eprp
Press Release

በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎች ላይ የኢሕአፓ የአቋም መግለጫ

ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢ.ሕ.አ.ፓ) በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎች ላይ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሀገራዊ ምክርቤት አንደኛ አመት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባዉን ከመስከረም 29/2013- ጥቅምት 1/2013 ዓ.ም ሲያካሂድ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የሰላም መደፍረስ ጉዳዮች ላይ በስፋትና በጥልቀት መክሯል፤ ፓርቲው የሚተገብራቸውን የተለያዩ መመሪያዎች፣ እንዲሁም የ2013-2017 ዓ.ም የፓርቲዉን የአምስት አመት ስልታዊ ዕቅድና የ2013 ዓ.ም የአንድ አመት እቅድ በስፋት እና በጥልቀት በመመርመር ወደተግባር እንዲገቡ በሙሉ ድምጽ ዉሳኔ ካሳለፈ በኋላ የሚከተሉትን የአቋም መግለጫዎች አዉጥቷል፡፡

1. ሁሉንም ተግባራት ማከናዎን የሚቻለዉ በሀገሪቱ አራቱም ማእዘኖች ሰላም ሲኖርና የህግ የበይላነት ሲከበር መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነዉ፤ ነገር ግን በመላ ኢትዮጵያ ሀገሪቱን ለ27 አመታት ሲዘርፍና የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በመንፈግ እንደፈለገ ሲያስር ሲገድልና ሲያኮላሽ የነበረዉ ዘረኛዉ ህዉሀት ከጠቅላይ አምባገነንቱ ተባሮ መቀሌ ከመሸገበት እና በዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራዉ‹‹ የለዉጡ ቡድን›› መንግስታዊ ስልጣን ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ሁነቶች ተከስተዋል፡ ፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ እጅግ ዘግናኝ ግድያዎችና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ነፍስ ባላወቁ እምቡጥ ህጻናት ሳይቀር በጽንፈኛ ብሄርተኞችና እነሱ በሚደግፏቸዉ ታጣቂ ቡድኖች፤ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ል (በተለይ በመተከል በተደጋጋሚ) እንዲሁም በደቡብ እስካሁን ድረስ እየተፈጸሙ ነዉ፡፡ ዜጎች በገዛ ሀገራቸዉ እንደሁለተኛ ዜጋ እየታዩ ሀብት ንብረታቸዉ እየተዘረፈና እየወደመ፣ ከመኖሪያ ቀያቸዉ እየተፈናቀሉ ነዉ፡፡

ኢሕአፓ ከዚህ በፊት ባወጣቸዉ ተደጋጋሚ አቋሞቹ እንደገለጸዉ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያሳየዉ ቸልተኝነትና፣ መዘግየት እነዚህ ሁሉ ዘግናኝ ድርጊቶች እንዲፈጸሙ በር እንደከፈተ ያምናል፡፡ ስለዚህ ሉአላዊነታችንንና የህግ የበላይነትን የማስከበር፣ሀገራዊ ሰላምን የማረጋገጥ እና የዜጎችን ደህንነነት የመጠበቅ ሃላፊነት ያለባቸዉን የተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮች የሚመራዉ መንግስት ስለሆነ አሁን የጀመረዉን ህግ የማስከበር ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ በአጥፊዎችም ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ፣ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በቤኒሻንጉልና በኦሮሚያ መሽገው የዜጎችን ህይወት የሚቀጥፉ ህገወጥ ታጣቂ ቡድኖች ላይ ትጥቅ የማስፈታት እና ወደህግ የማቅረብ፤ በወንጀል ድርጊት ያልተሳተፉትን አጣርቶ ወደ ሰላማዊ ኑሮቸዉ እንዲመለሱ የማድረግ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ ይጠይቃል፤ ፓርቲያችን ኢህአፓም ጸረሰላም ሀይሎችን በጽናት ታገላል ፡፡

ሙሉ መግለጫው …

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *