር ላይ በአደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በሕወሃት የሚዘወረው ግዥው መንግሥት ኢሕአዴግ “እሣትና ጭድ” በማለት የፈረጃቸውን የአማራ እና የኦሮሞ ሕዝብ አንድ በሚያደርግ መልኩ “የኦሮሞ ደም የኔም ደም ነው!” የሚል መፈክር በመያዝ ነበር የወያኔን ቅስም የሰበረ። ይኸውም “ ዶ/ር መራራ ጉዲናን እና በቀለ ገርባን” ለማስፈታት እንደነበረ ይታወሳል።

ነገር ግን ‘በቄ’ ከተፈታ በኋላ የወያኔ ነገር አልሆንለት ስላለ በፍቅር ነፍሱ ልተወጣ ደርሳለች። እሥር ቤት ውስጥ በነበረ ጊዜ የሆነ ነገር ሳያቀምሱት እንዳልቀሩ የብዙ ታዛቢዎች ግምት ነው። የፈለገው ቢሆን ለክብሩ ሲል እንኳ መቀሌ መሄድ አልነበረበትም የሚሉ ብዙ ብዙ ተቆርቋሪዎች በቁጭት ሲናገሩ ይደመጣሉ። እሱ እቴ፤ ብዙ ጉድ ነገር ቢሠሩትም ከነፍጠኛው ይልቅ ሕወሃት እንደሚሻለው ምንም ዓይነት የኅሊና ወቀሳ ሳይገጥመው ስብከቱን በይፋ እያጧጧፈው ነው። እንዲያውም ባለውለታችን ስለሆኑ ልንታደጋቸው ይገባል በማለት ወደ ቀድሞ ቦታቸው ለመመለስ እየጣረ መሆኑን ምንም ሳይሸማቀቅ ስሜቱን እየገለጸ ይገኛል። ለነገሩ የወደደ እና ያበደ አንድ ነው ይባል የለ? በቄ አማኑኤል ሆስፒታል የሚወስደው ወይም ሁለት ሰባት የሚያስጠምቀው ችግሩን የተረዳ ቁርጠኛ ዘመድ የሌለው ሆኖ ነው እንጂ ርኩስ መንፈስ ሳይጠናወተው አልቀረም።

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የኦፌኮ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር መራራ ለካስ ለምድ እንደ ለበሰ ቀበሮ ኖረዋል። ገና ከመጀመሪያው ከሕወሃት ጋር ያልተስማሙት ሥልጣን እና ገንዘብ ፈልገው ኖሯል፤ የወያኔው ጠርናፊ መለስ ዜናዊ፤ ዶ/ር መራራ ከአምቦ በመውጣታቸው፤ ቂም ስለያዘ አላቀርባቸው በማለቱ እንደሆነ ባይታወቅም፤ ጊዜው ሲደርስ ግን አሁን ዋናው መልካቸው ተገለጸ።

ለነገሩ በሽግግር ጌዜው ወቅት ዶ/ር መራራ የተወካዮች ምክር ቤት ዓባል ሆነው ማገልገላቸው ይነገራል። የዋሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ጠለቅ አድርጎ ሳያይ ለጠላቱ በመወገን ዘብ ካልቆምኩ በማለት አበሳውን ሲያይ ቆይቷል።

‘አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ’

የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር እውነተኛ ለመሆኑ ምስክር አያሻም። በኦሮሞ ሕዝብ ስም ከተቋቋሙት ደርጅቶችም ሆነ ፓርቲዎች ወደ ቀኝ ያዘነበለ እንደነበር የሚነገርለት በዶ/ር መራራ ጉዲና የሚመራው ‘ኦፌኮ’ ነበር። ነገር ግን ኦፌኮ የሕዝብን ስሜት ለማደንዘዝ ጭምብል አጥልቆ ነበር ሲያታልል የኖረው።

ሙሉውን ለማንበብ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *