Save Ethiopia Forum
Analysis Politics

የሽግግር መንግስት ማቛቛም ሂደት፣

በኢትዮጵያ ሊከሰቱ የሚችሉትን ቢሆኖች ካየን በኋላ አካታችና ዲሞክራሲያዊ 
የሆነ ስርዓት ለመፍጠር ምን ይደረግ በሚለው ላይ የሁሉም ትኩረትና አስተዋጽኦ 
ይጠይቃል። ኢትዮጵያን የማዳን መድረክ ለዚሁ መነሻ ሊሆን ይችላል ያለውን 
ፍኖተካርታ እንደሚከተለው ያቀርባል።

የሽግግር መንግስት የሚመሰረተው የለውጥ ሃይሉ አሸናፊ ሆኖ ሲወጣ ወይም መንግስትን በማስገደድ ወደ ድርድር ሲመጣ ነው የለውጥ ሃይሉ አካታችና አሳታፊ መሆን እንዳለበት ቀደም ሲል ተገልጿል። የለውጥ ሃይሉ ስንል ኢትዮጵያዊነትንና አንድነትን የተቀበሉ፣ ለፍትህና ለሰላም እንዲሁም ለዲሞክራሲ የሚታገሉትን የተለያዩ የታጠቁ ሃይሎችን፣ ክልልሎችን እና የፖለቲካ ድርጅቶችን ያካተተ ግንባር ማለት ነው። ይህ ግንባር በውስጡ ወይም በጋራ ከመንግስት ጋር በሚያደርገው የስልጣን ክፍፍል በሽግግር ጊዜ የህግ አስፈጻሚነትን (executive)ተግባር ይፈጽማል። የፍትህ አካሉ(judiciary) በነጻነት እንዲሰራ ይደረጋል። ፓርላማው ፈርሶ በሽግግር ወቅት የሚቋቋም ጊዚያዊ ህዝባዊ ሸንጎ ይኖራል። ህዝባዊ ሸንጎ በሽግግር ወቅት የሚያስፈልጉትን ህጎች ያጸድቃል። በህገመንግስቱ ለሽግግሩ እንቅፋት የሚሆኑትን አንቀጾች ያስተካክላል ወይም ያነሳል። ለመደበኛ ፓርላማ ምርጫን አስመልክቶ የሚያስፈልጉ ህጎችና አሰራሮችን ያወጣል። መደብኛ ፓርላማ ሲመረጥ ጊዚያዊ ህዝባዊ ሸንጎ ስራውን ያቆማል። የለውጥ ግንባሩም በፓርላማ ለሚመረጠው መንግስት ስራውን ይለቃል።

የለውጥ ግንባሩ የሽግግር ሸንጎ እስኪመሰረት ድረስ የመንግስት ስልጣኑን ይዞ እንደ ሞግዚት መንግስት ይሰራል። የሞግዝት መንግስት ስራና ሃልፊነት በዚሁ ሰነድ መጨርሻ ላይ ተገልጿል።

ግዚያዊ ህዝባዊ ሸንጎ ለማቋቋም አገራዊ መፍትሔ አፈላላጊ ግብረ ሃይል  ይቋቋማል። ይህ አካል የለውጥ ግንባሩ በሰየመው ኮሚቴ /አሰባሳቢ ኮሚቴ/ ይቋቋማል። የሚከተለውን ቅደም ተከተል ይዞ ይሂዳል፣

  1. አሰባሳቢ ኮሚቴ
  • በለውጡ ግንባር (በሞግዚት መንግስቱ) ይሰየማል
  • የስራ መመሪያውን ያዘጋጃል፣
  • ለስራ ማስኬጃ የሚሆን በጀት ከሞግዚት መንግስቱ ይጠይቃል፣
  • በአገራዊ መፍትሔ አፈላላጊ ግብረ ኃይል ውስጥ ሊሳተፉ የሚችሉ አካላት/አባላት የምርጫ መስፈርት ያዘጋጃል፣
    ለአገራዊ መፍትሔ አፈላላጊ ግብረ ኃይል የሚመጥንና የሚሆን መታዳደሪያ ደንብ ያዘጋጃል፣ ጊዜው ሲደርስም፣ በግብረ ኃይሉ እንዲጸድቅ ያስደርጋል፣
  • የአገራዊ መፍትሔ አፈላላጊ ግብረ ኃይሉ ዓላማና ግብ ምን እንደሆነ የሚዘረዝር ሰነድ ያዘጋጃል፣
  • በመስፈርቱ መሰረት የአገራዊ መፍትሔ አፈላላጊ ግብረ ኃይል ተወካዮች ተመርጠው ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ፣ኃላፊነት ተከፋፍለው ስራ ይጀምራሉ።
  •  የአገራዊ መፍትሔ አፈላላጊ ግብረ ኃይል ስለመቋቋሙና ስለሚያከናውናቸው ተግባሮች ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለዓለም ያሳውቃል። ተቋሙን እንዲተባበሩት ያሳስባል። ከዚያም ይህ አካል ራሱን ያከስማል።
  • ግብረ ኃይሉ ከፈለገው ይህ አካል በአማካሪነት ሊቆይ ይችላል።
  1. አገራዊ መፍትሔ አፈላላጊ ግብረ ሃይል

 

ሙሉ ሰነዱን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *