shoa fano
News Press Release

ከፋኖ አማራ በሸዋ የተላለፈ መግለጫ!

ከፋኖ አማራ በሸዋ የተላለፈ መግለጫ!

የሸዋ ፋኖ በምንጃር እና ሸንኮራ ልዩ ስሙ አውራ ጎዳና በተባለ ቦታ የኦሮሚያ መንግስት ታጣቂዎች ያደረጉትን ጥቃት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ።

እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ መዋቅራዊ በሆነ ጥቃት ብዙ መሰዋዕትነት መክፈል ከጀመረ ከሰላሳ(30 ) አመታት በላይ አስቆጥሯል ዛሬም እንደ ትላንቱ በመንግስት ስልጣን እና መዋቅር በመታዘዝ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አውራ ጎዳና የሚባል ቀበሌ ላይ የመንግስት ታጣቂዎች ማለትም የኦሮሚያ ልዩ ሃይል የኦሮሚያ ሚሊሻ እና የኦሮሚያ ሰላምና ደህንነት ሃላፊ በጥምረት በከፈቱት ጥቃት የአንድ ወንድማችን ሂወት ሲሰዋ 6 የሚሆንኑ ወንድሞች ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የኦሮሚያ ሚሊሻ ልብስ የለበሱ እና መታወቅያ የያዙ በባለ ሶስት ከከብ ማዕረግ ወታደር እየተመሩ መነሻቸውን መጋቢት 20/2014 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ ዜጎች ላይ የቡድን መሳርያ ተኩስ በመክፈት እና አካባቢው ላይ ያሉ የፌደራል ፖሊሶችን በመግደል ወደ ሌላ ጥቃት ሊሸጋገሩ ሲሉ በጀግናው የምንጃር ህዝብ እና የሸዋ ፋኖ ትብብር ብዙ ጉዳት ሳያደርሱ ቀርተዋል።

ሰላም ወዳዱ የአማራ ህዝብ የማንም ሰው ህይወት ሳይጠፋ እነዚህን ታጣቂ አካላቶች በሰላም እጅ እንዲሰጡ እና በሰላም ችግሩ እንዲፈታ ቢጠይቁም አሻፈረኝ በማለታቸው እና ተኩስ አቁሙ በሰላም እጃችሁን ስጡ ሲል የነበረን ወንድማችን ላይ በመተኮስ በመግደላቸው ብሎም ሌሎች ሰወች በማቁሰላቸው ራስን ለመከላከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ህወታቸው ሊያልፍ ችሏል።

ከላይ እንደተባለው የኦሮሚያ መንግስት የጸጥታ አካል እንደሆኑ ብዙ መረጃወች እጃችን ላይ የሚገኝ ሲሆን ራሱ ገዢው መንግስት ባወጣው ህግ የማንኛውም ክልል ሚሊሻ እና ልዩ ሃይል ወደ ሌላ ክልል ያለምንም ስምምነት ወይም ፍቃድ ወደ ሌላ ክልል መግባት የማይቻል መሆኑ እየታወቀ ድንበር ጥሰው ገብተው ጥቃት ለማድረሳቸው በቂ መረጃ እያለ መንግስት ግን ግጭቱ የተፈጠረው ድንበር ጥሰው በመጡ ታጣቂዎች አማራ ክልል ላይ ጥቃቱን መፈጸማቸውን በመካድ ኦሮሚያ ክልል እንደተፈጸመ አርጎ ያወጣው መግለጫ የአማራ ህዝብን የካደ እና በሞቱት ወገኖቻችን ደም መቀለድ መሆኑ ታውቆ እንዲስተካከል ስንል እናሳስባለን በመሆኑም የሸዋ ፋኖ የሚከተሉትን ባለ 4-ነጥብ መግለጫ አውጥቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለሀገራዊ ዘላቂ ሠላም መስፈንና ለዴሞክራሲያዊ ሥርአት ግንባታ የሚደረግ እልህ አስጨራሽ ጉዞ እያስከተለ ያለው መዘዝ !

1) የዚህ ጥቃት ዋና አቀነባባሪ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት በህግ እንዲጠየቁ ስንል እናሳስባልን

2) በኦሮሚያ ክልል እንደተፈጸመ ተደርጎ በየሚዲያው የሚሰጠው መግለጫ ፍጹም ስህተት መሆኑ ታውቆ የአማራ ህዝብን ይቅርታ እንዲጠየቅ ስንል እናሳስባለን።

3) ኦሮሚያ ክልል ወደ አማራ ክልል የሚደረገውን ህገወጥ ወረራ እንዲያቆም ግጭቱ የተፈጠረው አማራ ክልል ሆኖ ሳለ ኦሮሚያ ክልል እየተደረገ ፈንታሌ ቆርኬ ቀበሌ የተባለው ባስቸኳይ ማብራርያ እንዲሰጥበት እናሳስባለን

4) መላው የአማራ ህዝብ በብልጽግና መንግስት አማራ ላይ እያደረገ ያለውን መዋቅራዊ ጥቃት እውቅና እንዲኖረው ስንል ጥሪያችንን እያስተላለፍን ለቀጣይ መንግስት ሃገር በውሸት እና በሴራ እንደማይመራ አውቆ ከላይ የጠቀስናቸውን ማሳሰቢያዎች ባስቸኳይ መፍተሄ እንዲሰጥ ስንል እያሳሰብን ባስቸኳይ መፍተሄ የማይሰጠን ከሆነ ህዝባችንን ይዘን ወደ ሌላ የትግል ምዕራፍ እንደምንሸጋገር እናሳስባለን

አማራ በልጆቹ ክንድ የተቃጣበትን የህልውና አደጋ ይቀለብሳል!

ሸዋ ፋኖ!

ምንጭ – ዘ፡ሀበሻ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *