Democracia Header
News Press Release

አገራችን ዛሬም አደጋ ላይ ነች!

የሥነ ምድር ጥናቶች እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ (ሉሲ)፣ የሦስት ሚሊዮን ዘመን ባለፀጋ የሆነች ምድር ነች። ኢትዮጵያ የታላቁ የዜማ ሰው የቅዱስ ያሬድም አገር ናት። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 43 ጊዜ ሰሟ የተጠቀሰ ሲሆን የመጀመሪያው ጥቅስ ኦሪት ዘፍጥረት 2:13 “የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል” ይላል። “ትንቢተ-ኤርሚያስም በ13:23 “በእውን ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁን”? ይላል። በእስልምና ዕምነት የታሪክ ማኅደር ውስጥም የመጀመሪያውን ፍልሰት “የስደተኛ መዳረሻ ገነት” የሚል ስያሜ ያሰጣት ወይም ሂጅራን ያስተናገደችው ብቸኛ አገር ኢትዮጵያ መሆኗን ያወሳል።

ታላላቅ የዓለም ዕምነቶች ወደ ተለያዩ አገራት ከተስፋፉበት ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ከማንኛውም አገር አማንያን በላይ ቅዱሳን መጻሕፍትን በትክክል ተከታዮች መሆናቸውን የአሜሪካ የጥናት ማዕከል (ፒው ሪሰርች) እንደ ምሳሌ ይገልጻል። ዓለም ለምትገዛበት የሞራል ሕግጋት ከማንም አገር አማንያን በላይ የሞራል ባለቤቶች ነን።

ኢትዮጵያ የታላቁ የግዮን ወንዝ መነሻ ናት፡፡ በዓለም ውስጥ ከሚገኙት ወንዞች ከደቡብ
ወደ ሰሜን የሚፈሰው ረጅሙ ወንዝ ኢትዮጵያዊው የአባይ ወንዝ ነው፡፡ አባይ ከኢትዮጵያ ተነስቶ የተጠሙ አናፍስትን ጥማት እያረካ 6,650 ኪሎሜትር (4,130 ማይል) ተጉዞ የሜዲትራኒያንን ባሕር ከመቀላቀሉ በፊት ለግብፃውያን የዕለት ጉርስና የኤሌትሪክ መብራት ለጋሽ የሆነው ወንዝ ምንጭ የሆነች የተፈጥሮ ፀጋ ባለሀብት አገር ኢትዮጵያ ነች።

ሙሉ ዲሞክራሲያን ለማንበብ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *