All parties counsel
Press Release

የውጭ ጣልቃ ገብነትን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ጠንካራ የውጭ ግንኙነት ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ በሀገራት መካከል የሚደረግ ግንኙነት የዓለምን ሰላም ለማስከበር፣ በሀገራት መካከል መልካም ግንኙነትን ለማጎልበት፣ ዓለማቀፋዊ ትብብርን ለማጠናከር ይረዳል፡፡ በረዥሙ የመንግሥትነት ታሪኳ፣ ሀገራችን በውጭ ግንኙነት ዘርፍም የረዥም ጊዜ ልምድ እና ሰፊ ተሞክሮ ባለቤት ናት፡፡ ከአፍሪካ፣ ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካ፣ ከአስያ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር የረዥም ጊዜ የዲፕሎማሲ ታሪክ አላት፡፡ ነፃነቷን አስጠብቃ የኖረችው ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ በተለያዩ ወቅቶች ሉአላዊነቷን የሚፈታተኑ ልዩ ልዩ የውጭ ጫናዎች እና ጣልቃ ገብነቶች አጋጥመዋታል፡፡ በመሆኑም የሀገራችን የውጭ ግንኙነት ታሪክ በስኬቶች እና ተግዳሮቶች የተሞላ ነው፡፡

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ አንዳንድ የጎረቤት ሀገራት እና በሩቅ የሚገኙ የአውሮፓ እና የአሜሪካ መንግስታት በኢትዮጵያ ላይ እያደረሱት ያለው ጫና እየጨመረ መጥቷል፡፡ በምዕራብ የሀገራችን ክፍል የሱዳን መንግስት ወታደሮች ድንበራችንን ጥሰው በመግባት መሬታችንን ወረዋል፣ ሕዝባችንን አፈናቅለዋል፡፡ በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ድንበራችንን አቋርጠው የገቡ የኤርትራ ወታደሮች ግዛታቻንን ለቀው ስለመውጣታቸው እስከ አሁን ግልጽ መረጃ የለም፡፡ የግብጽ መንግስት በአባይ ወንዝ ላይ የመጠቀም ተፈጥሯዊ እና ህጋዊ መብታችንን በመካድ የታላቁን ህዳሴ ግድብ ግንባታ ለማስተጓጎል፣ ብሄራዊ ጥቅማችንን እና ሉአላዊነታችንን በመፈታተን ላይ ይገኛል፡፡  ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *