addis abeba
Press Release

አዲስ አበባ የኹሉምና ለኹሉም እንጂ የጥቂት ግለሰቦች ፍላጎት ማስፈጻሚያ አይደለችም

አዲስ አበባ የኹሉምና ለኹሉም እንጂ የጥቂት ግለሰቦች ፍላጎት ማስፈጻሚያ አይደለችም!

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት፣ መኢአድና ኢሕአፓ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ

ባለቤት አልባነት ተጫጭኗት እንደዛሬው ሳይሆን “አዲስ አበባ” ሲባል የሰላም ከተማነቷ፣ እንደነ ኒዮርክ፣ ጀኔቫ፣… ከኸሉም የዓለም ማዕዘናት መሪዎች ተሰባስበው ጉዳያቸውን የሚመክሩባት፣ አፍሪካውያን በባርነት ቀንበር ሲማቅቁ የነጻነታቸው ቀንድል ሆና የትግሉን ፊደል ሀ ሁ… ያስቆጠረች ከተማ ነበረች።

አዲስ አበባ ጎልታ የወጣችው በሕንጻዋ ሰማይ ጠቀስነት፣ በቪላዎቿ ዐይነ ገብነት፣ በመንገዶቿ ማማር፣ በቴክኖሎጂ ርቀቷ ሳይሆን በነዋሪዎቹ እንግዳ ተቀባይነትና አይበገሬነት፣ በሰላማዊነቷ፣ በተስማሚው የአየር ንብረቷና በቁርጠኛ መሪዎቿ ነበር።

ቀደም ያለውን ነገር ትተን በ1879 ዓ.ም በብርሃናተ ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ከተቆረቆረች ወዲህ እንኳን አዲስ አበባ እንደ ስሟ እንድታብብ ጠጠር ያልወረወረ ኢትዮጵያዊ አለ ለማለት ያስቸግራል፡፡ ኹሉም ኢትዮጵያዊ በነባርነት ኖሮባታል፣ ኹሉም ዋና ከተማውን ላለማስደፈር ተዋድቆላታል፣ ኹሉም ሠርቷታል እና “ኹሉም” በኩራት “የእኔ” ይላታል፡፡ ዛሬ ላይ አዲስ አበባ አይደለም የመላው ኢትዮጵያውያን የመላው አፍሪካውያን ዋና ከተማ ሁናለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *