badr ethiopia
News

ረ መ ዳ ን ሙ ባ ረ ክ

አፕሪል 12, 2021

በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በዲያስፖራ የምትገኙ ሙስሊም ወንድምና እህቶችእንዲሁም ለዓለም ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ለ 1442 ኛዉ  ዓመተ ሂጅራ የረመዳን ወር አላህ (ሱብሁዋነሁ ወተአላ) በሰላምና በጤና አደረሳችሁበማለት ምኞቱን ይገልጻል።

በሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከዉጭ እና ከዉስጥ ዘርፈ ብዙ ችግሮችየሀገሪቱን አንድነትና ሰላም እየተፈታተኑ መሆኑን  በድር ኢትዮጵያይገነዘባል ። በዚህ ፈታኝና ወሳኝ ወቅት በተደጋጋሚ የንጹሀን ዜጎች በግፍ መገደል ፤ መሰደድ ፤ መፈናቀል  ብሎም ሰላም ማጣት አሳሳቢ ጉዳይ በመሆኑ ይህንኑ የመከራ ጊዜን ለመሻገርማህበረሰቡ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ ግድ የሆነበት ወቅት ላይ እንገኛለን።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ተቋማዊ አደረጃጀቱንአስመልክቶ በሚያዝያ 23/2011 በሸራተን አዲስ የተላለፈዉን ዉሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የተቋሙ ህገ ደንብ በሚፈቅደዉመሰረት የጠቅላላ ጉባኤዉ መጠራቱ ተገቢ ነዉ። በጠቅላላ ጉባኤዉ የተላለፉትን ዉሳኔዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ መንግስትና የሚመለከታቸዉአካላት አስፈላጊዉን ህጋዊ ከለላና ድጋፍ እንዲያደርጉ ለማሳሰብ እንወዳለን።

በጉባኤዉ ሂደት በተለያዩ የዉጭ አካላት በኡለማዎቻችንና አዛዉንቶቻችንላይ ክብር በሚነካ መልኩ የደረሰዉ እንግልትና ወከባ የህግ መሰረት የሌለዉ ግልጽ ጣልቃ ገብነት በመሆኑ አስፈላጊዉ እርምት ሊወሰድይገባል። ኡለማዎቻችን በመካከላችሁ ያሉትን ልዩነቶች ለመፍታት በቂ እዉቀት፤ ልምድና ቁርጠኝነት ያላችሁ በመሆኑ በሙስሊሙ መካከልሱፊ ሰለፊ ወይም ሌላ ስያሜ እየሰጡ ለመከፋፈል የሚደረገዉን ማንኛዉንም አንቅስቃሴ ተሻግራችሁ ለሙስሊሙ የአንድነት ብስራት እንደምታሰሙትሙሉ እምነት አለን።

የዘንድሮዉን ረመዳን ችግሮቻችንን ታሳቢ በማድረግና አላህ (ሱብሁዋነሁወተአላ) ባዘዘን መሰረት በተቀደሰዉ የረመዳን ወር መልካም ስራዎችን በማብዛት ምንዳችንን ከፍ ለማድረግ ለተፈናቀሉ ዜጎች ልዩትኩረት በመስጠት መርዳት ፤ የተራቡ ወገኖቻችንን በመመገብ ፤ የተጎዱትን በመርዳት፤ የታመሙትን በመጎብኘትና ጾማችንን ከሚያበላሹስራዎች በመቆጠብ ዉጤቱ እንዲያምር ማድረግ ይጠበቅብናል።

በመጨራሻምለሀገራችንና ለህዝቦቿ ሰላም እንዲመጣ አበክረን ፈጣሪያችንን በጸሎት መለመንና በየበኩላችን የሚጠበቅብንን ሁሉ በማድረግ መጪዉ ጊዜየተሻለ እንዲሆን መልካሙን በመመኘትና በመተግበር የተሳካ የረመዳን ወር እንዲሆንልን እንመኛለን።

በድር ኢትዮጵያ     ሰሜን አሜሪካ     አፕሪል 12, 2021

 

Source: https://badrethiopia.org/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *