ኅዳር ፲፱ ቀን ፪ ሺህ ፲፫ ዓ. ም
የሰው ልጅ ሕይወት ክቡር ነው። ጦርነት ደግሞ በማንኛውም መሥፈርት አስከፊ ነው፣
ሕይወትን ይቀጥፋል፣ ንብረት ያወድማል፣ አገርንም ሊያፈርስ ይችላል። የአገር ህልውና
ሲደፈርና ሕግ ሲጣስ ግን ዜጎች ከጥፋት ለመታደግና የሀገራቸውን ህልውና ለማስከበር
ሕይወታቸውን መስዋዕት ያደርጋሉ፣ አሁን በሀገራችን እየታየ ያለውም ይኽው ነው። ፀረሕዝብና ፀረ-አንድነት የሆነው ህወሓት ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ አንድነትና ህልውና፣ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስርና ወንድማማችነት ሲያናጋ እንደቆየ የሚታወቅ ነው።
ህወሓት የሕዝባችንን መሠረታዊ የዴሞክራሲያዊና የሰብዓዊ መብቶች ደብዛቸውን
በማጥፋትና በፍጹም አምባገነንነት በዜጎች ላይ ተወዳዳሪ የሌለው ስቆቃ ለአሥርተዓመታት ሲፈጽም ኖሯል።
ለተጨማሪ ቪድዮ Ethio radiodemo ይጎብኙን