መኢአድ ( ኢሕአፓ ) እና እናት ፓርቲዎች ሦስቱ ፓርቲዎች ይህንን ለማድረግ ያስችለናል ያሉትንና ዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ማለትም ሀገራዊ የምክክር ሥራው እንዴት መከናወን አለበት ?በኢትዮጵያ የተባባሰው የመብት ጥሰትና የዜጎች እልቂት ቆሞ ሰላም እንዴት ሊሰፍን ይችላል? በሚሉና በምርጫ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመሥራት የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።
መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ( ኢሕአፓ ) እና እናት ፓርቲዎች በቅርብ ጊዜ ቅንጅት እንደሚፈጥሩና በሂደት ወደ ውሕደት እና ግንባር እንደሚሸጋገሩ አስታወቁ። ሦስቱ ፓርቲዎች ይህንን ለማድረግ ያስችለናል ያሉትንና ዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ማለትም ሀገራዊ የምክክር ሥራው እንዴት መከናወን አለበት ?በኢትዮጵያ የተባባሰው የመብት ጥሰትና የዜጎች እልቂት ቆሞ ሰላም እንዴት ሊሰፍን ይችላል? በሚሉና በምርጫ ጉዳዮች አብሮ ለመሥራት የትብብር ስምምነት ሲፈራረሙ ነው ይህ የተገለፀው። ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ምህዳሩ በገዢው ፓርቲ ጥንካሬ ሳይሆን በተቃዋሚ ፓርቲዎች መለያየትና መበታተን፣ ችግር በፈጠረው አዙሪት ውስጥ እንዲወድቅ በማድረጉ ፓርቲዎች ወደ ውስን ቁጥር ተሰባስበው ጠንካራና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማስፈለጉ ለመተባበር መስማማታቸውን አስታውቀዋል።በስፍራው የተገኘው ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝርሩን አዘጋጅቷል።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት “ለራሷ ሰላም ያጣች ፣ ዜጎቿ የጎሪጥ የሚተያዩባት ፣ ኢፍትሓዊነት ፣ ጦርነት፣ ረሃብ፣ ስደትና ጉስቁልና መገለጫዋ ሆኗል” የሚሉት መኢአድ ፣ ኢሕአፓ እና እናት ፓርቲዎች የዚህ ሁሉ ምስቅልቅል መነሻው ሥር የሰደዱ ብዙ ጉዳዮች ቢሆኑም ዋናው “ኹነኛ አመራር እና አስቻይ ሥርዓት ያለመዘርጋት” ነው በማለት የእናት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አቶ ጌትነት ወርቁ ገልፀዋል።”ዛሬ በይፋ የምንፈራረመው ትብብር እንዲህ ሀገርና ሕዝብ ጭንቅ ላይ በወደቁበት ፣ የሕዝብ ሞት ለርእስ እንኳን በማይበቃበት ጊዜ በትብብር ቆመናል ለማለት፣ ለሌላውም አርዓያ
ለመሆን” ነው ብለዋል።ኢትዮጵያ ውስጥ ከ 100 በላይ የፖለቲካ ድርጅቶች ከእውቅና ሰጪው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፈቃድ ወስደው የነበረ ሱሆን አሁን በግማሽ ዝቅ ብለዋል። በሀገሪቱ ውህደትም ተደርጓል፣ ግንባርም ተፈጥሯል፣ ቅንጅትም ተመስርቷል። ሆኖም ሀገሪቱ ላይ መሰረታዊ የፖለቲካ – ኢኮኖሚ ለውጥች አይታዩም። ይህ የናንተስ መሰባሰብ ከዚህ በምን ይሻል ይሆን የተባሉት የመኢአድ ፕሬዝዳንት ማሙሸት አማረ ምላሽ ሰጥተዋል።
“አንዱ የመፈረካከሱ ምክንያት መንግሥት ጣልቃ እየገባ ነው። የሀሰት ውንጀላዎች እና የራሳችን የፓርቲዎች መዳከም አለ” ይህም ድጋፍ ይሻል ብለዋል።
ደስታ ጥላሁን የኢህአፖ ዋና ፀሐፊ ናቸው። ሦስቱ ፓርቲዎች ባደረጉት ትብብር ውስጥ ሌሎች እንደሚቀላቀሉ ከሳወቁ በኋላ ለምን የሉም ? ተብለው ተጠይቀው ሲመልሱ
“አሁን ያለው የሀገሪቱ የፖለቲካ መለዋወጥ ዛሬ ያላቸውን አቋም ነገ የሚለውጡበት ሁኔታ ላይ ነው ያሉት” በማለት ተችተዋል። አቶ ማሙሸት እንደሚሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች መበታተን ሌላኛውን ፓርቲ እድል እንዲያገኝ አድርጓል ስለሆነም ተገዳዳሪ ፓርቲዎች እንዲወጡ መሰል በጋራ መሥራቶች መጠናከር አለባቸው።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ
ምንጭ – https://www.dw.com/