Ethiopia defence minister replaced after criticising Abiy
Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed’s office announced Tuesday that he was replacing his defence minister, a fellow ethnic Oromo and former close ally who has recently been openly critical of Abiy’s political reforms.
The ouster of Lemma Megersa, announced on Twitter as part of a broader cabinet reshuffle, underscores tensions between Abiy and other high-profile politicians from his Oromo ethnic group over how Ethiopia’s democratic transition should be managed.
Abiy, the winner of last year’s Nobel Peace Prize, became Ethiopia’s first Oromo leader when he was appointed prime minister in 2018 after years of anti-government protests.
He was tasked with leading the country to landmark elections which were originally scheduled for this year but have been delayed because of the coronavirus pandemic.
Many Oromos contend Abiy has not sufficiently addressed their longstanding feelings of political and economic marginalisation.
In an interview with Voice of America’s Afaan Oromo language service last November, Lemma criticised Abiy’s push to merge the coalition of ethno-regional parties which had ruled Ethiopia for three decades into a single political party known as the Prosperity Party.
Lemma, formerly Abiy’s boss when he was president of the Oromia region, also rejected Abiy’s philosophy “Medemer” (Amharic for synergy) which is aimed at uniting the country.
Lemma was widely believed to have been sidelined for months, with analysts predicting his future as defence minister was untenable.
Earlier this month the Oromia regional branch of the Prosperity Party announced Lemma had been suspended from its central and executive committees, though it was unclear if he had ever actually joined the party.
Lemma will be replaced by Kenea Yadeta, a former security official in Oromia.
Tuesday’s cabinet reshuffle also saw Abiy replace his attorney general and move the mayor of the capital Addis Ababa, Takele Uma, to mines and energy minister.
Lemma is far from the first influential Oromo politician to publicly break with Abiy.
Media mogul Jawar Mohammed has notably become one of the prime minister’s most high-profile critics and last year joined the opposition Oromo Federalist Congress.
Jawar was arrested in July for his alleged role in violence that erupted after the shooting death of popular Oromo singer Hachalu Hundessa.
The violence left more than 200 people dead and highlighted simmering ethnic tensions throughout Oromia, which surrounds the capital Addis Ababa.
Source: yahoo 8/18/2020
ለማ መገርሳ የሀገርና የህዝብ ባለውለታ ነው ! – አበጋዝ ወንድሙ
ባለፈው ሳምንት፣ የኦሮሚያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ለሁለት ቀናት በክልሉ ውስጥ ስላለው ሁኔታና በፓርቲው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስብሰባ ተቀምጦ ነበር። ስብሰባው ሲጠናቀቅ በክልሉ ውስጥ ስላለው የጸጥታ ሁኔታ፣ በዜጎች ላይ ብሄር ወይንም ሃይማኖት ተኮር የሆኑ እጅግ አሳዛኝ ግድያዎችና አካላዊ ጥቃቶች፣መፈናቀሎች ፣ የግለሰቦች ንብረት ውድመትና፣ እጅግ የከፋ የከተሞች ውድመትን አስመልክቶ ስላደረገው ውይይትም ሆነ ችግሩንም በጊዜያውነትም ሆነ በዘላቂነት ለመቅረፍ ያሳለፈው ይሄ ነው የሚባል ውሳኔ አልሰማንም።
ይልቁንም በስብሰባው መጨረሻና ከዛ በዃላ በኦሮሚያ ክልል የብልጽግና ፓርቲም ሆነ በዜና አውታሮች የመወያያ ርዕስ ሆኖ የከረመው፣ በሶስት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የብልጽግና ፓርቲ ወሰድኩ ያለው፣ ከድርጅቱ አመራርነት የማገድ ተግባር ነው።
እግድ ከተጣለባቸው ሶስት የአመራር አባላት አንዱ ለማ መገርሳ ነው። ለማ የዛሬ ዘጠኝ ወር ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ፣ ‘መደመር’ የሚለው እሳቤ ብዙም እንዳልገባው፣ኦዴፓን በአሁኑ ጊዜ አፍርሶ ብልጽግና የሚባል ፓርቲ መመስረትን እንደማይደግፍ ፣ ቢደግፍም አንኳን አሁን ወቅቱ እንዳልሆነና የቸኮለ ውሳኔ ነው ብሎ እንደሚያስብ ሃሳቡን አጋርቶ ነበር።
ይሄ የለማ ቃለ መጠይቅ አነጋጋሪ እንደነበርና፣ እናት ድርጅቱ ኦህዴድንም ባልጠበቀው ወቅትና ሁናቴ መከወኑ ስላሳሰበው ፣ ነባርና የአሁን አመራሮችን ያካተተ ኢ-መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ ለማ ላይ ጫና በማድረግ እርቅ ወርዷል የሚል መግለጫ በጊዜው ሰጥቶ ነበር።
ወርዶ የነበረው እርቅ ምን እንደነበር ድርጅቱ በጊዜው ባለመግለጹ፣ በርግጠኝነት ይሄ ነበር ለማለት ባይቻልም ለማን (መመስረት፣ ቢያንስ ጊዜው አይደለም ብሎ የሚያስበው ፓርቲን ) ከስም ያለፈ የድርጅቱ አመራር አካል ነበር ብሎ ማሰብ ይከብዳል። የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዱም ፣ ለማ የታገደበትን ምክንያት ሲያቀርብ መሰረታዊ ብሎ ያለው በልዩ ልዩ የፓርቲው የአመራርና ሌሎችም ስብሰባዎች አለመገኘትን ነው።
ከዚህ በመነሳት ምናልባትም ለማ ቃለ መጠይቁን በሰጠበት ወቅት እንዳለው፣ ገፍተው (እስኪያስወጡኝ ድርጅቱ ውስጥ ሆኜ እታገላለሁ ያለው) መንግስታዊ ሃላፊነቱን እያካሄደ ፓርቲውን ግን በሚመለከት ውስጣዊ ትግል ሲያካሂድ ቆይቶ ውጤት ለማምጣት ባለመቻሉና ፓርቲው ደግሞ ተፈጥሮ የነበረውን ችግር በእርቅ አስታግሶ አመቺ ባለው ሰዓት የእገዳው ሰለባ አድርጎታል ማለት ይቻላል።
በፓርቲው ውስጥ የተፈጠረው ውዝግብ ምንም ይሁን ምን ክስተቱ፣ ለጊዜውም ቢሆን ለማ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የነበረውን ተጽዕኖ ፈጣሪነት ያከሰመ ነው ብለን ለመውሰድ እንችላለን።
ያም ቢሆን ግን የአበው ብሂል እንደሚለው፣ ለማ ሰው የጠፋ እለት ሰው ሆኖ የተገኘ ነበርና በድርጅት ውስጥ አሁን የተፈጠረው ሁናቴ የለማን የሀገር ባለውለታነት በምንም አይነት ሊያሳንሰው አይችልም ፣ አይገባማምም !!
መስከረም 2008 ዓ. ም. ኦህዴድ አካሂዶ በነበረው አስቸኳይ ስብሰባ ከዚህ ቀደም በኢህአዴግ ድርጅቶች ውስጥ ባልተለመደ መልኩ (እህት የሚባሉ ድርጅቶችን በዋናነትም ህወሃትን ሳያማክር! ) ሙክታር ከድርና አስቴር ማሞን ከክልልና ከድርጅት አመራር (በወቅቱ ሁለቱም በም/ጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የመንግስት ኃላፊዎችም ነበሩ!) አንስቶ ለማንና ወርቅነህን ሲሾም፣ ለማ ነባር የኦህዴድ አባል የነበረ ቢሆንም፣ ከሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የተዋወቀበት ወቅት ነበር።
የክልል ፕሬዘዳንትነቱን ሲረከብ ‘ህወሃት አምላክ አይደለችም’ የሚለውን መርሆውን ተከትሎ የክልሉ ፕሬዘዳንት ከሆነ ማግስት ጀምሮ፣ በተጠና መንገድ በክልሉ ውስጥ የነበረውን የህወሃት ጣልቃ ገብነት መከርከም በመጀመሩ፣ በክልሉ ህዝብ ዘንድ ተሰሚነትንና ትብብርን በማግኘት፣ የክልሉን የጸጥታ ሁኔታ በአንጻራዊነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ማረጋጋት ቻለ።
ይሄንን የህዝብ ተቀባይነት አጉልቶ ያሳየውም፣ በ 2007 ዓ.ም. እሬቻ ክብረ በዓል ላይ የብዙ መቶ ሰዎችን ህይወት የቀጨው ድርጊት እንዳይደገም በማሰብ፣ በ 2008 ዓ. ም. ህዝብ የፌደራል ፖሊሶችና ወታደሮች በስፍራው እንዳይገኙ ያቀረበውን ጥያቄ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ተደራድሮ ማሳካት መቻሉና፣ ይሄም በመሆኑ በዓሉ ያለአንዳች ችግር በስኬት መጠናቀቁ ነበር።
በዚህ ወቅት እሱ ያዋቀረውና ‘የለማ ቡድን’ ተብሎ መታወቅ የጀመረው ስብስብ ከክልሉ አልፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ መፍጠር ጀምሮ ፣በኔ ግምት ሁለት ዋና የምላቸው ተግባራትን አከናውኗል።
በመጀመሪያ ደረጃ ህወሃት ለ 26 ዓመት የበላይነቱን ማስጠበቂያ ዋና መሳሪያ አድርጎ ይጠቀምበት የነበረውን፣ በኦሮሞና አማራ ማህበረሰብ መሃል ጥርጣሬና አለመተማመን፣ ከፍ ሲልም ጥላቻ በመዝራት የገነባውን የክፍፍል አጥር፣ ጎንደር በተካሄደው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ፣ ህዝብ ‘የሚፈሰው የኦሮሞ ደም ደማችን ነው’ በሚል ያበሰረውን የትግል አጋርነት በማጠናከር ፣ ባህርዳር ድረስ በመሄድ ባደረጉት ታሪካዊ ጉዞ መስበር መቻላቸው ነበር ።
ሁለተኛው የነለማ ቡድን ትልቁ አስተዋጽኦ በሻእቢያ የተጎነጎነውን፣ ሀውሃትም ሆነ ሌሎች የብሄር ድርጅቶችን ጨምድዶ ይዞ ብዙ እዳ ያስከፈለንን ኢ -ታሪካዊ ትርክት ድባቅ በመምታት፣ የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር፣በኢትዮጵያ ሃገራዊ ግንባታም ሆነ እድገት ፣እንዲሁም ለረጅም ጊዜ ነጻነቷን ጠብቃ እንድትኖር ያደረገውን አኩሪ ተጋድሎ ትክክለኛ ስፍራውን እንዲይዝ ማድረጋቸው ነው ።
‘የለማ ቡድን’ እነዚህን ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ተግባራዊ በማድረጉም ፣ በልዩ ልዩ ተቃውሞዎች ለስድስት ዓመት ስትናጥ የነበረችው ሀገራችን ውስጥ ሰፍኖ የነበረውን የሀገር መበታተን ፍራቻ በእጅጉ ለማቃለል በመቻሉና የሀገር ባለውለታነቱን በማስመስከሩ ክብርና ምስጋና ይገባዋል።
ለማ መገርሳ በአንድ ወቅት ይሄንን ብሎ ነበር
…ለዚች አገር ለአንድ ዓመትና ለአንድ ቀን አይደለም ለአንድ ሰዓትም ቢሆን ዋጋ የከፈለ ሰው ክብር ሊኖረው ይገባል!! እኛ አገር ዕድሜውን በሙሉ መስዋዕት ያደረገ ሰው ክብር ይሰጠዋል?.. ስንዞርበት ለውለታው ክብር ሳንሰጥ ኑሮውን፣ህይወቱን ሁለመናውን እናመሳቃቅላለን፤ ይህ ነው የእኛ አገር የፖለቲካ ባህል፤ ይህ ነው ከውስጣችን መውጣት ያልቻለው መርዝ !!
ይሄ ክፉ የፖለቲካ ባህል በሱ ላይ መደገም የለበትም የሚል ጽኑ እምነት አለኝ ።
የመከላከያ ሚኒስትሩ በቤታቸው እንዲቆዩ መታዘዙ ተሰማ – ሐይማኖት አሸናፊ
የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ከትላንት ረቡዕ ነሐሴ 6፤ 2012 ጀምሮ በቤት እንዲቆዩ ትዕዛዝ መሰጠቱን የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ታማኝ ምንጮች ተናገሩ። አቶ ለማ በዚህ ሳምንት በስራ ቦታቸው ላይ የታዩ ቢሆንም፤ ከትላንት ጀምሮ ግን ወደ ስራ ቦታ ጭምር እንዳይመጡ እንደተነገራቸው ምንጮች ገልጸዋል።
የኢፌዲሪ የመከላከያ ሚኒስትር በመሆን ከሚያዝያ 2011 ጀምሮ እያገለገሉ ከሚገኙት ከአቶ ለማ በተጨማሪም ለጸሃፊያቸውም ተመሳሳይ ትዕዛዝ እንደተላለፈ ምንጮች አስረድተዋል። በትላንትናው ዕለት በአቶ ለማ ጽህፈት ቤት ላይ ብርበራ ስለመካሄዱ መረጃዎች ቢወጡም፤ የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጮች ግን ይህንን አስተባብለዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ የስራ አስፈፃሚው እንጂ የሰራዊቱ አባል እንዳለመሆናቸው “ወደ ስራ ቦታ እንዳይመጡ” የሚለው ትዕዛዝ ከአስፈፃሚው አካል የመጣ መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የደረሰው መረጃ ያሳያል። ነገር ግን ለአቶ ለማ ይህንን መልክት ያደረሷቸው የጦር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄነራል አደም መሃመድ እንደሆኑ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጫችን ገልጸዋል።ጄነራል አደም ትዕዛዙን ለአቶ ለማ የነገሯቸው ትላንት ሊደረግ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረን አንድ ስብሰባ ለመሰረዝ በተነጋገሩበት ወቅት እንደሆነም እኚሁ ምንጭ ጠቁመዋል። “ሁለቱም ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው፤ ስልጣናቸውም የጎንዮሽ እንጂ የበላይ እና የበታች አይደለም” ሲሉም አክለዋል።
ባለፈው ዓመት ተሻሽሎ በወጣው የመከላከያ ሰራዊት አዋጅ ቁጥር 1100/2011፤ አንቀፅ 23 መሰረት የመከላከያ ሚኒስትሩ ዘጠኝ ዋና ዋና የስራ ተግባሮች አሉት። ተግባራቱ ከሰራዊቱ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ይልቅ የአስተዳደር ስራዎች ላይ ያተኩሩ ናቸው።
በአዋጁ መሰረት ሚኒስትሩ መከላከያን በተመለከተ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ለመከርባቸው እና ሊወሰኑ የሚገባቸውን ጉዳዮች እያቀረበ ያስወስናል። የመከላከያ ሚኒስትሩ የተለያዩ ህጎች እና ፖሊሲዎችን በተመለከተ ሃሳብ የማመንጨት ስልጣን ያለው ሲሆን ሲጸድቁም ስራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል።
እንደ መከላከያ ፋውንዴሽን ያሉ የሰራዊቱን የልማት ተቋማት የመምራት ኃላፊነት ያለው ሚኒስትሩ፤ የመከላከያ ሚኒስቴርን በጀት የማዘጋጀት እና በስራ ላይ መዋሉን በመጠየቅ የማረጋገጥ ስልጣን በአዋጅ ተሰጥቶታል። ይህ አካሄድ የአለም አቀፍ የሲቪሎች ክትትል (civilian supervision) መርህን የተከተለ፤ በህዝብ የተመረጠ አካልን ከዩኒፎርም ለባሹ ሰራዊት ጋር የሚያስተሳስር ነው።
ፎቶ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት
መከላከያ ሚኒስትሩ እነዚህን ኃላፊነቶቻቸውን መወጣት ይጠበቅባቸው የነበረ ቢሆንም፤ ባለፈው አንድ አመት ወደ ስራ ገበታቸው የሚመጡት አልፎ አልፎ ብቻ መሆኑን አንድ ከፍተኛ የስራ ኃላፊ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታውቀዋል። የአቶ ለማ ከስራ ገበታ መቅረት እንግዳ ነገር አይደለም የሚሉት እኚሁ ኃላፊ “በቤት ይቆዩ” የሚለው ትዕዛዝ መሰጠቱም አይስገርምም ባይ ናቸው። ለዚህ አባባላቸውም በማስረጃነት የሚጠቅሱት፤ አቶ ለማ ቀድሞውንም በአብዛኛው በቤታቸው የሚያሳልፉ መሆናቸውን ነው።
አቶ ለማ “በቤት እንዲቆዩ” ትዕዛዝ ቢተላለፍላቸውም በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን እንደተናኘው ጉዳዩ “የቁም እስር” አለመሆኑን በጸጥታው ዘርፍ ያሉ የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጭ ተናግረዋል። “በዚህ ሰዓት ማን፣ ምን አደጋ እንደሚያደርሰባቸው አይታወቅም። ስለዚህም በቤት እንዲቆዩ መታዘዙ ከእስር ጋር የሚገናኝ ሳይሆን ጥበቃ ይመስለኛል” ሲሉም አስረድተዋል።
ትዕዛዙ መተላለፉን ተከትሎ በአቶ ለማ መኖሪያ ቤት ዙሪያ “የተለየ እንቅስቃሴ ታይቷል” በሚል የተሰራጨውን መረጃ ለማጣራት በትላንትናው ዕለት ወደ ስፍራው የሄደው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ “ከወትሮው የተለየ ጥበቃም ሆነ እንቅስቃሴ” ያለመኖሩን ተመልክቷል፡፡ የአቶ ለማ ቤት በሚገኝበት ሰፈር የሚገኙ ሶስት ጥበቃዎችን ያነጋገረው ዘጋቢያችን በአካባቢያቸው ለየት ያለ ነገር ያለመመልከታቸውን ገልጸውለታል።
“ነገሮችን ማባባስ ሳይሆን ማረጋጋት መርጧል። በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረጉ ውይይቶችም ነገሮች ምላሽ ያገኛሉ ብሎ ያምናል። ለዚያም ነው ወደ መገናኛ ብዙሃን መቅረብ ያልፈለገው”
ከሚኒስትሩ ግቢ የወጡ ሁለት የጥበቃ ሰዎች ተመሳሳይ ጥያቄ ሲቀርብላቸው ግራ ሲጋቡ ተስተውለዋል። ጥያቄው ለምን እንደቀረበም ዘጋቢውን ማብራሪያ የጠየቁት የጥበቃ ሰዎች ከተወሰኑ ምልልሶች በኋላ “ሁሉም ነገር ሰላም እንደሆነ” ለዘጋቢው ምላሽ ሰጥተዋል። አቶ ለማም ትናንት ረቡዕ በቤታቸው ማሳለፋቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል።
“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጉዳዩን በተመለከተ የአቶ ለማን አስተያየት ለማግኘት ብትሞክርም፤ የእጅ ስልካቸው ጥሪ የማያስተናግድ በመሆኑ ሙከራው ሳይሳካ ቀርቷል። ሆኖም የአቶ ለማ የቅርብ ጓደኛ፤ ሚኒስትሩ ለመገናኛ ብዙሃን ምንም አይነት አስተያየት መስጠት እንደማይፈልጉ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
“ነገሮችን ማባባስ ሳይሆን ማረጋጋት መርጧል። በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረጉ ውይይቶችም ነገሮች ምላሽ ያገኛሉ ብሎ ያምናል። ለዚያም ነው ወደ መገናኛ ብዙሃን መቅረብ ያልፈለገው” ሲሉም የቅርብ ጓደኛቸው አስታውቀዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
[የኢትዮጵያ ኢንሳይደሩ ተስፋለም ወልደየስ ለዚህ ዘገባ አስተዋጽኦ አድርጓል]
Source: https://www.zehabesha.com/amharic