https://www.zehabesha.com/amharic
News

ሕወሓትን እየተጋፈጠ ካላው ከአምዶም ጎን እንቁም የወዳጆቹ ጥሪ! – አብርሃ በላይ

የአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አምዶምገ/ሥላሴ ሰሞኑን ሕወሓት በትግራይ እየደረሰበት ካለው ተቃውሞ አንጻር ተጠያቂ በማድረግ ከኪራይ ቤት እስከ ማስወጣት ደርሰዋል። የሰዎቹን ጭካኔ ለሚያውቀው የቀረው ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን በኮሮና ቫይረስ መከላከል ስም የፈጸሙትም ግድያ ገና ተጨማሪ ተቃውሞ ያስነሳብናል የሚል ሥጋት ላይ ወድቀዋል። ይህን ተቃውሞ ይመራሉ ብለው ከሚፈሩዋቸው አንዱ አንድም ነው። ዛሬ ቀርቶ አራት ህልም ስልጣን ላይ እያሉ በትግራይ ተቃውሞ ብርቅ በሆነበት ወቅት መቀሌ ሮማናት አደባባይ የከበቡትን የትግራይ ልዩ ሀይሎ ሳይፈራ ከአሥር የማይበልጡ ለተቃውሞ ሰልፍ በመውጣት አፈና በቃኝ ብሎ በግልጽ ለወጣቱ አርአያ ሆኗል። ዛሬስ ወዳጆቹ ያቀረቡትን ከአምዶም ግን የመቆም ጥሪ ያንብቡት ይደግፉ

“ለፍትህና ለዴሞክራሲ መከበር በመጮሁ ብቻ አክቲቪስት አምዶም ገ/ስላሴ ትናንት ተከራይቶ ይኖርበት ከነበረው ቤት ለ2 አመት ህጻን ልጁን እንኳን ሳይራሩ አውጥተውታል። “ሳባ” ብሎ የሚጠራት ህፃን ልጁን ደግሞ በሀገሩ በኢትዮጵያ አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ባንዴራ ስለሚያስጊጣት፣ ትህነጎች ይበልጥ ይቃጠላሉ። አከራዮችን ጠርተው፣ እሱን ካላባረርክ አንተ ትገባበታለሁ እያሉ አክቲቪስቶችን መኖሪያ ያሳጧቸዋል። ኢትዮጵያዊው ወገኔ የትግል አጋርነትህን በሞራል ይሁን በማተሪያል በቻልነው አቅም አምዶምን አይዞን ልንለው ይገባናል።”

አብርሃ በላይ

https://www.gofundme.com/f/Help-Amdom-and-His-Family?utm_source=customer&utm_medium=copy_link-tip&utm_campaign=p_cp+share-sheet&fbclid=IwAR0r_tLCQvhVatwNMzIHlWOFKulL7Azvqu1Vo75_RUOpqWM2Pv7Dd1hNQNM

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *